ተበልቶ የማይጠገበው የትኩል ባልትና !!
የከብት ስጋ ምግብ በብዙ መንገድ ቢዘጋጅም ሶስቱ ዋና ዋና አይነቶች (1) ብርንዶ (ቀይ ክትፎ)፣ (2) ስልስ (ጠለቅ ያለ ጥብስ ክትፎ) እና (3) ፍጹም የማይጠገበው ትኩል ናቸው ። ትኩል ተቀቅሎ እንደ ዱቄት የተከተፈ ስጋ በቅመምና ቅቤ የተዘጋጀ ነው ። በጣባ ቀርቦ በአንቀፎ (ቀንድ ማንኪያ) ይጎረሳል! እንደ እርጎ ጉሮሮ ውስጥ ይፈሳል! ትኩል ያልቃል እንጂ አይጠገብም ይባላል!! ቃሉ ትክል (ቅቅል) ከሚለው የመጣ ነው ።