Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Wedi
Member+
Posts: 8649
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

"ወደ ኦሮምያ ክልል የተሰማራ የሶማሌ ክልል ልዩ ሃይል የለም!" አቶ አብዲቃድር ረሺድ/የኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ

Post by Wedi » 11 Apr 2022, 17:36

👉የተጠለፈው ተሽከርካሪ እውነታ እና የመንግስት ምላሽ!

"ወደ ኦሮምያ ክልል የተሰማራ የሶማሌ ክልል ልዩ ሃይል የለም!"

አቶ አብዲቃድር ረሺድ/የኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ
*****
የሶማሌ ክልል የክልሉ ኃይል እራሱን የኦሮሞ ነጻነት ጦር ብሎ ከሚጠራው ቡድን ጋር ለመዋጋት በኦሮሚያ ክልል የተሰማራ ሃይል አለመኖሩን ገለፀ።

የሶማሌ ክልል መንግሥት ከፍተኛ ባለስልጣን የሆኑት አብዲቃድር ራሺድ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ሸኔ ብሎ ከሚጠራው ቡድን ጋር ለመዋጋት ወደ ኦሮሚያ ክልል የተሰማራ የሶማሌ ክልል ኃይል የለም ብለዋል።

ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ጦር ብሎ የሚጠራው ቡድን ቃል አቀባይ የሆኑት ኦዳ ተርቢ፤ በደቡባዊ የኦሮሚያ ክፍል ከፌደራሉ መንግሥት ጎን የሶማሌ ክልል ኃይል ተሰማርቶ እየተዋጋ ነው ብለው ነበር።

የሶማሌ ክልል መንግሥት ከፍተኛ ባለስልጣን የሆኑት አብዲቃድር ራሺድ ምንም እንኳ እስካሁን ድረስ የክልላቸው ጦር በኦሮሚያ ክልል ባይሰማራም እንዲሰማራ ጥያቄ ከቀረበለት ግን ወደ ክልሉ ሊገባ ይችላል ብለዋል።

[ መጋቢት 18 ቀን ከሀዋሳ መድሃኒት በመጫን ወደ ሊባን ዞን ፊልቱ ሆስፒታል ሲጓዝ የነበረ አንፑላንስ ነጌሌ ቦረና አከባቢ በኦነግ ሸኔ ተጠልፎ ከጫነው መድሃኒት ጋ መወሰዱ የሚታወስ ሲሆን ይህንኑ ተሽከርካሪ የሽብር ቡድኑ በውጊያ የማረኩት ነው ብሎ በማህበራዊ ድረገፅ የሀሰት መረጃ ሲያሰራጭ እንደነበር ይታወቃል።]

Please wait, video is loading...