Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 11594
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

የአማራ ህዝብን በዘመነ አቢይ ምን አተረፈ? ህወሓት የአማራ ህዝብን ጠላት አድርጎ አስቀምጦ ነበር ?? ወይስ ... By Finfinne Times

Post by sarcasm » 25 Apr 2022, 08:03

ህወሓት የአማራ ህዝብን ጠላት አድርጎ አስቀምጦ ነበር ?? ወይስ ...

ለማንኛውም በዘመነ ኢህአዴግ (ህወሓት ) በአማራ ክልል .. በመሰረተ ልማት የአስፓልት መንገድ 60% ፥የትምህርት ተደራሽነት 70%፥ የጤና ሴክተር 90% ሲያሳድጉ ግዙፍ ኢንቨስትመንትን ጨምሮ የአማራ ክልል አሁን የሚኮራበት ኢንዱስትሪዎች እንዲኖሩ ተደርጓል።

የአማራ ህዝብ ከ80% በላይ አሁን ያለው ትውልድ ትምህርት እንዲያገኝ ያደረገው የመለስ የልማታዊ መንግስት ፖሊሲ ውጤት ነው።
የትራንስፖርት የንግድ የአግልግሎት ዘርፉ እንዲቀላጠፍ መሰረት የተጣለው ብሎም እንዲያድግ የተደረገው በዘመነ ኢህአዴግ ነው። ከ24 ሚሊየን ህዝብ ቁጥር በላይ ይዞ አማራ ክልል እንዲመሰረት ጠንካራ ክልል እንዲሆን ያደረጉት የህወሓት ፖሊሲ ነው።

አሁን ላይ አማራ ክልል በጦርነቱ ምክንያት ወድሞብኛል እያለ በትሪሊየን የሚጠራው የንብረት ግምት የዘመነ ኢህአዴግ ውጤቶች ናቸው። ፖሊዮን ጨምሮ በእጅግ ብዙ ወረርሺኞች በየጊዜው ሲጠቃ የነበረው ክልል ላይ ወረርሽኙን ከማጥፋት ጀምሮ እስከ ቀድሞ መከላከል የደረሰ የጤና መድህን እንቅስቃሴ የተደረገው በዘመነ ኢህአዴግ ነው።

አማራ ክልል አሁን ላይ ካሉት ከ10 በላይ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የተገነቡት በዘመነ ኢህአዴግ ነው።

የአማራ ህዝብን ደርግ በቀይ ሽብር ታፔላ ገድሎታል አፄ ሀይለስላሴ በሀይማኖት ሸብበው ኃላ አስቀርተውታል በዘመነ አብይ በጦርነት ምክንያት እንዲደቅ ሆኗል።
አንድ ብቸኛው የማይካደው ነገር ... ከነችግሮቹ የአማራ ክልል ልማት ሆነ እድገት ያስመዘገበው በዘመነ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ነው !! ባሻዬ ምንም አትካድ ዝም ብለህ ዋጠው !! እንደውም ከሌሎች መሪዎች የተሻለ የመራህ ኢህአዴግ ነው።

መሪነት በክራርና በማሲንቆ ማስጨፈር ከመሰለህ ወይም ኢትዮጵያ ትቅደም እያሉ ማውራት ብቻ ነው ብለህ ካሰብህ አጫፋሪ መሪዎች ሞልተውልሃል ባሻዬ .. ህወሃት ጠላት ቢያደርግህ ኖሮ የሚኖርህ ክልል ሳይሆን መንደር ነበር። ልማት ሳይሆን ችግር ነበር .. ህይወት ሳይሆን ሞት ነበር።

ባሻዬ ተረጋጋ 😁 !!
Finfinne Times
Please wait, video is loading...