እኔ ሆረስ አይናማው በሁለቱ የሆሩ አይኖች ነው የማየው ፤ ቀን በፀሃይ ብርሃን፣ ለሊት በጨረቃ ብርሃን! ከእኔ እይታ የሚያመልጥ የሆነም ያልሆነም ነገር የለም ።
በኦሮሞና በሲዳማ ክልሎች መሃል የመሬት ባለቤትነት የድምበር ግጭት ተነሳ ይባላል። ይህኮ ዜና መሆን የለበትም።
ኦሮሞ በሚመለከት ያልኩት ሁሉ እየሆነ ነው ። ኦሮሞ ከ33 ጎስዎች ጋር ይዋሰናል፣ ያም ማለት በዛሬ የኢትዮጵያ የጎሳ ክልል መሬት ስሪት መሰረት ከ33 ጎሳዎች ጋር የመሬት ጥያቄ አለበት ማለት ነው።
ይህን የሆረስ ማክሲም ወይም መሰረታዊ መርህ ልብ በሉ !
ማንኛው የጎሳ ግጭት ከቃላት እስከ መሳሪያ ዉጊያ የመሬት ግጭት፣ የመሬት ጦርነት ነው ።
የኦሮሞ እና የ33ቱ የመሬት ጦርነቶች ገና መጀመራቸው እንጂ ማብቂያቸው አይደለም፤ ማለትም የጎሳ ክልሎች እስካልፈረሱና አዲስ የመሬት ስሪት እስካልመጣ ድረስ።
ድሮ ሲዳማ የነበረው ዛሬ ምራብ አሩሲ የሚባለው የሻሸመኔ አካባቢ በሲዳማና ኦሮሞ ድምበር የጉጂ ሕዝብ አለ። ቢያንስ 13 ቀበሌዎች የመሬት የድምበር ግጭት አለባቸው ። ይህ ምንጊዜም የሚፈታ ጉዳይ አይደለም። ማለትም ኦሮሞ የጉጂን መሬት ለመዋጥ እስከ ፈለገና ሲዳማ ጉጂን ለመዋጥ እስከ ፈለገ ድረስ የሲዳምና ኦሮሞ ጦርነት አይቀሬ ነው።
ከዚያ ባላፈ ኦሮሞ ከታች ከሱማሌ አንስቶ ወሎ ትግሬ ጥግ ድረስ ከ33 ጎሳዎች ጋር የመሬት ጥያቄ አለበት ።
አዲሲቱ ሲዳማ ከወዲሁ ከኦሮሞም ከወላይታም ጋር የመሬት ጦርነት ጦርነት አለባት ።
ትግሬ ባለው የመሬት ጦርነት ከወዲሁ ባንድ አመት ተኩል 9 መቶ ሺ ሰው ሞተብኝ እያለች ነው ።
የአፋርና ሱማሌን ትተን በመላ ደቡብ ገና ዕልፍ የመሬት ጦርነቶች ይነሳሉ
የጎሳ ስርዓት ማለት የመሬት ጦርነት ዘመን ማለት ነው !
እኔ ሆረስ ነኝ ይህን ሺ ግዜ ተንብዬዋለሁ! ሺ ግዜ ተደጋግሞ እየተገልጸ ነው !!