Prioritize! Prioritize! Prioritize!
What kind of stewardship of public resources is this?
Do these people understand the tradeoffs of their economic decisions on how they use scarce public resources?
ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በዛሬው እለት ለ2000 ሰዎች የማእድ ማጋራት አከናወኑ፡፡
የከተማ አስተዳደሩ በዛሬው እለት በመላው ከተማይቱ ከ195ሺህ በላይ ለሆኑ ዜጎች የማእድ ማጋራት ስነስርዓት እያከናወነ ሲሆን ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በአጠቃላይ የከተማውን የማእድ ማጋራት በማስጀመር በከተማ ደረጃ ለ2000 ሰዎች ማእድ አጋርተዋል፡፡
በዚህ ስነስርዓት ላይ አስተያየታቸውን የሰጡት ከንቲባ አዳነች ከህዝባችን ጋር አብረን እንዳለን ፤ስለነሱ እንደምናስብ ፤እንደምንጨነቅ ካለን በማካፈል እነሱን እንደምናገለግል የምንገልፅበት ፕሮግራም ነው ብለዋል፡፡
አላማውም አሁን ያለውን ከፍተኛ ዋጋ ግሽበት ማቃለልና መደጋገፍ ነው ያሉት ከንቲባ አዳነች በከተማችን ብዙ ደጋፊ የሌላቸው፤ ብዙ ተመልካች የሌላቸው ሰዎች አሉ፤ እነዚህን ወገኖች ጠጋ ብለን ኑሯቸውን በመመልከት የተለያዩ ድጋፎችን ልናደርግላቸው ይገባል ብለዋል፡፡
ነገር ግን ይህ አሁን የገጠመንን ችግር የምንሻገርበት ጊዝያዊ መፍትሄ ነው ያሉት ከንቲባ አዳነች በዘላቂነት ችግሮችን ለመፍታት የከተማው አሰርተዳደር ጎን ለጎን በርካታ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡
ከዚህ ውስጥ ምርትን በማሳደግ ተግቶ በመስራት፤ ስንፍናን በማስወገድ የአኗኗር ዘይቤን በማሻሻል፤ የግብይት ሰንሰለቱን በማሳጠር ፤እና ምግባችን በጓሮአችን ብለን በመነሳት በከማ ግብርና የምግብ ዋስትናችንን ለማረጋገጥ እየሰራን ነው ህብረተሰቡም ይህን ስራ ሳያቃልል ሳይንቅ በዚህ ስራ ላይ ሊረባረብ ይገባል ብለዋል፡፡
ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አስተዳደሩ ለዚህ ተግባር 600 ሚሊዮን ብር ማሰባሰቡን ገልፀው 500 ሚሊዮን ብር ከአስተዳደርና ከህዝብ አቅም በማስተባበር መዋሉን ገልፀው ቀሪውን 100 ሚሊዮን ብር የከተማዋ በጎ ባለሃብቶች (አዋሽ ባንክ ሚድሮክ፤ ሆራ ትሬዲንግና ፤ MWS ትሬዲንግ) ላደረጉት አስተዋፅኦ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
መስጠት አያጎድልም!! በመስጠት ምክንያት ብዙ በረከት ወደ ስራችሁ ይገባል፡፡ መልካምነትን ታተርፋላችሁ፤ ታስተምሩበታላችሁ፤ ያሉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለነጋዴው ማህበረሰብ ባስተላለፉት መልእክት በዚህ ወቅት ለህዝቡ ማዘን አለባችሁ ለትርፍ ብቻ ሳይሆን ዜጎችም እንዳይጎዱ ለህሊናችሁ ስሩ ብለዋል፡፡
የከተማችን መካከለኛ ገቢ ያላችሁ ሰዎች ሰው ባያያችሁም የሚያያችሁ አለና ከሁሉ በላይ አጠገባችሁ የሚኖሩ ሰዎችን ማእድ አጋሩ፤የምታጋሩት ባይኖር እንኳን ፍቅራችሁን አጋሯቸው አትንፈጓቸው በማለት መልእክት አስተላልፈዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ህብረተሰብ ተሳትፎ ማስተባበርያ ሃላፊ አቶ አስፋው እንደተናገሩት ደግሞ ከእነዚህ ድጋፎች የዛሬውን ጨምሮ በአጠቃላይ ለ240ሺህ እማወራና አባወራ የማእድ ማጋራት መከናወኑን ገልፀው ከዚህ በተጨማሪ ባለፉት ሁለት ሳምንታት ታላቁ የረመዳን ወርን ምክንያት በማድረግ በወረዳ ደረጃ 77 የአፍጥር ፕሮግራሞች መከናወኑንና 18ሺህ 335 ሙስሊም ወንድምና እህቶች ጋር ማፍጠር መቻሉን ገልፀዋል፡፡

Please wait, video is loading...