Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abaymado
Member
Posts: 4617
Joined: 27 Sep 2017, 21:56

ለኢትዮ ቴሌኮም: እየተደረገ ያለው ቅናሽ በቂ አይደለም: ሀብታሞችን ብቻ ታሳቢ ያረገ ነው

Post by Abaymado » 15 Jan 2022, 06:12


እውነት ለመናገር እዚህ አገር እንደ ቴሌ የሚመቸኝ መስሪያ ቤት የለም:: ንፅህናው: ቅልጥፍናቸውና እንግዳ አቀባበላቸው በጣም አሪፍ ነው:: መብራት ኃይል ደሞ የባሰበት መስሪያ ቤት ነው::

በእነዚህ ሶስት አመታት የዋጋ ቅናሽ ለማረግ በጣም ይደነቃል:: ብዙ ለውጥ አለ:: ከዚህ በፊት ቅናሽ እንዲደረግ የሆነ ፅሁፍ ፅፌ ነበር: ከዛ በህዋላ ሁለቴ ቅናሽ ተደርግዋል:: ጥሩ ነው ግን በዝቅተኛ እና መካከለኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያሉትን ታሳቢ ያረገ አይደለም::

fixed broadband ኢንተርኔት በወር የሚከፈለው መነሻው 500 ብር ነው:: ይህ ከአመታት በፊት ለ 500kb እና ከተሻሻለ በህዋላ ወደ 1mb የተቀየረ እና አሁን ደሞ በተደረገው ቅናሽ ወደ 2mb የተደረገ ነው: : ዋጋው ግን ምንም ፈቀቅ አላለም::

ይህ ዋጋ እንደእኔ ወደ 300 ብር መውረድ አለበት:: ብዙ ሕዝብ ተጠቃሚ ይሆንና የቴሌ ገቢ በብዙ እጥፍ ያድጋል::
አሁን ቴሌ ከፍተኛ ቅናሽ ያደረገው ሀብታሞች የሚጠቀሙበትን የፍጥነት መጠን ነው:: ለምሳሌ በወር 10 ሺ ብር የሚከፍሉ የነበሩ ወደ 5 ሺ ብር ሆኖላቸዋል::
እንደሚመስለኝ ቴሌ መቀነስ ቢፈልግም የፈሩት ነገር አለ:: ምናልባት ተጠያቂ እንሆናል በሚል ይመስለኛል:: እናም ደፍራችሁ አርጉት :: ቅናሹ ሁሉንም ያማከለ ይሁን::

http://www.ethiotelecom.et/fixed-bb-internet/

TARIFF
ACCESS SPEED EXISTING PRICE (BIRR) NEW PRICE (BIRR)

2 Mbps 699 499

3 Mbps 899 699

4 Mbps 1,099 899

6 Mbps 1,499 1,249

10 Mbps 2,300 1,699

20 Mbps 4,320 3,189

30 Mbps 6,320 4,319

40 Mbps 8,350 5,199

50 Mbps 10,350 5,699