Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 11594
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

ደበበ ሰይፉ 'የአክሱም ጫፍ አቁማዳ' በዚህ ጊዜ ቢጽፈው እንዴት ይጨርሰው ነበር?

Post by sarcasm » 09 Apr 2022, 08:35



የአክሱም ጫፍ አቁማዳ
/ደበበ ሰይፉ/



ትግራይ ላከ ወሎ ጋ አበድሮኝ ብሎ አንድ ቁና ጤፍ
ወሎም አፈረና የለኝም ማለቱን ባህሉን መዝለፍ
ቆሌውን መንቀፍ
ላከ ወደሸዋ ምናልባት ቢሰጠው ለሰው እሚተርፍ።
ሸዋም አፈረና የለኝም ማለቱን ወደ ሐረር ዞረ
ሐረርም መልሶ ባሌን አተኮረ
ባሌም ወደአርሲ አርሲ ሲዳሞን
ሲዳሞም ተክዞ፣ ግን የለኝም ብልስ ማን ያምነኛል ብሎ
ወደ ጋሞ ላከ አቁማዳ ጠቅሎ።
ጋሞን ብርድ መታው ሐዘን ገባውና
የራሱን ምንዳቤ የግል ስቅየቱን ችሎት በጥሞና
በጋቢ ጀቡኖ የልቡን ጠባሳ ሲኖር እንደ ደህና
ዛሬ የወንድሙን የእርዳኝ አቤቱታ መስማት አልቻለና።
አውጥቶና አውርዶ ላከ ወደ ከፋ እጅግ አስተዛዝኖ
ከሀፍረት ያድነኛል ከረሃብ ያወጣኛል ሲል በአያሌው አምኖ።
ከፋ እንደደረሰው በድንገት አቁማዳው በነብሱ ዋይታ
ሐራራው ተሰማው የሥጋው ድንፋታ
ብልሀት አዛጋ ቆይቶ ቆይቶ የተስፋ ጠል ቀዳ
ሊልክ ከኢሉባቦር አበድረኝ ብሎ እህል በአቁማዳ።
ጭምት ኢሉባቦር ይኖር የነበረ የቤቱን ጉድ ጓዳ በሞኛሞኝ
ገላው ቆዳው ውስጥ ወሽቆ
ጠየቀ ወለጋን ሐፍረቱን ደብቆ ኩራቱን ዘቅዝቆ
ኬት አመጣ ብሎ ወደኔ ላከብኝ እያለ ወለጋ እጅጉን ተደሞ
ሄደ ወደ ጎጃም ዛሬን ሁነኝ ብሎ ሊማፀነው ቆሞ።
ጎጃምም ተሰምቶት ሰቀቀን ሐዘኑ ደረት እየመታ፣ ቅኔ እያወረደ፣
እንባ እያፈሰሰ
ወግና ኩራቱን በየቦዳው መሀል እየነሰነሰ
ዐባይን ተሻግሮ ከጎንደር ደረሰ።
ፋሲል ላይ ተነጥፎ ጎንደርም ሐዘን ላይ ነበረ ተቀምጦ
ተድላ ልጁ ሞቶ ገናን ክንዱ ታጥፎ በዘመን ተድጦ
ጎጃም መጣ ሲሉት የእዝን የተመኘን ልቡን በታዘበ
የኩራት ካባውን ሊጥል ባንጓበበ
የወንድሙ መምጣት እቅጩ መንስዔ መሆኑን
ሲረዳ ረሀብ አበሳ
ጥንትም አልሆነኝም ከእንግዲህ ይበቃኛል ለይሉኝታ አልሳሳ
ብሎ ከኤርትራ እህል ለመበደር በርትቶ ተነሳ።
የዘመዱ እጦት ነበርና እጦቱ በዝቶ ሰቀቀኑ
ኤርትራ ታመመ ደም ጎረፈ ከዓይኑ፡፡
ወደ ትግራይ ላከ መላ ባገኝ ብሎ ከአደራ ደብዳቤ
(እባክህ ላክልኝ አንድ አቁማዳ እህል ልሞት ነው ተርቤ።)
ትግራይ አስተውሎ አቁማዳው የራሱ መሆኑን ለይቶ
ረሀብ ዕጣቸው የሁል ወንድሞቹ መሆኑን አካቶ
ሐዘኑ አነቀው፤ ትንፋሹ መረረው፣ ትካዝ ሆዱ
ገብቶ።
“እኔና ወንድሞቼ” አለ በለዘብታ
ለራሱ እንዲያወራ የራሱን ስሞታ፤
“እኔና ወንድሞቼ ሁላችን . . . ሁላችን
ከባዶ አቁማዳ ነው እሚዛቅ ፍቅራችን
ይህ ነው አንድነታችን
ይህ ነው ባህላችን
ዘመን ማዛጋቱ በያንደበታችን።
ለኋላ ትውልዶች ተረት እንዳይመስል ይህ ብካይ
እሮሮ
ይህ ጠፍ ስብእና ይህ ስቁይ አእምሮ
እንዳኖረው ያሻኛል ይህንን አቁማዳ ከፍ ካለ ስፍራ
መጥቆ እንደባንዲራ
ምንም ባዶ ቢሆን በውስጡ አይጠፋና የታሪክ
አዝመራ።”
ይህንን ተናግሮ ከአክሱም ሐውልት ዘንድ
ትግራይ ተጠግቶ
አንዴ እየፀለየ አንዴ እየዘመረ ያለመጠን ተግቶ
ጫፉ ላይ ሰቀለው ያን አቁማዳ አውጥቶ።
1967
ደበበ ሰይፉ (ለራስ የተጻፈ ደብዳቤ/ የብርሃን ፍቅር ቅጽ 2) መጽሐፍ 1992ዓ.ም የታተመ


The government used starvation as a weapon to force the people surrender, and then enslaved them. This shall NEVER happen to the proud people of Tigray. Never!

The Ethiopian government's allegation that "TPLF is blocking humanitarian aid" is an utter sick joke. How on earth can TPLF, which is in charge of the state, block aid not to enter in to Tigray? It is anti logic! By starving the people of Tigray, the Ethio government seems to follow the war tactics applied to the people of Biafra region, in Nigeria, 50 years ago. The government used starvation as a weapon to force the people surrender, and then enslaved them. This shall NEVER happen to the proud people of Tigray. Never!

Please wait, video is loading...


Abere
Senior Member
Posts: 15496
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: ደበበ ሰይፉ 'የአክሱም ጫፍ አቁማዳ' በዚህ ጊዜ ቢጽፈው እንዴት ይጨርሰው ነበር?

Post by Abere » 09 Apr 2022, 10:11

በ1967 ባዶ አቅማዳ ትግራይ አክሱም ሃውልት ላይ እንድሰቀል ያደረገው ወያኔ ፤ አሁንም ባዶ አቅማዳ ወይም ጆንያ እንድሰቀል ያደረገው ያው ልማደኛ ወያኔ ነው።

ትግራይ አቅማዳውን አውርዶ ለምን ወያኔን አይሰቅልም? ባዶ አቅማዳ እና ጆንያ በየአገሩ ከሚዞር። የማይጠቅም ሙሾ ከማውረድ እጅጌውን ሰብሶ ወያኔን ማውረድ አይሻልም ወይ? የሞተ ድርጅት ይዞ መግማማት ምን ይረዳል።

Naga Tuma
Member+
Posts: 7442
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: ደበበ ሰይፉ 'የአክሱም ጫፍ አቁማዳ' በዚህ ጊዜ ቢጽፈው እንዴት ይጨርሰው ነበር?

Post by Naga Tuma » 14 Apr 2022, 11:09

ይህን ጥበብ ከየት ኣምጥተህ ነዉ ሳላዉቀዉ ዐይኖቼን የምታረጥበዉ። በዚህ መድረክ ስምህ መለጠፉን ቀና ብዬ ሳይ ጥበቡ እና የመድረክ ስምህ የማይጣጣሙ መስለዉ እየታዩኝ።

ከኣሁን በፊት የጥላሁን ገሰሰን ዋይ ዋይ ሲሉ የሚለዉን ዘፈን ሰምቼ ምነዉ ወደ ትግርኛ ተተርጉሞ በተንቆረቆረ ብያለሁ።

ኣሁን ደግሞ ይህን የደበበ እሸቱን ጥበብ ለመጀመርያ ጊዜ ሳነብ ምነዉ ወደ ብዙ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ተተርጉሞ በተነበበ ኣልኩኝ፣ ቦረናን፣ ሶማሌን፣ እና ጋምቤላን እንዲጨምር ማሻሻያ ተደርጎ። ጥበቡ የተጻፈዉ ቦረና ሲዳሞ ክፍለሃገር፣ የኢትዮጵያ ሶማሌ ሀረርጌ ክፍለሃገር፣ ጋምቤላ ከፋ ክፍለሃገር ዉስጥ የነበሩ ጊዜ መሆኑ ይገባኛል።

ይህ የደበበ እሸቱ የጥበብ ስራ ሁለት የኢትዮጵያ መሠረታዊ እሴቶች ኣሉት። አንድ ቭክትም ሜንታሊቲ (victim mentality) ኣይንጸባረቅበትም። ቭክትም ሜንታሊቲ የምያሳድግ ይሁን የምያሳንስ ላይቶ የምያዉቅ ካለ መጥቶ ቢገልጽልኝ።

ሁላተኛ ጥበቡን ኣንብቤ ስጨርስ ነብዩ መሃመድ ስለኢትዮጵያ ዘ ላንድ ዌርኢን ኖ ዋን ኢዝ ሮንግድ (the land wherein no one is wronged) ያለዉ መጥቶ ፊቴ ተደቀነ። ካዛም አክሱም ሃዉልት ማማ ላይ ብቻ ሳይሆን ነጃሽ መስጊድ ዉስጥ ነብዩ መሃመድ ያለዉን ለማስታወስ በተለጠፈ ኣልኩኝ። የተመድ ህንፃስ ስለዚህ ጽሁፍ ምን ይላል ብዬም እራሴን እጠይቃለሁ።

Post Reply