Please wait, video is loading...
Re: ጋላና ጋሪ ፒያሳ አይገባም ብሎ ያለው ኤርትራዊ መሆን አለበት...Lencho Letta
Lencho Letea and Asmerom Legesse must have been discussing Eri-Oromo relations

Re: ጋላና ጋሪ ፒያሳ አይገባም ብሎ ያለው ኤርትራዊ መሆን አለበት...Lencho Letta
C beyond wrote: ↑06 Mar 2022, 20:32[facebook]https://www.facebook.com/10004810883214 ... 6538483538[/facebook]
ካድሬ ገመቹ መገርሳ እና ዶክተር ገመቹ መገርሳ
ካድሬ ገመቹ መገርሳ፥
አርሲ ዉስጥ በጦርነት ዉስጥ እናቶቻችን ክፉኛ ተጎዱ።
ጨለንቆ ላይ በጦርነት ዉስጥ ህዝባችን ተጎዱ።
ከጋሪ ጋር ፕያሳ ኣትገቡም ተባልን።
ዶክተር ገመቹ መገርሳ፥
እንደምታዉቁት እኔ መመራመር ይችላል ተብሎ ከዩኒቨርዚቲ የተመራማሪነት ዕዉቅና የተሰጠኝ ነኝ። ስለዚህ መርምሮ ተመራምሮ መዝኖ እዉነትን መናገር ይጠበቅብኛል።
ልብ በሉ፣ ተዓምር እና ምርምር ለየብቻ ናቸዉ። ብዙ ሰዎች በሰባት ቀን ተዓምር ያምናሉ። የሰዉ ዘር ረጅም ታሪክ ከአፈር ዉስጥ ወርቅ ፈልጎ እንደማበጠር ሊታይ ይችል ይሆናል።
በረጅም ጊዜ ታሪኩ የሰዉ ዘር ቤት መስራት ፈጥሯል። ቀላል ፈጠራ ኣልነበረም። ቤተሰብን ያዋቀረ ፈጠራ ነበር።
ቀጥሎም ባለበት አከባቢ ድንበር ከልሎ ሃገር እና ብሄር መገንባትንም ፈጥሯል። ያም ቀላል ፈጠራ ኣልነበራም። ዜግነትን ኣዋቅሮ ከሩቅ፣ ከባህር፣ እና ዉቅያኖስ ማዶዎች የሚመጡትን በላንጣዎች ተባብሮ ለመመከት ያስቻለ ፈጠራ ነበር።
ቤት ሲሰራም ሆነ ሃገር ሲገነባ መድከም ነበር። መቁሰል ነበር። ማቁሰልም ነበር። እንኳን ቤት መስራት እና ሃገር መገንባት ካሊፎርንያ ሄጄ ያየሁት ጎልደን ጌት ድልድይ ሲሰራ የሰዉ ህይወት ኣልፏል። ድልድዩ ከተሰራ በሁዋላ የጎብኚዎች መነሃርያ ሆኗል። ድልድዩን ለመስራት የሰዉ ህይወት ኣልፏል ብሎ መጎብኘቱን የሚጸየፍ ኣልሰማሁም።
በጨለንቆ ጦርነት የሰዎች ህይወት ያለፈ ቢሆንም ከጦርነቱ በሁዋላ በሁለቱም ወገኖች የተፈረመዉ ታሪካዊ ስምምነት የላቀ ነዉ ማለት ይቻላል። ከዛ ጦርነት በሁዋላ የመጣዉ የአደዋ ክስተት ከጨለንቆ ጦርነት እና ከዛ በሁዋላ ከተፈረመዉ ስምምነት የላቀ ነዉ ማለት ኣይቻልም? የሚቻል ይመስለኛል።
እስቲ ኣስቡት! እንደዛ አይነት ዝግጅት፣ ስምምነት፣ እና የአድዋ ክስተት ሙሉ በሙሉ ባይሆንም በድል ባይጠናቀቅ ኖሮ እንደ እኔ እና እንደ እኛ ኣይነቱ ምን ይገጥመዉ ነበር? በሃገሩ ወይም ባህር ኣቋርጦ ጥጥ ለቃሚ መሆን፣ እግር መቆረጥ? ይህም እኮ ሰፊ ታሪክ ኣለዉ።
መመራመር መልካም ነዉ። መመራመር ነዉ እኮ ከአድዋ ድል በሁዋላ እሩቅ ሃገር በረራን የፈጠረዉ። የኛዉ ሎሬት እንዳስተዋለዉ ተምዘግዝጎ እሩቁን ሃገር ቅርብ ያደረገዉ። መመራመርማ ከተነሳ ዛሬ እኮ ቤት ወይም ቢሮ ሆኖ ማምዘግዘግ ይቻላል ይባላል።
የሰዉ ኣእምሮ እንደ ምንጭ ነዉ። በቀን ስንት ሀሳብ ስያመነጭ ይዉላል። ህልምም ያሳልማል። አንድ ሰዉ ህይወቱን ሙሉ ምንጭ መሳይ ኣእምሮን ተሸክሞ እየኖረ ኣንድ ቀን ከአፉ ባፈተለከ ሀሳብ ከመዘነዉ አፈር ዉስጥ ያለን ወርቅ አፈር ነዉ ብሎ መወርወር ይሆናል። ኣያችሁ ኣሁን እንኳን እያወረሁ ስሳሳት። አፈርም እኮ የማይወረወር ስብል ኣብቃይ ወርቅ ነዉ።
መመዘን ወርቁን ከአፈሩ ለይቶ በየኣይነቱ ለመድመቅያ ወይም ለማብቀያ መጠቀም ያስችላል። ከስህተት ምክክር እና መከባባር ይበቅላሉ። መርምሮ ተመራምሮ መማማር እና ተባብሮ ማደግ፣ በላንጣንም ለመመከት።
ፕያሳ መግባትን ኣንዱ ከጋሪ ጋር ብያመሳስልብንም ጎጃም ደግሞ ደሙ የሌለበት ደበናንሳ ነዉ ተብሏል። ሲገላምጡን ገላምጠናል እኮ። ለምን ሲሉን ደስ ስላልከኝ ነዉ ብላን ኣሸሽተናል እኮ። ቤተመንግስትን ኣስተዳድረናል እኮ። ያልተዘገበ ሃብት ኣፍርተናል እኮ። ክፍለሃገራትን ኣስተዳድረናል እኮ።
ከተማ አከባቢ የቋንቋ ጫናን ኣስተዉለናል። በገጠር የሚኖረዉ ሰፊዉ ማህበረስብ የተለያያ ቋንቋዎች ምንጮች ሆኖ። በሰዉ ዘር ረጅም ታሪክ ዉስጥ የቋንቋ እና ሃይማኖት ጫናዎች ኣንድ ሃገር ብቻ የታየ ኣይዴለም። የመመራመር እዉቅና ባገኘሁበት እንግሊዝ ሃገር ከእንግሊዘኛ ዉጪ ሲናገር የተሰማ ይቀጣ እንደነበር ናሽናል ጆኦግራፊክ የተባለ መጽሔት ዘግቧል። ያ ኣይብስም?
አርሲ እናቶቻችን በጦርነት ዉስጥ ክፉኛ ተጎዱ ቢባልም ቄልምን የጆቴ ወርቅ ብለዋል። ቄለምን በደንብ ኣዉቀዋለሁ። ስለ አርሲ እዉነት ነዉ ብዬ ስለ ቄለም ዝም ካልኩኝ የምያወራዉን የማያመዛዝን ተመራማሪ ተብዬ ልወቀስ እችላለሁ። ስለዚህ ስለሁሉም ቦታ እዉነትን መናገር ይጠበቅብኛል።
ጆቴ ተባባሪ ደጃዝማች ነበሩ። በአከባቢዉ የአኙዋክ ማህበረስብ በብዛት ኣሉ። እነሱም ከተባበሪዉ ደጃዝማች ስሞታ ካላቸዉ ማዳመጥ ኣስፈላጊ ነዉ። መመራመር፣ መማማር፣ መከባበር፣ እና መተባበር አድካሚ ነዉ። ፕያሳ ዉስጥ የተነጠረ ወርቅ ኣይቶ መዘባረቅ ቄለም ወንዝ ዳር ያለዉን ወርቅ ከአፈሩ ዉስጥ ኣንጥሮ ፕያሳ ማድረስ ምን ያህል ኣድካሚ መሆኑን መሳት ነዉ።
ለዜጎቹ ሁሉ የሚመች ሃገር መገንባት ከመዘባረቅ በጣም የራቀ ነዉ። ሰዉን መመዘን በዘባረቀዉ ሳይሆን ኣስቦ ኣሰላስሎ በጣቶቹ በፈረመዉ ሰነድ ነዉ። እሱም ቢሆን የዉጫሌ ስህተት ወይም ማሳሳት ለአድዋ ክስተት ኣብቅቷል።
እንደ ተመራማሪ መዝኜ የምናገርዉ ይህ ነዉ። የሳትኩኝ ካለ ኣርሙኝ። የተሻለ ምርምር ካለ የበለጠ ተምሬ የበለጠ ለመመራመር ዝግጁ ነኝ።
Re: ጋላና ጋሪ ፒያሳ አይገባም ብሎ ያለው ኤርትራዊ መሆን አለበት...Lencho Letta
መመራመር ከኣንድ ጥያቄ ወደሌላ ጥያቄ ይወስዳል።
ደጃዝማች ጆቴ ቱሉ የኣጼ ምኒልክ ቤተመንግስት ቤተኛ የነበሩ ከሆነ፣ ዶክተር ሰናይ ልኬ የኢትዮጵያ ቤተኛ የነበረ ከሆነ፣ ኦቦ ሌንጮ ለታን ኢትዮጵያዊ ለመሆን እንደራደራለን እስከማለት ምን ኣደረሰዉ? ይህን ማብራራት ይቻላል?
ደጃዝማች ጆቴ ቱሉ የኣጼ ምኒልክ ቤተመንግስት ቤተኛ የነበሩ ከሆነ፣ ዶክተር ሰናይ ልኬ የኢትዮጵያ ቤተኛ የነበረ ከሆነ፣ ኦቦ ሌንጮ ለታን ኢትዮጵያዊ ለመሆን እንደራደራለን እስከማለት ምን ኣደረሰዉ? ይህን ማብራራት ይቻላል?
Re: ጋላና ጋሪ ፒያሳ አይገባም ብሎ ያለው ኤርትራዊ መሆን አለበት...Lencho Letta
እውነት ለመናገር በንጉሳኑ ዘመናት የቤተ-መንግስት እና የአስተዳደር ሰዎች እንደዚህ ብለው አይናገሩም። ተራው ህዝብ እርስ በእርሱ ሲተራረብ አንዳንዶች ለብሽሽቅ ወይም ለፌዝ ሊሉ ይችላሉ። የዛሬው ዘመን የኦነግ ብልጽግና ባለስልጣንት ግን ከቤተ-መንግስት ቁጭ ብለው በአዋጅ አከርካሪታቸውን ሰበረነዋል - ወዘተ ወዘተ እያሉ መንግስት ሳይሆኑ ተራ ሰዎች ሁነዋል።
ነገስታት ህዝብ ከህዝብ ያጋምዱ፥ያዋድዱ ነበር እንጅ አያጣሉም። ለምሳሌ ዐጼ ሃይለ ስላሴ እርስዎ ጋላ ነዎት ወይ ተብለው ሲጠየቁ መልሳቸው የጋላ ደም የሌለበት ኢትዮጵያዊ ካለ እርሱ ሰው ሳይሆን ቡዳ ነው ብለዋል። እምየ ምኒልክም እንድሁ የጅማው የባርያ ነጋደ ቱጃር አባጅፋር የጅማ ኦሮሞዎች፥ ጃንጀሮዎችን፤ኩሉዎችን ለዐረቦች በባርነት እያሸጠ ዘር ሲያጠፋ ምኒልክ ሰምተው ከባድ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል እንድህ በማለት < በአርዕያ ስለሴ የተፈጠረ ሰውን ገባያ ላይ አውጥቶ መሸጥ ወንጀል ነው። ይህን ስራ በአስቸኳይ አቁም ይህን ካለደረግህ አልምርህም > በማለት።
በአስተሳሰብ ያነሰው ይህ ትውልድ እንጅ ያ ትውልድ አይደለም። እንደ እነ ገመቹ መገርሳ ( በግድ ከእንግሊዝ አገር በትምህርቱ ሊወደቅ በነበበት ጊዜ የአገሩ ልጆች በሆኑት ብሁለት ጎጃሜዎች እርዳታ ያለፈው) ሁል ጊዜ ተራ ዱርየ አስተያየት በመስጠት ኦሮሞን ዝቅ እጅግ ዝቅ ያደረገ ሰው ነው። ለነገሩ ባለጌ እና ዋንጫ ከወደ አፉ ይሰፋል ይባላል።
ለመሆኑ ስንት ከየትኛውም ገጠር በቁምጣ ሱሪ አዲስ አበባ ፒያሳ ወይም መርካቶ ገብቶ ኪሱ ሳይፈተሽ እና የሸጠውን የበሬ ይሁን የበግ ወዘት ብር አስረክቦ ነው ለሌባ የሚመለሰው። ይህ ጉዳይ የገጠር እና የከተማ የባህል ቅራኔ እንጅ የጎሳ አይደለም። ገጠር የዋህ ሰው አማኝ ነው ከተሜ ጮሌ ቀምቶ የሚኖር ተደርጎ ይወሰዳል - በእውነትም ብዙዎች ቀምቶ አደሮች አሉ።ስለዚህ የቀልድ እና የብሽሽቅ ወሬዎች የፓለቲካ ባህርይ የላችውም።