ያቦ:yaballo wrote: ↑20 Feb 2022, 22:151-ቀንደኛ የኢህአዴግ ደጋፊ በመሆን እያታለለ እስከ ሚኒስትር መሾም
2-የሰላም አርበኛ በመምሰል የሰላም ሽልማት መውሰድ
3- በድብቅ ከኢሳያስ ጋር እየተገናኘ የሰላም ስምምነት ያደረገ በማስመሰል እሱ ግን ከኢሳያስ ስለጦርነት በማሴር እና የጦርነት እቅድ በማውጣት ጦርነት እንዲጀመር ሁኔታ ማመቻቸት
4-ከሱዳን ጋር በሚስጢር በመነጋገር ከጎንደር መሬት እንድቆርሱ ማድረግ
እስካሁን በዚህ የተሳሳተ የዐቢይ ስሌት ከሁለቱም ሃገራት ማለትም ከሱዳን እና ከኤርትራ ጋር ያለው ግንኙነት ተበላሽቷል። በሃገር ውስጥም በክልሎች መካከል ያለው ግንኙነት ተበላሽቷል።
በቅርቡ የሚጋለጡ የዐቢይ ድብቅ ቃልኪዳኖች ደግሞ ከሁሉም የባሰ ዋጋ ያስከፍላሉ። በቅርቡ ከሚጋለጡት የዐቢይ ድብቅ ስምምነቶች መካከል:
1- ገንዘብ እና የጦር መሣሪያ ለማግኘት ሲባል ለተባበሩት አረብ ኤምሬቶች መሬት ለመስጠት እና እስልምናን የሚያስፋፉ ድርጅቶች ወደ ኢትዮጵያ በስፋት እንዲገቡ ለማድረግ የተገባው ቃል
2- የጦር ድሮኖች ለማግኘት ሲባል ቱርክ በሶማሌ ክልል ያሉ ማዕድናትን ለማልማት የተሰጣት ድብቅ ስምምነት
3- እስካሁን እስልምና በኢትዮጵያ ተጨቁኖ እንዳለና አብይ ይህን ለመቀየር እንደመጣ አድርጎ ራሱን በማቅረብ ከኢራን የጦር መሣሪያ ያገኘበት ስምምነት
አብይ እነዚህን ስምምነቶች ይፈጽማል ወይስ ይከዳቸዋል።
1) ባንተ ቤት መንጌ አስመስሎ እያታለለ ኮሎኔል ድረስ ቆየና ንጉሡን ገለበጠ፤ ምን ማለት ነው ይሄ?
2) በሰላም ማስመሰል ኖቤል አይገኝም፣ በጊዜው መስፈርቱን አሟልቷል።
3) ኢሳይያስ የወያኔን ባሕሪ ያውቃል፣ ጦርነት አይፈልግም፣ የብሔር ፌደሬሽን የሚያመጣውን ጣጣ ጠንቅቆ ስለሚያውቅ ከኤርትራ ጓሮ እንዲርቅ ይፈልጋል፣ ዶ/ር ዐብይ ከኢሱ መማር መሞከሩ ያባት ነው፣ ድብቅ የሆነው ለናንተ ብቻ ነው።
4) መሬት የሚቆረሰው ዳቦ አይደለም፣ ሱዳን ልዩ ሐይላችን ሁለት ሚሊዮን ሲደርስ ቀስ ብላ ሳትጠየቅ ላሽ ትላለች፤
ኤርትራ የችግር ጊዜ አጋር ሆና በመገኘቷ የኢትዮጵያኖችን አንጀት በልታለች፣ ፈጠነም ዘገየም ግንኙነታችን የውሸት አይደለም፤ ሱዳን የራሷ ችግር ላይ ታተኩር።
1) አረብ ኤምሬቶች ነጋዴዎች ናቸው፣ የሚቀጥለው ናፍጣ ውሃ ነው፣ ኤሌትርክ ለአውሮፓ እንሸጣለን፣ እዛ ላይ ገንዘባቸውን ለማስቀመጥ ቅድሚያ በወንድምነታቸው ይሰጣቸዋል፣ ግድቦች ላይ ገንዘብ ያፈሳሉ፤ በሐይማኖት ማስፈራራቱን ተወው፣ የተበላ እቁብ ነው።
2) ቱርክ በሶማሌ ክልል ያሉ ማዕድናትን ለማልማት የተሰጣት ድብቅ ስምምነት፧ ከተደረገ ደግ ነው፣ ያንሳቸዋል።
3) ኢራን ችግሯ የንግድ ልውውጥ ነው፤ ሐይማኖት ያንተ ማስፈራሪያ ነው።