Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Wedi
Member+
Posts: 8649
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

“አባገዳዎቹ የሚገደሉበት ሰዓት እየደረሰ እንደሆነ ተነገራቸው” በመጨረሻም የኦህዴድ ፖሊሶች ጨቢ አኖሌ ጫካ ከወሰዷቸው በኋላ በረድፍ እንዲተኙ ካደርጉ በኋላ ረሸኗቸው!!

Post by Wedi » 02 Feb 2022, 17:59

“አባገዳዎቹ የሚገደሉበት ሰዓት እየደረሰ እንደሆነ ተነገራቸው” በመጨረሻም የኦህዴድ ፖሊሶች ጨቢ አኖሌ ጫካ ከወሰዷቸው በኋላ በረድፍ እንዲተኙ ካደርጉ በኋላ ረሸኗቸው!!

የከረዩ የሚችሌ ገዳ የጅላ አባላት የተገደሉት በኦህዴድ መንግስት ትዕዛዝ መሆኑን ኢሰመኮ አጋለጠ!!

በከረዩ የሚችሌ ገዳ የጅላ አባላት ግድያ ላይ የተደረገ የኢትይጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ( ኢሰመኮ ) የምርመራ ሪፖርት

“በመጨረሻም የሚገደሉበት ሰዓት እየደረሰ እንደሆነ ተነገራቸው”

ድርጊቱ ሲፈጸም በቦታው የነበረ አንድ የአይን እማኝ የነበረውን ሁኔታ አንደሚከተለው ለምርመራ ቡድኑ አስረድቷል፦

“ሁሉንም በቦታው የነበሩ ወንድ የጅላ አባላትን ሰበሰቡ፣ቤት የቀሩ ሰዎችንም እንዲወጡ አድርገው አንድ ቦታ ሰብስበው አስቀመጧቸው፡፡ የጅላ አባላቱ ለውይይት ወይም ለስብሰባ የተጠሩ ነበር የመሰላቸው። በመቀጠል የጅላ አባላቱ የያዙትን መሳሪያ አንዲያስረክቡ ተደረገ፣ ቤት የቀረውንም ቤቶቻቸውን እየፈተሹ ወሰዱ፡፡የያዙት መሳሪያ ፍቃድ ያለው ነበር፡፡ ‘በሀሮ ቀርሳ የተገደሉት ፖሊሶችን ማን ነው የገደላቸው?’ እያሉ ደጋግመው እየጠየቁ በተቀመጡበት ቦታ ይዝቱባቸው ነበር፡፡ እነሱም ድርጊቱ ሌላ ቀበሌ ላይ የተፈጸመ በመሆኑ እንደማያውቁ አስረዷቸው።ፖሊሶቹ ግን ‘ካልነገራችሁን እንገድላችኋለን’ እያሉ ያስፈራሯቸው ነበር፡፡”

በተጨማሪም የፀጥታ አባላቱ የጅላ አባላት ቤተሰብ የሆኑ ሴቶችና ሕፃናትን ነጥለው የአባ ገዳ ባንዲራ የነበረበት ቦታ ላይ በመሰብሰብ ዛቻና ማስፈራርያ የፈጸሙባቸው መሆኑን፣እንዲሁም ድርጊቱ ከተፈጸመባቸው ሴቶች መካከል አንዲት እናት “ከነ ገዳ ሥርዓታችሁ እናቃጥላችኋለን” ብለው ይዝቱ እንደነበር አስረድተዋል፡፡

የፀጥታ ኃይሎቹ በወቅቱ በቦታው የነበሩ ሁሉንም 39 ወንድ የጅላ አባላትን ከሰበሰቡ በኋላ በእግር ወደ አስፋልት መንገድ (ከአዳማ ወደ መታሃራ የሚወስደው መንገድ) የወሰዷቸው መሆኑን በወቅቱ በቦታው የነበሩ ሴት የተጎጂዎች የቤተሰብ አባላት ይናገራሉ። የኮሚሽኑ የምርመራ ቡድን ካነጋገራቸው ምስክሮች መካከል ወደ አርዳ ጅላው በመምጣት ሟቾችን የያዙ፣ የፖሊስ፣ የሚሊሻ እና የአስተዳደር አባላት መካከል የተወሰኑትን በስም ወይም በመልክ የሚለዩዋቸው መሆኑን አስረድተዋል፡፡

አንድ የሟች የጅላ አባል ባለቤት ለኮሚሽኑ ሲያስረዱ፤ “እኛ በሕግ አካላት የተያዙ በመሆናቸው ተመልሰው ይመጣሉ በሚል ተስፋ ሲወሰዱ ብዙም አልተጨነቅንም ነበር፤ነገር ግን የሆነው በተቃራኒው ነው” ብለዋል፡፡

የጅላ አባላት ወደ አስፋልት መንገድ ከተወሰዱ በኋላ የነበረውን ሁኔታ የተመለከቱ የአይን ምስክሮች በበኩላቸው የሚከተለውን አስረድተዋል፡

የፀጥታ ኃይሎቹ 39 የጅላ አባላቱን ከተሰበሰቡበት ቦታ ተነስተው ወደ አውራ ጎዳና (ትልቅ አስፋልት መንገድ) እንዲሄዱ አዘዙዋቸው፣ እነሱም ወደ ታዘዙበት አቅጣጫ ሄዱ፣ በዚህ መካከል የከረዩ አባ ገዳ ‘እኛ ሕጋዊ ሰዎች ነን፤ ከመንግስት ጋር አብረን ስንሰራ ነበር፣ ለዚህም ከመንግስት አካል የተሰጠን መታወቂያ አለን ለምን እንዲህ ይደረጋል?’ ብሎ መታወቂያውን ሲያሳያቸው አንድ የፖሊስ አባል ‘መታወቂያህን ይዘህ አብረህ ትሞታለህ’ በማለት ቀኝ እጁን መታው፡፡ አስፋልት መንገድ ዳር ሲደርሱ ብዙ የፖሊስ ፓትሮል መኪኖች ቆመው ነበር፤ በተጨማሪም መንገድ ሲሄድ የነበረ አንድ ‘ኤፍ.ኤስ.አር አይሱዙ

መኪናን አስገድደው አስቆሙ፡፡ የታርጋ ቁጥሩ እንዳይታይ አድርገው ጭቃ ቀብተው የጅላ አባላቱ እንዲሳፈሩ አደረጉ፡፡ በዚሁ መኪና ከዋናው የአስፋልት መንገድ ወጥተው ወደ ውስጥ በመግባት ራቅ ወዳለ ‘ሃምሳ አምስት’ የሚባለው መንገድ አጠገብ ኛቆ በሚባል ቦታ አወረዷቸውና ለረጅም ጊዜ እንዲቀመጡ ተደረገ፡፡ የመንግስት ባላሥልጣናት ኮብራዎችና የተለያዩ ይዘት ያላቸው ተሸከርካሪዎች በብዛት ሰዎቹ ወዳሉበት ስፍራ መጡ፡፡ በስፍራው የነበሩ የፀጥታ ኃይሎች እና ሲቪል የለበሱ ሰዎች ጭምር ብዙ የስልክ ንግግሮችን ሲያደርጉ ይታይ ነበር፡፡ በዚህ ጊዜ ሟቹ አባገዳ ከድር ሀዋስ ከሚያውቃቸው በቦታው ከተገኙት የመንግስት ባለስልጣናት መካከል አንድ የሚሊሻ ጽ/ቤት ኃላፊን ስም ጠርቶ ስለሁኔታው ቢጠይቀውም፣ ሰውየው አመናጭቆት ከሰደበውና እንደሚገደሉ ከነገረው በኋላ በሆዳቸው እንዲተኙ ተደረገ፡፡ ከመካከላቸው አንዳቸው ቀና በሚሉበት ጊዜ ወደ ታች እየረገጡ ይደበድቧቸው ነበር፡፡ ወደ 12፡00 ሰዓት አካባቢ የጅላ አባላቱን ለሁለት ቡድን ከፈሏቸው፡፡ አባገዳ ከዲር ሀዋስን ጨምሮ 16 ዋና ዋና የጅላ አባላት አንድ ቦታ አንዲሆኑ ተደረገ፡፡ ቀሪዎቹን 23 የጅላ አባላት ..... Read more

https://ehrc.org/ኦሮሚያ-ክልል፡-በከረዩ-የሚችሌ-ገዳ-የጅላ/
Last edited by Wedi on 02 Feb 2022, 21:18, edited 4 times in total.

Misraq
Senior Member
Posts: 17868
Joined: 27 Sep 2009, 19:43
Location: Zemunda

Re: “በመጨረሻም የሚገደሉበት ሰዓት እየደረሰ እንደሆነ ተነገራቸው” የከረዩ የሚችሌ ገዳ የጅላ አባላት የተገደሉት በኦህዴድ መንግስት ትዕዛዝ መሆኑን ኢሰመኮ አጋለጠ!!

Post by Misraq » 02 Feb 2022, 18:07

It looks like OnEG Shene killed 13 Oromia police and security forces around the area.

We will never know if
1) These elders were sheltering OnEG Shene and collaborating with them
2) Also what if OnEG Shene itself killed them to use dirty tactics like the TPLF used on its people?

Politically speaking Prosperity Oromo wing will not benefit killing these elderly. Infact it will do some domage to itself. We can't rule out #1 either and the event being revenge driven by Prosperity Oromo.

In any case, this is one ample evidence that ONeg Shene is not Abiy hidden army as being accused by some narrow amhara activists

Abere
Senior Member
Posts: 15490
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: “በመጨረሻም የሚገደሉበት ሰዓት እየደረሰ እንደሆነ ተነገራቸው” የከረዩ የሚችሌ ገዳ የጅላ አባላት የተገደሉት በኦህዴድ መንግስት ትዕዛዝ መሆኑን ኢሰመኮ አጋለጠ!!

Post by Abere » 02 Feb 2022, 18:22

አባ ገዳ ማለት እኮ ኦነግ ነው። There is no other way to say it. This is not a surprising findings. An OLF killed and other OLF, how is this a big deal.
Misraq wrote:
02 Feb 2022, 18:07
It looks like OnEG Shene killed 13 Oromia police and security forces around the area.

We will never know if
1) These elders were sheltering OnEG Shene and collaborating with them
2) Also what if OnEG Shene itself killed them to use dirty tactics like the TPLF used on its people?

Politically speaking Prosperity Oromo wing will not benefit killing these elderly. Infact it will do some domage to itself. We can't rule out #1 either and the event being revenge driven by Prosperity Oromo.

In any case, this is one ample evidence that ONeg Shene is not Abiy hidden army as being accused by some narrow amhara activists

Wedi
Member+
Posts: 8649
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

Re: “በመጨረሻም የሚገደሉበት ሰዓት እየደረሰ እንደሆነ ተነገራቸው” የከረዩ የሚችሌ ገዳ የጅላ አባላት የተገደሉት በኦህዴድ መንግስት ትዕዛዝ መሆኑን ኢሰመኮ አጋለጠ!!

Post by Wedi » 02 Feb 2022, 18:29

Misraq wrote:
02 Feb 2022, 18:07
It looks like OnEG Shene killed 13 Oromia police and security forces around the area.

We will never know if
1) These elders were sheltering OnEG Shene and collaborating with them
2) Also what if OnEG Shene itself killed them to use dirty tactics like the TPLF used on its people?

Politically speaking Prosperity Oromo wing will not benefit killing these elderly. Infact it will do some domage to itself. We can't rule out #1 either and the event being revenge driven by Prosperity Oromo.

In any case, this is one ample evidence that ONeg Shene is not Abiy hidden army as being accused by some narrow amhara activists
Misraq are you rejecting Ethiopian Human Rights commission Report?
*
Please wait, video is loading...

Educator
Member
Posts: 2370
Joined: 03 Jun 2021, 00:14

Re: “በመጨረሻም የሚገደሉበት ሰዓት እየደረሰ እንደሆነ ተነገራቸው” የከረዩ የሚችሌ ገዳ የጅላ አባላት የተገደሉት በኦህዴድ መንግስት ትዕዛዝ መሆኑን ኢሰመኮ አጋለጠ!!

Post by Educator » 02 Feb 2022, 19:59

Wedi,

Misraq is not rejecting the human rights report, rather supporting the extra judicial killings of anyone suspected of supporting Shane or OLF. Such individuals condone state terrorism when they think it is targeting those they perceive are their enemies . Little they know this kind of terrorism knocks their own door when the time comes. It has been Tigrians and Oromos turn. Tomorro is Amharas turn in the name of eliminating Fano. Brace for the worst. Ethiopia has turned into Isayas' hell with the support of wutaf nekais worshipping one man, Satan Abiy aka Mamo Killo. Did you recall Horus was saying Abiy has the right to arrest qnyone he wants? This Misraq is a similar wutaf nekai moron.
Wedi wrote:
02 Feb 2022, 18:29

Post Reply