Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abere
Senior Member
Posts: 12865
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: የአቢይ አህመድ አገዛዝ ምን አይነት ነው?

Post by Abere » 08 Jan 2022, 20:22

ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊያንን ለማዳን የግድ እነኝህ ሁለቱ ከምድረ ገጽ መጥፋት አለባቸው።
1ኛ) ወያኔ(ትህነግ)
2ኛ) ኦነግ (ብልጽግና ኦነግ፥ ሸኔ፥ ወዘተ)

ከዚህ ውጭ ውይይት አገራዊ ወዘተ ዝባዝንኬ ዓሳማ በውሃ ዘፍዝፎ በሳሙና ማጠብ ነው። የግዛት እና የመሬት ጥያቄ ችግርም አይደለም፤ እነኝህ የህመሙ ምልክቶች ናቸው። የኢትዮጵያ ህዝብ ህመም ወያኔ እና ኦነግ ናቸው። አብይ አህመድ አንደኛ አውሬ ኦነግ ነው። በየዋሃን ህዝብ መካከል ተመሳስሎ የሚኖር የሚፈልጉት እየዘመረ ወጥመድ የሚያስገባ። ይህ ሰውየ በጨለማ ከወያኔ እና ኦነግ ጋር ያሴራል በቀን ደግሞ በንጹሃን ይቀልዳል። በቀላሉ ሊያልቅ የሚችል የትግራይ እና ሌላው ኢትዮጵያዊያን ህዝብ እረፍት ሊያገኝ ሲችል የኦሮሙማው የጥፋት ሴራ መቋጫ ውል እስከሚያገኝ ድረስ ግጭቱ እንድ ቀጥል ይፈልጋል። አሁንም አብይ ስልጣን ላይ ቁጭ ብሎ ይች አገር አንድ ምዕራፍ ላይ ትደርሳለች የሚል ካለ ወይ ሞኝ ወይ ሆዳም ውታፍ ነቃይ ነው። ልክ አንድ አንድ ወፍ እራሽ ዩቲዮቦች እንደሚለጠፉት። አሁን ለእኔ አብይ የኢትዮጵያን ህዝብ ፍላጎት እና መሰረታዊ ግብ የሚያሳካ ሰው አይደለም ስለዚህ ከስልጣኑ በመውረድ ሌላ አገሪቱን በዚህ ወቅት የሚመራ መሪ ያስፈልጋል። የኢትዮጵያ እጣ ሰማይ ቢወጣ ምድር ቢወረድ በውይይት እና በሰላም አይፈታም። መፍትሄው አንድ ነው በጦርነት ወያኔን እና ኦነግን ከምድረ ገጽ ማጥፋት። ያእስካልሆነ ድረስ ለቀጣዮቹ 50 አመታት ለሌላ ጦርነት መዘጋጀት ብቻ ነው። ሌላ 50 አመታት ጦርነት ይታየኛል።
Educator wrote:
08 Jan 2022, 19:59
Correct. Once the coalition government is set up, The leader will be President Sahilework and Abiy will be kicked out of the country. This is also part of the deal. Before the coalition though, Wolkait will be surrendered to Woyane. Had the Amharas kicked him out even 4 or 5 weeks ago.they could have saved Wolkait and Humera. Too bad the hodam Amharas are controlling the whole Amhara region.
Abere wrote:
08 Jan 2022, 17:24
አገሪቱ ጦርነት ላይ ስለሆነች አብይ አህመድ በሌላ ጊዜያዊ መሪ ተተክቶ ጦርነቱን መምራት አለበት። እንደ ሃይለማርያም ደሳለኝ ስልጣን መልቀቅ አለበት።

Horus
Senior Member+
Posts: 34529
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የአቢይ አህመድ አገዛዝ ምን አይነት ነው?

Post by Horus » 08 Jan 2022, 22:52

Abe Abraham wrote:
08 Jan 2022, 19:03
Horus wrote:
08 Jan 2022, 17:54
ክብራምላክ
ማን ሊተካው ይችላል ያልኩት ዝም ብዬ በአጠቃላይ ሳይሆን አሁን ባሉት ሁኔታዎች ውስጥ ማለቴ ነው፤ እሱም አንድ ፒፒ የሚባል ፓርቲ ስልጣን ላይ ቁጭ ብሏል፣ በጦር፣ ሴኩሪትይና ፖሊስ (ያመጽ መሳሪያዎች) ይደገፋል፤ ሁሉም የተቀበለው ምርጫና ፓርላማ መሰረት 5 አመት የሚቆይ አገዛዝ (ሪጂም) አለ። ይህ በሆነበት ሁኔታ አቢይ ሊለወጥ የሚችለው በራሱ ስልጣን ላይ ባለው ፓርቲ ነው፣ ፓርቲው ስለሆነ ጠ/ሚ ያደረገው ። በዚህ መሰረት የሚተካው ሰው ወይ ደመቀ መኮንን፣ ወይ ሌላ ብልጽኛ ሰው ነው ። ያን ማለቴ ነው! እኔ አንድም፣ እደግማለሁ አንድም የአቢይን እስታቹር ያለው ሌላ ፒፒ የለም ። አይ አድዲስ አገር አቀፍ ድምጽ የሚጠይቅ አብዮት ይደረግ ከሆነ ያ ሌላ ሃሳብ ነው ። እኔ ከ5 አመት በኋላ ስላለው ምርጫ አይደለም ሃሳቤ።

እኔ ጦርነት የተባለ ነገር ሁሉ መቆም አለበት ብዬ ስለማምን ነው በመጀመሪያ የብሄር ጥያቄ በገሃድ በአዋጅ ተወግዞ መወገድ አለበት ። ያ ካልሆነ አንድም የሚለወጥ ነገር የለም ። አሁን አንተ ስለ አማራ መጠቃት አልክ። ያ የሆነውኮ በጎሳ ፖለቲካ መሳሪያነት ነው። ኦሮሞ ተመሳሳት የጎሳ ስሌት አለው፣ ትግሬው ፣ ሱማሌው ወዘተ እስከ ታች ደረስ ።

እንዳሻን ብንተነትነው ምንም ሌላ ሪያሊቲ ፕሮዲዩስ አያደርግም! የጎሳ ሞዴል የወለደው ምንም መውጫ የሌለው ቅርቃር ነው። አሁን ያለብን ችግር ሌላ መሪ፣ የተሻለ መሪ ምናምን መለለግ መለወጥ አይደለም ። የሶሺያልና የፖለቲካ አደረጃጀት ሞዴላችን መለወጥ አለበት ባይ ነኝ። የኢትዮጵያ ችግር ቁጥር አንድ መፍትሄ የብሄር ጥያቄን ማውገዝ ነው ።
When I read your text with my Primary School Amharic I pay attention to your word use and when I google some of the words I discover more interesting things like this one :

( " የጎሳ ስሌት " took me to a book on Single Variable Calculus in Amharic. The effort done by the writer is amazing !! )

  • ይህ መፅሃፍ እና ቀድሞ በ፳፻፱ (2017 CE) በርእስ “ነጠላ ተባራይ ንፍቅ ስነ-ስሌት” የታተመው ፅሁፍ ኣላማቸው በትምህርት ቤት ላሉ ተማሪዎች እና ራሳቸውን በራሳቸው ለማስተማር ለሚጥሩ ሁሉ ጥናታቸውን ለመደገፍ/መደጎም እና የስነ-ስሌት ፋይዳን እንዲረዱ ለማድረግ ነው። ኣቀራረቡን ለማቅለል በተቻለ መጠን ተጥሯልና ምናልባት ጠባብ ወይም ውስን ሂሳባዊ ዳራ ያለቸው ኣንባቢዎችም ሆኑ ያለፈ የሂሳብ ጥናታቸውን ለዘነጉ ይረዳል ብለን እንገምታለን። ባጭሩ “ጥርንቅ” (integral) የ”ንፍቅ” (differential) ተቃራኒ ነው። ስለዚህ፣ “ንፍቅ ስነ-ስሌት” (differential calculus) ተግባርን በንኡስ ክፍሎች ከፍሎ እና የክፍሉን “ለከት” (limit) ወስዶ “ቅፅበታዊ የለውጥ ቅልጥፍና” (instantaneous rate of change) እንዳገኘ፣ በሳይንስ እና ምህንድስና ኣግልግሎት እንደሰጠ ሁሉ፣ “ጥርንቅ ስነ-ስሌት” ቅፅበታዊ የለውጥ ቅልጥፍናዎቹን ሰባስቦ በ”መደመር” እና የድምሩን ለከት በመውሰድ የጠቅላላ ለውጡን ውጤት፣ ማለትም፣ ተግባሩን መልሶ በመስጠት ለሳይንስ እና ምህንድስና ታላቅ ኣስተዋፅኦ ይለግሳል። ልገሳውም፣ በኣልጀብራ፣ ስነ-ቅርፅ (Geometry) ወይም ስነ-ዘዌ (trigonometry) ፈፅሞ ሊገኙ ያማይችሉ፣ ከተገኙም ካስፈላጊ በላይ እጅግ የሚያለፉ ፅንሰ-ሃሳቦችን በቀላሉ እና በፍጥነት ሂሳባዊ ቀመራቸውን ለማግኘት መርዳቱ ነው። ጥርንቅ የንፍቅ ተቃራኒ ነውና ኣንዳንድ ጊዜ ኢ-ኑፋቄ ወይም ኢ-ድናን ይባላል። በዚህ ቅራኔ በመመርኮዝ፣ ፅሁፉ በምርጥ እና ቀላል የተግባሮች ድናን (derivative) ጀምሮ፣ “ደናኑ ይህ ሊሆን የሚችል ተግባር ምንድን ነው?” ብሎ በመጠየቅ “ጥርንቅ”ን ያሰተዋውቃል። በተጨማሪም፣ ኣዲስ ፅንሰ-ሃሳብን ለማቅረብ፣ ወደ ፅንስ-ሃሳቡ በሚመሩ ምሳሌዎች እና ጥልቅ ፍቻቸውን በመስጠት ይነሳል። ፅሁፉ ከሁለት መቶ በላይ ምሳሌዎችን የያዘ ከሞሆኑም በላይ በያንዳንዱ ንኡስ ክፍል መጫረሻ በቂ መለማመጃዎችን ይሰጣል። የምርጥ መለማመጃ መልሶች በፅሁፉ ኣባሪ ተካተዋል።
Abe Abraham

በጣም አመሰናለሁ! መልካም ገና

አው የግዕዝ፣ የግሪክ፣ የላቲን፣ የሳንስክሪት (ስንክሳር) እና የቀምጥ (ኮፕት) ቃላት ስሮች በጣም ስለሚዛመዱ አንዳንድ ቃላት የተውሶ እስከ ሚመስሉ ተመሳሳይ ናቸው ። ለምሳሌ ስነስሌት እና ካልኩሌት ተመሳሳይ ናቸው፣ የድምጽ ማፈንገጥ ነው የሚለያዩት ። ለምሳሌ ለከት (ልክ/ልኬት) እና ስል (ስዕል ፣ ስሌት) አንድ ቃል ናቸው። በጉራማይሌ በመጻፋቸው ነው የተለያዩት ። ትርጉማቸው አንድ ነው ። የአንድ ነገር እኩል (ቅጥ) ቅጂ መለኪያው ስዕሉ ወይም ምስሉ ነው። ይህ ጽንሰ ሃሳብ በማቲማቲክስም፣ በኮግኒቲቭ ሳይንስም (ሰነህሳቤ) ያላቸው ትርጉም ተመሳሳይ ነው ። የምናስበው በምስልና በምሳሌ ሲሆን ሂሳብ የምንቀምረው በስዕል ፣ በምልክት፣ በሲምቦል ነው ። ፊደላትና ቁጥሮች ምልክት ናቸው ። ምልክት፣ መለካት፣ መልክ፣ ማርክ ሁሉም አንድ ትርጉም ነው ያላቸው ። ሃ + 1 = ለ (ባለ 5 ምልክት ፎርሙላ ነው፣ ሃ፣ ለ፣ 1፣ +፣ =) እነዚህ ምልክቶች እያንዳንዳቸው ወይ የአንድ ነገር ምስል ወይም የአንድ ነገር ምሳሌዎች ናቸው ። የነገሮች ወኪል ምስለኔዎች ናቸው !!! ኬር

kibramlak
Member
Posts: 2155
Joined: 26 Sep 2013, 09:27

Re: የአቢይ አህመድ አገዛዝ ምን አይነት ነው?

Post by kibramlak » 09 Jan 2022, 01:30

ሆረስ
አብይ አሁን ይውረድ ከሚሉት ጎራ አደለሁም ምክንያቱም ብዙ ውስብስብ ጉዳዮች ስላሉ፣ ማን ሊተካው ይችላል ሌላ ሰው የለም አይነት ላነሳኸው አስተያየት እንጅ፣ ፣ ጀግና እና ታላቅ መሪወች የግድ ከተዋቂወች ጎራ መሆን የለባቸውም፣ መሪነት መታወቅ ሳይሆን የተፈጥሮ ስጦታ ነው፣፣ ያ ስጦታ ያላቸው ብዙ ብዙ ሊገኙ ይችላሉ፣ ግን እንደተባለው ይህች ሀገር በጎሳ ፖለቲካ ተተብትባ ባለችበት ሁኔታ የደም (ጎሳ) ተወካይ እንጅ መሪ አይመረትም፣፣ ይህን ሀቅ መቀበል አለብን፣፣ እብይን አሁን ይውረድ ማለት የሚቻለው ሰለጠን በሚሉ ሀገሮች ብንሆን እና ተቋሞች ለህግ አገልጋይ ቢሆኑ ነበር፣፣ እና ምንድን ነው ሌላ አማራጭ? አንዳንድ የወደፊት የህዝብን ደህነት አደጋ ላይ ለሚጥሉ የአብይ ውሳኔወች የእንቢተኝነት አቋም መያዝ ነው፣፣ ከgrassroot ጀምሮ፣ ማህብፕረሰብን ማንቃት ነው፣፣ እንደውነቱ ከሆነ ይህችን ሀገር መንግስት ሳይሆን የህዝቡ ብልህነት ነው እስካሁን ያቆያት፣፣ አብይ ከሚሸከመው በላይ ስዕል ሰርተንለታል፣ እንደ መሪ ግን ሀገሪቱን መቀመቅ ውስጥ ከቷታል፣፣ በታሪክ ያልታየ የንሮ ውድነት በሀገሪቱ ተንሰራፍቷል፣፣ ሌብነት በሌላ ሀገር የምንሰማውን አይነት በአስደንጋጭ ሁኔታ ተስፋፍቷል፣ የህብታረተሰብ ደህነት እና ዋስትና የለም፣፣ አብይ እኮ አፉን ሞልቶ እንዲህ ብሏል " አንድ ሀገር ውስጥ ስምንት ፣ ብረት እና ነዳጅ ከጠፋ ሀገር እያደገ ነው ማለት ነው" ብሏል ፣፣ እንደ መሪ በጣም ያሳፍራል ፣ እንዲት የጠፋውን ለማቅረብ እንስራ ሳይሆን በችግር እንቀጥል እይነት መልዕክት ነው ለሚሰማው፣፣ አንድ መሪ ሶስት ዋና ዋና መሰረቶች ላይ ካላገለገለ ምኑን መራው፣ 1) ፍትህ 2) ፀጥታና ደህነት 3) ኢኮኖሚ፣፣ በሶስቱም መመዘኛወች እብይ ወድቋል (በገሀድ የሚታይ ስለሆነ)፣፣ ሰው ፖርክ ስለሰራ ይታለላል፣፣ የአሮጊቶችን ቤት እድሳት ላይ ስለቆመ፣ ሊስትሮ መስሎ ጫማ ስለጠረገ፣ የወደቀ ጫማ የቤተ መፅሀፍት ምረቃ ወቅት ስላነሳ፣ ስደተኞችን በአሮፕላን ይዞ ሲመጣ ስለታየ ልክ እንደመንፈሳዊ ወይም መለኮታዊ መሪ እስከመሳል ነው የተደረሰው፣፣ እንኝክ በሙሉ የገፅታ ግንባታ ዝዘዴወች ናቸው፣፣ አብይ በመሰረታዊ ጉዳዮች እላይ በጠቀስኳቸው ሶስት ጉዳዮች የተሻለ ለውጥ አላመጣም፣፣ እንደውም የባሰ አደረጋቸው እንጅ፣፣ ይህን ነው መመርመር ያለብን፣፣ አብይ አንገቴ ቢቀላ በኢትዮጵያ ጉዳይ አልደራደርም ብሎ በተቃራኒው ለአሜሪካ ፍላጎት ስለተንበረከከ ነው እነ ስብሀትን የፈታው፣፣ ይህም ማለት የኢትዮጵያን ደህንነት አደጋ ለሚጥሉ ሀይሎች ማለት ነው፣፣ የተፈቱት አቅም ባይኖራቸው እንኳን መዘዙ ያው ኢትዮጵያን አደጋ ላይ ስለሚጥል፣፣ አብይ ሲበዛ ውሸታም እና ሴረኛ ነው፣፣

ይህን ስል ላይ በጠቀስኳቸው ሶስት መሰረታዊ ጉዳዮች ያልተጠቀሙ የሉም ማለት አደለም፣፣ በእንተ አባባል የጎሳ ከበርቴወች ተጠቅመዋል፣ በሶስቱም፣፣ ፍትህን በማንሻፈፍ፣ ሽብርን በመፍጠር ፣ የኢኮኖሚ ተጠቃሚ በመሆን፣፣ ለሰፊው ማህበረሰብ ግን አልሆነም፣፣

Horus wrote:
08 Jan 2022, 17:54
ክብራምላክ
ማን ሊተካው ይችላል ያልኩት ዝም ብዬ በአጠቃላይ ሳይሆን አሁን ባሉት ሁኔታዎች ውስጥ ማለቴ ነው፤ እሱም አንድ ፒፒ የሚባል ፓርቲ ስልጣን ላይ ቁጭ ብሏል፣ በጦር፣ ሴኩሪትይና ፖሊስ (ያመጽ መሳሪያዎች) ይደገፋል፤ ሁሉም የተቀበለው ምርጫና ፓርላማ መሰረት 5 አመት የሚቆይ አገዛዝ (ሪጂም) አለ። ይህ በሆነበት ሁኔታ አቢይ ሊለወጥ የሚችለው በራሱ ስልጣን ላይ ባለው ፓርቲ ነው፣ ፓርቲው ስለሆነ ጠ/ሚ ያደረገው ። በዚህ መሰረት የሚተካው ሰው ወይ ደመቀ መኮንን፣ ወይ ሌላ ብልጽኛ ሰው ነው ። ያን ማለቴ ነው! እኔ አንድም፣ እደግማለሁ አንድም የአቢይን እስታቹር ያለው ሌላ ፒፒ የለም ። አይ አድዲስ አገር አቀፍ ድምጽ የሚጠይቅ አብዮት ይደረግ ከሆነ ያ ሌላ ሃሳብ ነው ። እኔ ከ5 አመት በኋላ ስላለው ምርጫ አይደለም ሃሳቤ።

እኔ ጦርነት የተባለ ነገር ሁሉ መቆም አለበት ብዬ ስለማምን ነው በመጀመሪያ የብሄር ጥያቄ በገሃድ በአዋጅ ተወግዞ መወገድ አለበት ። ያ ካልሆነ አንድም የሚለወጥ ነገር የለም ። አሁን አንተ ስለ አማራ መጠቃት አልክ። ያ የሆነውኮ በጎሳ ፖለቲካ መሳሪያነት ነው። ኦሮሞ ተመሳሳት የጎሳ ስሌት አለው፣ ትግሬው ፣ ሱማሌው ወዘተ እስከ ታች ደረስ ።

እንዳሻን ብንተነትነው ምንም ሌላ ሪያሊቲ ፕሮዲዩስ አያደርግም! የጎሳ ሞዴል የወለደው ምንም መውጫ የሌለው ቅርቃር ነው። አሁን ያለብን ችግር ሌላ መሪ፣ የተሻለ መሪ ምናምን መለለግ መለወጥ አይደለም ። የሶሺያልና የፖለቲካ አደረጃጀት ሞዴላችን መለወጥ አለበት ባይ ነኝ። የኢትዮጵያ ችግር ቁጥር አንድ መፍትሄ የብሄር ጥያቄን ማውገዝ ነው ።

Guest1
Member
Posts: 1926
Joined: 28 Dec 2006, 01:02

Re: የአቢይ አህመድ አገዛዝ ምን አይነት ነው?

Post by Guest1 » 09 Jan 2022, 02:52

Interesting
የግዕዝ፣ የግሪክ፣ የላቲን፣ የሳንስክሪት (ስንክሳር) እና የቀምጥ (ኮፕት) ቃላት ስሮች በጣም ስለሚዛመዱ አንዳንድ ቃላት የተውሶ እስከ ሚመስሉ ተመሳሳይ ናቸው ። ለምሳሌ ስነስሌት እና ካልኩሌት ተመሳሳይ ናቸው፣ የድምጽ ማፈንገጥ ነው የሚለያዩት ። ለምሳሌ ለከት (ልክ/ልኬት) እና ስል (ስዕል ፣ ስሌት) አንድ ቃል ናቸው። በጉራማይሌ በመጻፋቸው ነው የተለያዩት ። ትርጉማቸው አንድ ነው ።
‘የግዕዝ ፊደል የተገለበጠ የግሪክ አልፋቤት ነው’ በቅርብ ጊዜ አንድ ፈረንጅ የጻፈውን አንብቤአለሁ። ለምሳሌ ያህል ፀ theta ለ ላምዳ ጋምማ ገ ተመሳሳይ ነው። ስለዝህ ከኮፕቲክ ጋር የተያያዘ መሆኑ አይገርምም።እንግዲህ ታሪክን እንድንቃኝ ያደርገናል። ፀ ለ ገ መሰረታቸው ከግብጽ ነውና ከአረበኛ በጣም የተለየ ማለትም ያዳግታል። የግዕዝ አጻጻፍ ከቀኝ ወደ ግራ ሳይሆን ከላይ ወደ ታች እንደ ቻይናዎቹ ነበር መሰለኝ። አናባቢ የሌለው እንደ አረብኛ። እና ሁሉም ነገር በግብጽ የመጣ ሊባል? ወይ ጉድ!
በእንግሊዝኛ ቅጽል baddy goody happy ኢ ገቢ ቀሪ ወጪ noun ...ate ... ity ...ian ነቢያት መጽሃፍት ግዕዝ (አማርኛ ወይም ዘመናዊ ግዕዝ አይደለም ወይ ጉድ! ክክክክ) ከግሪክ የተወረሰ፤ ግሪኮች ከመካከለኛው ምስራቅ ወይም ከግብጽ እነ የመኖችስ? ወይ ጉድ!

ስለምልክት ድምጽን በምልክት ተቀርጾ እየጻፍንበት ነው። አንዳንዴ ስሜትንም! ኣው!! ሰእል የአጻጻፍ መጀመሪያ ላይ ነበር (አሁንም አልጠፋም 8) )። ሰእል ኮንክሪት የምናየውን ኮፒ ማድረግ ነው። አልፋቤት ወይም ፊደል አብስትራክት በጭንቅላታችን የቀረጽነው። ከሁሉም አብስትራክት ቁጥር 1 2 3 ...ወይ ጉድ!

Educator
Member
Posts: 2370
Joined: 03 Jun 2021, 00:14

Re: የአቢይ አህመድ አገዛዝ ምን አይነት ነው?

Post by Educator » 09 Jan 2022, 06:48

Please wait, video is loading...
kibramlak wrote:
09 Jan 2022, 01:30
ሆረስ
አብይ አሁን ይውረድ ከሚሉት ጎራ አደለሁም ምክንያቱም ብዙ ውስብስብ ጉዳዮች ስላሉ፣ ማን ሊተካው ይችላል ሌላ ሰው የለም አይነት ላነሳኸው አስተያየት እንጅ፣ ፣ ጀግና እና ታላቅ መሪወች የግድ ከተዋቂወች ጎራ መሆን የለባቸውም፣ መሪነት መታወቅ ሳይሆን የተፈጥሮ ስጦታ ነው፣፣ ያ ስጦታ ያላቸው ብዙ ብዙ ሊገኙ ይችላሉ፣
Horus wrote:
08 Jan 2022, 17:54
ክብራምላክ
ማን ሊተካው ይችላል ያልኩት ዝም ብዬ በአጠቃላይ ሳይሆን አሁን ባሉት ሁኔታዎች ውስጥ ማለቴ ነው፤ እሱም አንድ ፒፒ የሚባል ፓርቲ ስልጣን ላይ ቁጭ ብሏል፣ በጦር፣ ሴኩሪትይና ፖሊስ (ያመጽ መሳሪያዎች) ይደገፋል፤ ሁሉም የተቀበለው ምርጫና ፓርላማ መሰረት 5 አመት የሚቆይ አገዛዝ (ሪጂም) አለ። ይህ በሆነበት ሁኔታ አቢይ ሊለወጥ የሚችለው በራሱ ስልጣን ላይ ባለው ፓርቲ ነው፣ ፓርቲው ስለሆነ ጠ/ሚ ያደረገው ። በዚህ መሰረት የሚተካው ሰው ወይ ደመቀ መኮንን፣ ወይ ሌላ ብልጽኛ ሰው ነው ። ያን ማለቴ ነው! እኔ አንድም፣ እደግማለሁ አንድም የአቢይን እስታቹር ያለው ሌላ ፒፒ የለም ። አይ አድዲስ አገር አቀፍ ድምጽ የሚጠይቅ አብዮት ይደረግ ከሆነ ያ ሌላ ሃሳብ ነው ። እኔ ከ5 አመት በኋላ ስላለው ምርጫ አይደለም ሃሳቤ።


kibramlak
Member
Posts: 2155
Joined: 26 Sep 2013, 09:27

Re: የአቢይ አህመድ አገዛዝ ምን አይነት ነው?

Post by kibramlak » 10 Jan 2022, 15:52

ራሱ አብይ አስልኮበት ቢሆንስ? ከገሙ ላይቀር በደንብ በኦሮሙማ
ለመግማማት የታለመ ቢሆንስ
Horus wrote:
10 Jan 2022, 15:22

Horus
Senior Member+
Posts: 34529
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የአቢይ አህመድ አገዛዝ ምን አይነት ነው?

Post by Horus » 14 Jan 2022, 23:16

የብሄር ጥያቄ የጎሳ ፖለቲካ ነጋዴዎች ራስ ሰራሽ ጥረታዊ ከበርቴዎች ሳሆን የቢሮ ከበርቴዎች መፈልፈያ የጉቦና ክራይ ሰብሳቢዎች ምሽግ ነው!

Fiyameta
Senior Member
Posts: 15680
Joined: 02 Aug 2018, 22:59

Re: የአቢይ አህመድ አገዛዝ ምን አይነት ነው?

Post by Fiyameta » 15 Jan 2022, 01:41

As an Eritrean, I cringe when I see the Amharic-speaking Ethiopians use the word "አገዛዝ" in stead of "አመራር" for governance. I guess old habits from the feudal era are hard to break.

Horus
Senior Member+
Posts: 34529
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የአቢይ አህመድ አገዛዝ ምን አይነት ነው?

Post by Horus » 15 Jan 2022, 02:22

Fiyameta wrote:
15 Jan 2022, 01:41
As an Eritrean, I cringe when I see the Amharic-speaking Ethiopians use the word "አገዛዝ" in stead of "አመራር" for governance. I guess old habits from the feudal era are hard to break.
ፊያሜታ!
ከኤርትራ ቋንቋዎች የትኛውን እንደ ምትናገር አላቅም፤ ግን የኤርትራ መንግስት 'መንግስቲ ኤርትራ' ነው የሚባለው! መንግስት ማለት ግዛት፣ አገዛዝ ወይም ሩል ማለት ነው ። አመራር ወይም መሪነት ገዢዎች የሚሰሩት ስራ ነው ። መንግስት ማለት ስልጣን ማለት ነው። የአቢይ አገዛዝ ማለት ሪጂም ማለት ነው ። አድሚኒስትሬሽን የሚባለው በኢትዮጵያ ለዝቅተኛ ቢሮዎች መጥሪያ ቃል ነው። ግዛት (አገዛዝ) ማለት መንግስት ማለት ነው ። በኤርትራም ያለው ቃል ያው ነው! አዛዥ ማለት ትዕዛዝ የሚሰጥ ማለት ነው! እዝ ማለት ሩል ማለት ነው !! ሰላም


Horus
Senior Member+
Posts: 34529
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የአቢይ አህመድ አገዛዝ ምን አይነት ነው?

Post by Horus » 12 Feb 2022, 03:08

እጅግ የማከብረው እስማትና ሚዛናዊ የሆነው መላኩ ይልማ የብልጽግና በሽታ ካሳሰበው በውነትም የፓርቲው ችግር ካዳነች አቤቤ ያለፈ ነው ማለት ነው።
ሁልግዜ እንደ ምለው የጎሳው ከበርቴው የሚመሳቀለው በገንዘብ፣ በስልጣን ቅርምት ላይ ነው !


Horus
Senior Member+
Posts: 34529
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የአቢይ አህመድ አገዛዝ ምን አይነት ነው?

Post by Horus » 23 Feb 2022, 02:07

የፖለቲካ ሳይንስ አይስትም ! ኢትዮጵያዊያን የውጭ ጠላት ሲመጣባቸው አንድ ይሆናሉ! ያ ጥላት ዞር ሲል እርስ በርስ መፏከት ይጀምራሉ ! የጎሳ ከበርቴዎችም እንደዚያ ናቸው! አሜሪካ ስልጣናቸውን ሲጋፋቸው ብሄራዊ ከበርቴ ሆነው ያገር አንድነት ጠሩ ልክ የውጭ ዞር ሲል እርስ በርስ መፏከት ብቻ ሳይሆን በሽተኛው የጎሳ ሰርአት እንዳይነካ መከላከር ጀመሩ! ባንዲራ እስከ መከልከል!

Horus
Senior Member+
Posts: 34529
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የአቢይ አህመድ አገዛዝ ምን አይነት ነው?

Post by Horus » 05 Mar 2022, 15:52

ጎሳ ከበርቴው ሌብነት መጋለጥ ተጀመረ

Horus
Senior Member+
Posts: 34529
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የአቢይ አህመድ አገዛዝ ምን አይነት ነው?

Post by Horus » 06 Mar 2022, 01:15

ስለ ሲዳማ የጎሳ ከበርቴ ሌብነት ስሙ!

Horus
Senior Member+
Posts: 34529
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የአቢይ አህመድ አገዛዝ ምን አይነት ነው?

Post by Horus » 06 Mar 2022, 04:24

የጎሳ ቢሮ ከበርቴ የሌብነት ሲስተምና ሊፈነዳ የደረሰው የህዝብ ስቃይና መከራ !


Horus
Senior Member+
Posts: 34529
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የአቢይ አህመድ አገዛዝ ምን አይነት ነው?

Post by Horus » 22 Jul 2022, 01:52

ይህ ከ7 ወር በፊት ያደረግነው ወይይት ነው። ዛሬ አቢይ ቢሞት ፒፒ በማን ይተካዋል? አቢይ እነ ስባት ነጋን ባሜሪካ ግፊት የፈታ ወን ነው የሱ መሪነት ያበቃው ! ከዚያ ወዲህ የለው ነገር ሁሉ ድግግሞሽ ግዜ ማጥፊያ ነው። አሚሪካ አቢይን ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋራ ከቃረነ በኋል ነጥለው ይመቱታል ብዬ ነበር ። መለስ የሞተው ተመርዞ ነው ። ዛሬ እንዴት ነው አቢይ በ45 አመቱ በሃርት አታክ ለ15 ቀን ሆስፒታል ሊተኛ የቻለው። አቢይ ላለመመረዙ ምን ፋክት አለ?

Horus
Senior Member+
Posts: 34529
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የአቢይ አህመድ አገዛዝ ምን አይነት ነው?

Post by Horus » 16 Dec 2022, 16:17

ይህን ያልኩት የዛሬ አመት ነበር!

"ይህ የመንግስት ጥያቄ ነው። መንግስት (እስቴት) እና አገዛዝ (ሪጂም) ይለያያሉ። የትግሬ አገዛዝ እስከ ወደቀበት 2018 ድረስ የነበረው የኢትዮጵያ መንግስት (እስቴት) የጎሳዎች ከበርቴና ንዑስ ከበቴዎች ጥርቅም ቅንጅት ነበር ። አገዛዙ፣ የመለስ አገዛዝ (ሪጂም) በሞላ ጎደል የትግሬ ጎሳ ሪጂም ነበር።

ከበርቴዎቹ ብሄራዊ የግል ከበርቴና ንዑስ አለ፤ በመንግስትና ሪጂም ስልጣን ላይ ያሉት የቢሮ ከበርቴና ንዑስ ከብርቴዎች አሉ ። ሁሉም የጎሳ ከበርቴዎች ናቸው። በመንግስት ስም ቀረጥና ኪራይ ሰብሳቢ ብቻ ሳይሆን ያገሪቱን መሬት ይቆጣጠራሉ፣ በመንግስት ስም ያገሪቱን እርሻና ኢንዱስትሪን ይቆጣጠራሉ ። ስለዚህ እነዚህ የጎሳ ከበርቴዎች ሁሉ መንግሳታዊ ከበርቴዎች ናቸው ፤ እስቴት ቡርዡዋ ናቸው ።

ስለዚህ ነው በያንዳንዱ ጎሳ ውስጥ የፈሉት የጎሳ ከበርቴና ንዑስ ከበርቴዎች በትግሬ ጎሳ ንዑስ ከበርቴ የዛሬ 30 አመት የቆመው የጎሳ ሰርዓት እንዳይለወጥ የሚከላከሉት። የትግሬ ብቸኛ ሪጂምና በትግሬ የጎሳ ቁጥጥር ስር የነበረው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከተናጋ በኋላ፣ ትግሬን የተካው የኦሮማራ የጎሳ ከበርቴ የኢትዮጵያ ብሄረተኛ ሪጂም እንዲሆን ያስገደደው ነገር አለ ። እሱም ከትግሬ ጎሳ ከበርቴ፣ ከግብጽ እና አሜሪካ መንግስት የተቃጣበትን አደጋ ለመቋቋም የኢትዮጵያ ብሄራዊ ህልውና ዘመቻ በማስነሳት መንግስቱን ወደ ኢትዮጵያ ብሄረተኘት እንዲጠጋ ገፍቶታል።

አሁን ትግሬ ከተሸነፈ፣ ግብጽና አሜሪካም ያሰቡት ከከሸፈ በኋላ የኢትዮጵያዊነት ንቅናቄ ከጎሳው ፌዴራሊዝም ጋር ፊት ለፊት መፋጠጣቸው አይቀሬ ነው፣ ባቢይ ዙሪያ ያለው ሃይል ግልጽ የሆነ ዝማሜው አሁን በያዘው የአንድ ኢትዮጵያ ብሄራዊ ርዕዮት ካልጸና ።

በዚህ ምክንያት መንግስታዊ ከበርቴዎቹ ገሚሱ (ባቢይ የሚመራው) ወደ ኢትዮጵያ አንድነትና ኢትዮጵያዊ ብሄረተኘነት ሲቦድኑ ገሚሱ ከበርቴዎች በጎሳ ብሄረተኘነት ጸንተው አሉ። አንዱ በገዢው መደቦች ውስጥ ያለው ቅራኔ ግጭት ይህ ነው ። ባቢይ የሚመራው የኢትዮጵያ ብሄረተኛ መንግስታዊ ከበርቴና የግሉ ዘርፍ ብሄራዊ ከበርቴ በብዙ መንገድ ትብብርና ቅንጅት አላቸው ።

ይህን መሰል ኢትዮጵያዊ፣ አገራዊ ብሄራዊ የመደብ ትብብር የቅኝ ገዥ ኢኮኖሚ ባለቤቶችን አላስደሰተም። ለምሳሌ ያሜርካና አውሮጃ አለም አቀፍ ከበርቴ ከትግሬ ጎሳ ብሄረተኛ ና ጸረ ኢትዮጵያ ከበርቴ ጋር የተቆራኙት በዚህ ምክኛት ነው።

በአቢይ አህመድ የሚመራው መንግስታዊ የቢሮና ንዑስ ከበርቴ በአገር አዳኝነትና የውጭ ጠላት መካችነት ከስሩ ካሉት ጎሳዎች ቁጥጥር የተወሰነ ነጻነት ስለያዘ (እስቴት አውቶኖሚ) ስላገኘ አንዳንዴ የሚወስዳቸው እርምጃዎች ለብዙ ሰው ግር ያሰኛል ። ለምሳሌ ...

ይህ መንግስት እነጃዋርን፣ እስክንድርን፣ ስብሃት ነጋን ሲያስር ወይም ሲፈታ ያለው ክስተት ይህ የመንግስት አንጻራዊ ተጻነት ነው። ሌላ ግዜ ወደ ዜጋ መደቦችና የግል ብሄራዊ ከበርቴዎች ጋር ሲሻረክ ያለው ክስተት ይህ የመንግስት አንጻራዊ ነጻነት ነው።

በአንድ ቃል ይህ በስልጣን ላይ ያለው በኦሮሞ ከበርቴ የሚመራው መንግስት ከጎሳ መሰረቱ መላቀቅ ስለሚሳነው፣ በሌላ በኩል በግድ ከዜጋ የግሉ ዘርፍ ከበርቴዎች ጋር መሻረክ ስላለበት ሁልግዜ የቅራኔዎች አስተናጋጅ ነው። ለምሳሌ የክልል ልዩ አይሎችና ሚሊሺያዎች በኢትዮጵያ ሰራዊት ስር ለመዋጥ አለመፈለጋቸው የዚህ የጎሳ ከበርቴዎ ውስጥ ያለው ውጥንቅጥ የስልጣንና የሃብት ምንጭ ፍትጊያ ነው።

ይህን የማያባራ ፍትጊያን የሚያቆመው የመሬት ይዞታ ከመንግስት ወጥቶ የግል ሲሆን እና መንግስት ከኢኮኖሚው እንዲወጣ ሲደረግ ብቻ ነው ። እንዲሁን የፖለቲካ ስልጣን፣ ዝናና የክብር ምንጭ ከጎሳ ባለቤትነትና ማንነት ወጥቶ የልዑላዊ ግለሰብ ዜግነት ሲሆን ነው።

ስለዚህ አሁን ያሉት ሶስት የትግል አሰላለፎች ናቸው፤ የመንግስት ክንፍ፣ የጎሳ (ክልል) ክንፍ እና የዜጎች የግሉ ክንፍ ናቸው ።"

Post Reply