B-No he will not
C-i don't know, because u never know what this galla-adwan abiy will do
ወልቃይት በአማራ ክልል ስር በብልፅግና ማዕከላዊ ኮሚቴ ተወከለች
ብልፅግና ፓርቲ ባደረገው ጉባኤ ወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን አስተዳዳሪ በአማራ ክልል ስር የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ሆነው ተመርጠዋል። የትግራይ ብልፅግና በእነ ዶ/ር አብርሃም በላይ ጨምሮ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ያስመረጠ ሲሆን ወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ የተወከለው በአማራ ብልፅግና ስር ነው። የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ አስተዳዳሪ አቶ አሸተ ደምለው የአማራ ብልፅግና አባል ሲሆኑ ትናንት በተደረገው የብልፅግና ጉባኤ ወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞንን ወክለው የብልፅግና የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ሆነዋል።
የየክልሎቹ ዞን አመራሮች የብልፅግና ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ሆነው የተመረጡ ሲሆን ለአብነት ያህልም የምዕራብ ጎጃም ዞን አስተዳዳሪ አቶ መልካሙ ተሾመ፣ የምዕራብ ጎንደር ዞን አስተዳደር አቶ ደሳለኝ ጣሰው፣ የደቡብ ወሎ ዞን አስተዳደሪ ዶ/ር አብዱ ሁሴንና ሌሎች የዞን አስተዳዳሪዎች የብልፅግና ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል እንደሆኑት አቶ አሸተ ደምለው የአማራ ክልል አንድ ዞን የሆነው ወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራን ወክለው በአማራ ክልል ኮታ የብልፅግና ማዕከላዊ ኮሚቴ ሆነው ተመርጠዋል።
