Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 11594
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

ክለቦች እና ክልሎች ወደ ባሕር ዳር መሄድ አንፈልግም | አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ውድድሩ ወደ ሐዋሳ ቀየረው | "ሰከን እንበል፤ ከሌላው ሕዝብ እየተነጠልን ነን።" የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር

Post by sarcasm » 28 Mar 2022, 20:54

የአማራ ክልል ለቅድመ ዝግጅት ላወጣው ወጪ ካሳ እንደሚከፍል ፌዴሬሽኑ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣መጋቢት 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ለ51ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ቅድመ ዝግጅት የአማራ ክልል ላወጣው ወጪ ካሳ እንደሚከፍል የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታወቋል፡፡

ፌዴሬሽኑ በደብዳቤ እንዳስታወቀው÷ 51ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በባህርዳር ከተማ እንዲካሄድ ውሳኔ በማሳለፍ እንቅስቃሴ ሲያደርግ መቆየቱን አስታውቋል፡፡

ነገር ግን የካቲት 21 ቀን 2014ዓ.ም የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ባደረገው ስበሰባ አንዳንድ ክለቦች እና ክልሎች ያቀረቡትን የበጀት ወጪ መጠንን ቁሳቁስ ለማጓጓዝ የሚፈጀውን ርቀት ታሳቢ በማድረግ ውድድሩ በሐዋሳ እንዲካሄድ መወሰኑ ተመላክቷል፡፡


ይሁን እንጂ ጠቅላላ ጉባኤው ቀደም ሲል የወሰነውን ውሳኔ ባለማክበሩ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንን እና የአማራ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮን ይቅርታ ጠይቋል፡፡

በመሆኑም ክልሉ በቅድመ ዝግጅት ምዕራፍ ላይ ያወጣቸው ወጪዎች በተገቢው መንገድ ተጣርተው በፌዴሬሽኑ የሚሸፈኑ መሆኑን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በፃፈው ደብዳቤ አስታውቋል፡፡

https://www.facebook.com/fanabroadcasti ... 2929783739


ሰከን እንበል፤ እየተነጠልን ነን። በጣም ጫፍ የረገጠ አስተሳሰብ ነው ይሄ ክልል ስሜቱንም እየጎዳ፤ ከሌላው ሕዝብ ጋርም እየነጠለው ያለው - የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ