Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 11594
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

ወዲ አፎም የአማራ ወጣትን በምዕራብ ትግራይ በመማገድ የስልጣን ጊዜያቸውን ለማስረዘም አሰፍስፈዋል። ፖለቲካው ከመሬቱ በላይ ነው! እነ ባሻዬ መሬት መሬት እያዩ ለመበላት እየተዘጋጁ ነው

Post by sarcasm » 16 Apr 2022, 10:04


የርስት ፖለቲካ .. ምዕራብ ትግራይ
By Finfinne Times


የአማራ ተስፋፊው ልሂቅ ከኤርትራ ጋር ሆኖ ምዕራብ ትግራይ ላይ ለመዋጋት መወሰናቸውን የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትር አቶ የማነ ገ/መስቀል በዚህ ሳምንት አስታውቀዋል። ምክንያት የተደረገው ደግሞ ህወሃት ከሱዳን ጋር ተዋስና አቅሟን እንድታጠናክር አናደርግም የሚል ይዘት አለው።

ኢሳያስ አፈወርቂ ከ40 አመታት በላይ ቋንቋውን ባለመናገር የተጠየፉትን ፊውዳል በዝባዥ ነው ብለው .. ህዝብን በጅምላ እንደ ጠላት የፈረጁትን የአማራ ህዝብን ከውስጣቸው ካለው የዘመናት ቂም በተጨማሪ በቀጣይ ጥይት ማብረጃ ለማድረግና መስዕዋትነት ለማስከፈል ወስነዋል።

የምዕራብ ትግራይ ነገር አማራ መሬቱን በመያዝ ርስቴ ነው ብሎ እንደሚፎክረው አይደለም። የኤርትራን እጣፈንታ ፣ የወደፊቷን የትግራይና የኢትዮጵያ ፖለቲካ መወሰኛ ብሎም የአሜሪካን አዲሱ የምስራቅ አፍሪካ ቀጠናዊ ስሪት ማስተካከያ የመጨረሻው ፕሮጀክት ነው።

ሀገራዊ ፣ ቀጠናዊ ፣ አለምአቀፋዊ አንድምታዎች አሉት። በዚህ ሰአት ምዕራብ ትግራይ ልክ እንደ ጋዘ ሰርጥ እጅግ ስትራቴጂካዊ ቦታ ናት።

በእርግጥ አማራ የምዕራብ ትግራይ ጉዳዩን ከርስት አንፃር ብቻ ነው እየተመለከተው ያለው። ዙሪያውን በማየት የሀይል አሰላለፍ ለውጥ ፣ ቀጠናዊ ዲፕሎማሲያዊ ፣ ወታደራዊ ሆነ አጠቃላይ ጂኦፖለቲካዊ ጉዳዮችን መመልከት አልፈለጉም። የመሬት ጥያቄ ብቻ ነው የነ ባሻዬ ፉከራ ...

ኢሳያስ አፈወርቂ ነገሩ ገብቷቸው .. የምዕራብ ትግራይ ቀጣይ እጣፈንታ ወደ እሳቸው እንደሚነፍስ ከራማቸው ነግሯቸው .. ቢያንስ ቀውሱን ለማዘግየትና ባለበት ለማስቀረት የተለያዩ እቅዶችን መተግበር ከጀመሩ ቆይተዋል።

ፌደራሉ መንግስት እንደካዳቸው ሲገባቸው የአማራ ህዝብን እንደ ታክቲካል አጋር በመያዝ የመጣውን ማዕበል ለመከላከል ቆረጠዋል። በእርግጥ የፌደራሉ መንግስት ዝምታ ... ወዲ አፎም በደንብ ገብቷቸዋል።

ወዲ አፎም ዝም ቢሉና እጃቸውን ቢሰበስቡም .. ቀውሱ አስመራ እንደሚመጣ አያጡትም። ስለዚህ በዝምታ ከመበላት ተንቀሳቅሶና የሆነ ነገር ሞክሮ መጥፋትን አልመዋል።

የአማራ ወጣትን በመማገድ የስልጣን ጊዜያቸውን ለማስረዘም አሰፍስፈዋል። እነ ባሻዬ መሬት መሬት እያዩ ለመበላት እየተዘጋጁ ነው። በእነሱ ማገዶ ቀጠናዊ ሰደድ እሳት ሊነሳ እንደሆነ አልገባቸውም።

በእርግጥም ምዕራብ ትግራይ ላይ ከኤርትራ ጋር አንድ ላይ ሆኜ እዋጋለሁ የሚል የአማራ ወጣት ማገዶ ሆኖ ለአዲሲቷ ምስራቅ አፍሪካ መሰረት ይሆናል። ፖለቲካው ከመሬቱ በላይ ነው !!

Finfinne Times
Please wait, video is loading...


Post Reply