Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Thomas H
Senior Member
Posts: 13070
Joined: 27 Jan 2007, 16:30
Location: Kaliti
Contact:

ሰበር ዜና : ፋኖ በኦሮሚያ ሕግ ለማስከበር ጦሬን እልካለሁ አለ

Post by Thomas H » 16 Feb 2022, 09:58

እነዚህ የአዕምሮ በሽተኞች ለይቶላቸዋል
Andinet Zeleke Bekele
1h ·
ከመንግስት መዋቅር ውጪ የተደራጀው የፋኖ ታጣቂ ሐይል አባይን (የአማራና ኦሮሚያ ክልል ድንበርን) ተሻግሬ በኦሮሚያ ክልል ህግ አስከብራለሁ አለ!!
*************************
#ፋኖ አባይን ተሻግሮ ኦሮሚያ ክልል በመግባት እርምጃ እወስዳለሁ ብሎ ዛሬ ማስጠንቀቁ ተነግሯል፡፡ በአዴፓ፤ በአብን እና በባልደራስ ፓርቲዎች እንደ ልጅ የሚታየው ፋኖ በዚህ ደረጃ ከክልሉ አልፎ በሌላው ክልል ህግ አስከብራለው ማለቱ የዛሬው አስገራሚ ክስተት ነው፡፡ ‘’ባለቤቷን የተማመነች በግ ላቷን ውጪ ታሳድራለች’’ ከሚለው ተረት ጋር የሚቀራረብ ድርጊት ነው፡፡
ፋኖ ማለት በአማራ ክልል ውስጥ የሚገኝ ከመንግስት መዋቅር ውጪ ያለ ታጣቂ ሐይል ነው፡፡ ይህ ሐይል በምን ህጋዊ መሰረት ኦሮሚያ ክልል ገብቶ እርምጃ ለመውሰድ እንደፈለገ እስካሁን ግልጽ አይደለም፡፡ ቢሆንም ፋኖ ከዚህ ቀደም በትግራይ እና በቤንሻንጉል እንዲሁም በወለጋ ከህግ ማዕቀፍ ውጪ ገብቶ ጥቃቶችንና ግድያዎችን መፈጸሙ አይዘነጋም፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ በህገወጥ መንገድ ተደራጅቶ እንደፈለገ የሚንቀሳቀስ ሐይል ፋኖ ሲሆን ፓርቲ ስለሌለው አላማው ግልጽ አይደለም፡፡
የሆኖ ሆኖ በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ለሚገኘው የትኛውም የሰላም እና የማህበራዊ ችግር ሓላፊነቱን መወጣት የሚችለው የኦሮሚያ ክልል ብቻ ነው፡፡ የኦሮሚያ ክልል የገጠመው ችግር ከአቅሙ በላይ ከሆነ በፌዴሬሽን ምክር ቤት በኩል የፌደራል ጦርን በጣልቃገብነት ሊያስገባ ይችላል፡፡ ይሁንና ፋኖ ህገወጥ አደረጃጀት ስለሆነ ትጥቁን የማይፈታ ከሆነ ሌሎች ክልሎችም ህገወጥ ታጣቂ ሀይሎችን በማደራጀት የፋኖን ጣልቃገብነት መከላከል አለባቸው፡፡
የኦሮሚያ ክልል እስከዛሬ ወደ ባህርዳር በሚወሰደው መንገድ ላይ በሁለቱ ክልሎች ድንበር አከባቢ በሚገጥም የትራንስፖርት መስተጓጎል ችግር ምንም ባላለበት ሁኔታ፤ የፋኖ ፉከራ ጉዳዩን ሌላ ትርጉም አሰጥቶታል፡፡ ስለሆነም የፋኖ በኦሮሚያ ክልል ላይ የሚደረግ ጣልቃገብነት ወይም ድንበር ተሸጋሪ ጥቃት ከወረራ ውጪ ሌላ ትርጉም ሊሰጠው አይችልም፡፡