Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 11594
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

‹‹በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሊብራላይዜሽን ማድረግ ራስን እንደማጥፋት ነው›› ዓለማየሁ ገዳ (ፕሮፌሰር) የምጣኔ ሀብት ምሁር (Reporter)

Post by sarcasm » 14 Apr 2022, 07:37

‹‹በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሊብራላይዜሽን ማድረግ ራስን እንደማጥፋት ነው›› ዓለማየሁ ገዳ (ፕሮፌሰር) የምጣኔ ሀብት ምሁር
10 April 2022
አማኑኤል ይልቃል
ዓለማየሁ ገዳ (ፕሮፌሰር) የኢትዮጵያን የምጣኔ ሀብት ዘርፍ ለብዙ ዓመታት ከተከታተሉና ሒደቱን ጠንቅቀው የሚያውቁ ጉምቱ የምጣኔ ሀብት ባለሙያ ናቸው፡፡ ዓለማየሁ (ፕሮፌሰር) እስካሁንም ድረስ የምርምር ሥራ ከሚሠሩበት አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ባሻገር በተለያዩ የዓለም አቀፍ ተቋማት ውስጥ ጥናቶችን በመሥራትና በተለያዩ ሥራዎች ላይ ተሳትፈዋል፡፡ አሁንም ለዓለም አቀፍ ተቋማት ጥናቶችን በመሥራት ላይ ናቸው፡፡ ሁለተኛ ቤቴ በሚሏት ጎረቤት አገር ኬንያን ጨምሮ በተለያዩ የአፍሪካ አገሮች ውስጥ በተለያዩ ሥራዎች ላይ ተሰማርተው አገልግለዋል፡፡ ከጉምቱው የምጣኔ ሀብት ባለሙያ ዓለማየሁ ገዳ (ፕሮፌሰር) አጭር ቆይታ ያደረገው አማኑኤል ይልቃል ስለሰሞነኛው የኑሮ ውድነት ትኩሳትና ተያያዥ ጉዳዮች አነጋግሯቸዋል፡፡

ሪፖርተር፡- አሁን ላይ የኢትዮጵያን ሕዝብ እያማረሩ ካሉ ችግሮች ውስጥ ቀዳሚውን ድርሻ የያዘው የኑሮ ውድነት ነው፡፡ ገዥው ፓርቲ በቅርቡ ባካሄደው የሕዝባዊ ውይይት ሕዝቡ በኑሮ መወደድ ምን ያህል እንደተማረረ ታይቷል፡፡ የኑሮ ውድነቱን እዚህ ደረጃ ያደረሰው ምንድነው ይላሉ?

ዓለማየሁ (ፕሮፌሰር)፡- የዋጋ ግሽበቱን ያመጡት ችግሮች አራት ናቸው፡፡ አንደኛ የእርሻ ምርታማነት ከሕዝብ ቁጥሩ አብሮ አልሄደም፡፡ ሁለተኛ በኃይለ ሥላሴ ጊዜ የነበረው ሕዝብ ብዛት በአራት እጥፍ ጨምሯል፡፡ በሰብል ያለው ምርታማነት ግን አሁንም ዝቅተኛ ነው፡፡ ለምሳሌ ጤፍን ብንወስድ በሔክታር 22 ወይም 23 ኩንታል ነው የምናመርተው፡፡ ይኼ ግን በሳይንስ እስከ 60 ኩንታል መድረስ ይችላል፡፡ ስንዴን ብትመለከት እስከ 30 ገደማ መሰለኝ የሚያመርተው እሱም እስከ 60 ሊሄድ ይችላል፡፡ ሁሉም ምርታማነት ከግማሽ በታች ነው፡፡ በኃይለ ሥላሴ ጊዜ 30 ሚሊዮን ሕዝብ የነበረው አሁን ወደ 120 ሚሊዮን ሲደስር ያረስነው መሬት ግን ከዘጠኝ በመቶ ወደ 12 በመቶ ብቻ ነው ያደገው፡፡ ሦስት በመቶ ብቻ ማለት ነው የጨመርነው፡፡ ስለዚህ ላለፉት 30 እና 40 ዓመታት እርሻ ላይ ስላልሠራን አልተቻለም፡፡ ለዚህ ነው መዋቅራዊ ችግር ነው የምንለው፡፡

ሁለተኛው ምክንያት ይኼ መንግሥት ላለፉት ሁለትና ሦስት ዓመታትና ያለፈው ኢሕዴግም ብሩን አርክሰውታል፡፡ በየቦታው ስጮህ ነበረ፣ አታርክሱት እያልኩኝ፡፡ የዋጋ ንረት ይመጣል እያልን ይኼው መጣ፡፡ እነሱ ኤክስፖርቱን ይጨምርልናል ኢምፖርቱን ይቀንስልናል ለዚህ ነው የምናረገው ነው ያሉት ሳይሳካ የዋጋ ንረቱን እዚህ ደረሰ፡፡ ሁለተኛው የመንግሥት ስህተት ነው፡፡ ሦስተኛው ችግር ብር ማተም ነው፡፡ የበፊቱ ኢሕአዴግ በጣም ነበር ብር የሚያትመው፡፡ 2000 ዓ.ም. አካባቢ ኢትዮጵያ ውስጥ የነበረው ጠቅላላ ብር 67 ቢሊዮን ዶላር ነበረ፡፡ ጠቅላላ ኪሳችን ውስጥ ባንክ ያለው ተደምሮ፡፡ በአሥር ዓመታት ውስጥ 2012 ዓ.ም. አካባቢ 870 ቢሊዮን ዶላር ሆነ፡፡ 67 ሚሊዮን የነበረው በዓመት በአማካይ በ30 በመቶ አደገ፡፡ ዕድገት ተብሎ የተጠቀሰው ነገር በሙሉ በብድርና በብር ማተሙ የመጣ ነበር፡፡ ይኼንን በጊዜው ስጮህ ነበረ የሰማኝ የለም፡፡ አራተኛ ደረጃ ችግሩ ነጋዴው ነው፡፡ ነጋዴው ያልተገባና የሚዘገንን ትርፍ ያተርፋል፡፡ 100 እና 200 በመቶ ነው የሚያተርፉት፡፡ ሌላ አገር 20 በመቶ ካተረፍክ በጣም ቆንጆ ሥራ ነው፡፡ አሜሪካ አገር አሥር በመቶ ነው የምታተርፈው፡፡ 20 በመቶ ካተረፍክ በጣም ቆንጆ ቢዝነስ ነው፡፡ እስኪ ሽሮ ለመብላት ሂድ ጠቅላላ የሚፈጅባት 15 ብር ነው አይደል? 50 ብር ነው፡፡ አሁን 100 ገብትዋል እንዲያውም፡፡ ስለዚህ እኛ አገር ከትንሽ ነጋዴ እስከ ትልቅ ነጋዴ ድረስ 100 እና 200 በመቶ ካላተረፈ ያተረፈ አይመስለውም፡፡ ስለዚህ የዋጋ ንረቱን ለማቆም እነዚህ ችግሮች ላይ መሥራት ያስፈልጋል፡፡

ሪፖርተር፡- ችግሮቹ እነዚህ ከሆኑ፣ ለእነዚህ ችግሮች መንግሥት እየወሰደ ያለው ዕርምጃ ምን ይመስላል?

ዓለማየሁ (ፕሮፌሰር)፡- መንግሥት እየወሰደ ያለው ዕርምጃ ለምሳሌ የመጀመርያ ፖሊሲዬን ሰምቶኛል ማለት ነው፡፡ እርሻው ላይ እየሠሩ ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ኩታ ገጠም የሚሉትና ትንንሽ መስኖዎች የሚሉት ቆንጆ ነው፡፡ ችግር ያለብኝ እኔ ምንድነው? እሳት ማጥፋት ነው የተያዘው፡፡ ዕቅድ አውጥቶ ወጣቶችን በመስኖ ሥራ ላይ ማሰማራት፡፡ በዚያውም የወጣት ሥራ አጥነት ትቀርፋለህ፡፡ የወጣት ሥራ አጥነት እስከ 25 በመቶ ደርሷል፡፡ በጣም ትልቅ ነው፡፡ ብዙ ጊዜ ሦስት፣ አራትና አምስት ከበለጠ ሥጋት ነው፡፡ እኛ ጋር 25 በመቶ ደርሷል፡፡ ወጣቱ ደግሞ ሥራ ካጣ ወደ ፖለቲካዊ ብጥብጥ ነው የሚሄደው፡፡ ስለዚህ ወጣቱን ይኼ ትንንሽ መስኖዎች ላይ ማሰማራት ጥሩ ነው፡፡

በአጭር ጊዜ ውስጥ ምርታማነትን መጨመር አትችልም፡፡ አሁን ቅድም እንደተራገርኩት በጤፍ፣ በስንዴ፣ በገብስ የምንለውን ምርት በአንድ ጊዜ በሔክታር እጥፍ ማድረግ ይከብዳል፡፡ ማዳበሪያ ይፈልጋል፡፡ ኤክስቴንሽን ሥራ ይፈልጋል፡፡ ፀረ አረም ይፈልጋል፡፡ እነዚህ ደግሞ ዋጋቸው በዚህ ሰሞን ብቻ ሳይሆን ላለፉት አምስት ዓመታት አሥር እጥፍ ነው የጨመረው፣ ከባድ ነው፡፡

ስለዚህ ምንድነው በአጭር ጊዜ ማድረግ የምትችለው? ሁለቴ ማምረት ነው፡፡ በትንንሽ መስኖ ማለት ነው፡፡ ስለዚህ እዚያ ላይ ኢንቨስት አድርጎ በተለይ ወጣቶችን እንዲሠሩ ዘመናዊ ገበያ መሥራት ማለት ነው፡፡ አንዱ ይኼ ነው፡፡

ሁለተኛ የብር ምንዛሪ ተመንን ቋሚ አድርጉት ብዬ በየቦታው ተናግሬያለሁ፡፡

Continue reading https://www.ethiopianreporter.com/article/25196