Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
-
DefendTheTruth
- Senior Member
- Posts: 13262
- Joined: 08 Mar 2014, 16:32
Post
by DefendTheTruth » 16 Mar 2022, 15:52
ሆረስ፣ የጎሳ ከበርቴዎች የሉም ለማለት የምደፍር ያለ አይመስለኝም፣ ግን በዚያዉ ልክ ደግሞ ተግቶ የምለፉ ዜጎች የሉም ለማለት የሞራል ብቃት ና ድፍረት ያለን አይመስለኝም። ምስጋና የምገባቸዉን ማመስገን ግድ ይላል፣ በኔ ግምት።
There are visible results, which can't have been possible without diligent efforts of many hard-working citizens, at different positions. We should give credit where it is due.
If there was no such efforts by many, Ethiopia could have been in a shambles by now, taking many of the factors that have befallen this country in the last few years.
-
Horus
- Senior Member+
- Posts: 42903
- Joined: 19 Oct 2013, 19:34
Post
by Horus » 16 Mar 2022, 16:20
DTT
እኔ ብዙ ቦታ ደጋግሜ ጽፌአለሁ ። የጎሳ ከበርቴ የምላቸው በጎሳ ፖለቲካ የቢሮ ስልጣን ይዘው በመሬት ደላላነት፣ ጉቦ ሰብሳቢነት፣ ሌብነት፣ ደረሰኝ ፎርጅ በማድረግ የታክስ ከፋዩን ሕዝብ የሚመዘብሩት ይህን ሁሉ እየሰረቁ ለህዝቡ ንጹህ ዉሃና ሰላም የነሱትን እንጂ የተከበሩት አገር አልሚ፣ የንግድ፣ የርሻ፣ የኢንዱስትሪና የባንክ የፈጠራ ብሄራዊ ከበርቴዎችን አይደለም። እኔ እንደ ኮሶ የምጠላችደውና እንደ ሰው ዋጋ ማልሰጣቸው ዲፕሎማ በመግዛትና የኢህ ዴግኛ አሁን ደሞ የብልጽኛ አባል ሆነው ሕዝቡ እንደ ቅማል የሚመነዥጉትን ነው የጎሳ የቢሮ ከበርቴ የምላቸው! እጅግ ግልጽ የሆኑ ካታጎሪ ናቸው፣ ማምን አይስታቸውም። እነዚህ አንድ እቃ በጃቸው ሰርተው የማያውቁ፣ አንድ ነገር ገዝተው ሸጠው የማያውቁ፣ የማይፈጥሩ፣ የማያለሙ የቢሮ ስልጣን ይዘው በላቡና በእውቀቱ አገር የሚያለማውን ፈጣሪ አምራች ሕዝብን በታክስና ጉቡ የሚበዘብዙ ሳይሰሩ የሚከበርት ሌቦች የጎሳ የቢሮ ከበርቴዎን ነው ያልኩት! ዛሬ ባዲስ ቃል ባለ ሃብት የሚባሉት የአለምን ዘመናዊ ኢኮኖሚ የገነቡ የሳይንስ፣ የኢንዱስትሪ፣ የቴክኖሎጂ ኮሜርስና ፋይናንስ ፈልሳፊዎና ፋፍሪካ ገምቢዎችማ የስልጣኔ ጌቶች ናቸው! ግን በኢትዮጵያ እነዚህ የስልጣኔ ጀግኖችን ነው የጎሳ ከበርቴው በክልል አጥሮ የሚያሳቃያቸው ።
-
DefendTheTruth
- Senior Member
- Posts: 13262
- Joined: 08 Mar 2014, 16:32
Post
by DefendTheTruth » 16 Mar 2022, 16:36
ሆረስ፣
እንደሱ ከሆነ ታዲያ አታጠቃልላ፣ ይህን ስራ የሰሩትም እኮ ብልጽግናዎች ነቸዉ። የብልጽግ ና መመሪያን ነዉ የምተገብሩት ። ብልጽግ ና ነዉ እድሉን የሰጣቸዉ ና እዚያ ቦታ እንድቀመጡ ያደረጋቸዉ፣ ብልጽግ ና ተነሱ ካለ ነጌ ጠዋት ከቦታቸዉ ማንሳት ይችላል። በዛሬይቷ ኢትዮጵያ ዉስጥ የፓርቲ መርነት እንጂ የግለሰቦች መርነት የለም።
-
Horus
- Senior Member+
- Posts: 42903
- Joined: 19 Oct 2013, 19:34
Post
by Horus » 16 Mar 2022, 16:52
DefendTheTruth wrote: ↑16 Mar 2022, 16:36
ሆረስ፣
እንደሱ ከሆነ ታዲያ አታጠቃልላ፣ ይህን ስራ የሰሩትም እኮ ብልጽግናዎች ነቸዉ። የብልጽግ ና መመሪያን ነዉ የምተገብሩት ። ብልጽግ ና ነዉ እድሉን የሰጣቸዉ ና እዚያ ቦታ እንድቀመጡ ያደረጋቸዉ፣ ብልጽግ ና ተነሱ ካለ ነጌ ጠዋት ከቦታቸዉ ማንሳት ይችላል። በዛሬይቷ ኢትዮጵያ ዉስጥ የፓርቲ መርነት እንጂ የግለሰቦች መርነት የለም።
የተግባባን ስላልመሰልኝ አንድ ነገር ብዬ ላቁም። አንድ መንግስት ለማስተዳደር በክህሎትና ልምድ የተመረጡ ባለሙያ ኢኮኖሚስቶች አሉ። ቴክኖክራት ፕሮፌሻናል ይባላሉ ። እነሱ ያገር ማክሮ ኢኮኖሚ ይመራሉ ማለት አንድ አገር በ20 ሚሊዮን ካድሬ ተጠርንፎ እንደ ከብት ይነዳል፣ ይታዘዛል፣ ይመዘበራል ማለት አይደለም ። ኢኮኖሚን የሚያለሙ ሕዝቦች ናቸው የቢሮ ከበርቴ አይደለም ። እርሻን ተመልከት የእርሻ ሳይንቲስቶች የሚፈጥሩት የምርጥ ዘር ሳይንስና በእጁ የሚለፋው ወይም በገንዘቡ ሰራተኛ ቀጥሮ የሚያለማው የኢንዱስትሪ ጀግና አንተ ከምትላቸው ፓራሳይት ሌቦች ጋር ምን ያገናኘዋል! እንዲያውም አንድ ወረቀት ለመፈረም ነው እነዚያን አልሚ ፕሮዳክቲቨ የማህበረ ሰብ ክፍልን የሚያሰቃዩ ! ታዲያ ያ ካልሆነ ለምንድን ነው አቢይ አህመድ ምርር ብሎ ስለሌቦች ይህ ያክክል ያሳሰበው ? የቢሮ ከበርቴ የመዥገር መደብ እንጂ የልማት መደብ አይደለም።