የተተበተበው ፖለቲካ .. በድርድር ወይስ በቀውስ ሂደት ??
የተተበተበው ፖለቲካ .. በድርድር ወይስ በቀውስ ሂደት ??
Finfinne Times
እርግጥ ነው ግራ ያጋባል። እየፈካ የመጣው ሰላማዊ ሁኔታን መቀበልም ሆነ የጦርነቱ መቀጠል አጠራጣሪ ነው። ብቻ ግራ ያጋባል። በመንግሥት በኩል ስለ ሰላማዊ ድርድር ይወራል። በነጋታው የሆነ ባለስልጣን የሆነ አፍራሽ ቃል ይናገራል። ህዝቡም ግራ ይገባዋዉል ..
ከTDF በኩልም ለሰላማዊ አማራጭ የአፋርና የአማራ ክልል መሬቶችን እንደተለቀቁ ይነገራል። በሳምንቱ ስለ ጦርነት ቀጣይነት ሂደት ይሰበካል። የተለያዩ እንቅስቃሴዎችም ይደረጋሉ። ህዝቡም ግራ ይገባዋዉል ...
በሁለቱም በኩል ያልተጨበጡ ነገራቶች ስለሚደረጉ የቱን መያዝና የቱን ማመን እንዳለብን ግራ ሊገባን ይችላል። ከሁሉም በላይ በዚህ ምስቅልቅል ሂደት ውስጥ ንፁሃን ዋጋ ሲከፍሉም እንመለከታል። ይህ ደግሞ እጅጉን ያሳዝናል።
የሆነው ሆኖ እንደኔ ምልከታ የጦርነቱ መቋጫ ድርድር ነው። ወይም መድረሻ ነጥብ የተደረገለት ድርድር ከፊታችን አለ። ይህንን በአንድ ጀንበር ማስፈፀም እንደማይቻል ደግሞ ካለው ሀገራዊ ቀጠናዊ አለምአቀፋዊ ተግዳሮቶች አንፃር መናገር ይቻላል።
የህዝቡ ስነልቦናም ዶ/ር ደብረፅዮንና ጠ/ሚ አብይ አህመድ ሲጨባበጡ ለማየት ዝግጁ አይደለም። ህዝቡ ብቻ ሳይሆን ብልፅግና ውስጥ ያሉ ጉምቱ ባለስልጣናትም ይህንን ለማየት አይፈልጉም።
ኤርትራና የአማራ ተስፋፊ ልሂቃን በጦርነቱ የነበራቸው ሚና ብሎም ከድርድሩ ሂደት የሚያገኙትና የሚያጡትን ካልኩሌት ካደረግን በምንም መልኩ ድርድሩ ለእነሱ አዋጭ አይደለም።
ስለዚህ ይህንን የቀውስ ትብታብ በጊዜ ሂደቶች መፍታት አስፈላጊ ነው። ይህ ትብታብ የሚፈታው በተለያዩ መንገዶች ነው። በጦርነት በፖለቲካ ስራዎች በፕሮፖጋንዳ ወይም በዲፕሎማሲያዊ መንገዶች ይህንን ትብታብ መበጣጠስ አስፈላጊ ነው።
የአሜሪካን የዲፕሎማሲ ጫናን ወይም የምስራቅ አፍሪካን ፖሊሲ እንደ ዋና የፖለቲካ ካፒታል በመጠቀም ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከአስራ አምስት ቀናቱ ዘመቻ በኃላ በገነቡት ስም በመታገዝና በብልፅግና ፓርቲ ውስጥ ባላቸው ተፅዕኖ በመንተራስ የድርድር ሂደቱን እየመሩ ይገኛሉ።
ከባዱ ነገርን ጦርነቱ ካልቀጠለ ለሚሉት ለኤርትራና ለአማራ ተስፋፊ ልሂቃኖች ጦርነቱን በባለቤትነት አስረክበዋል። ይህንን አሜሪካንም በመግለጫዋ ገልፃለች። ከአሜሪካን ከምዕራብ ትግራይ እንዲወጡ የታዘዙት የአማራና የኤርትራ ሃይሎች ብቻ ናቸው።
በፓርቲው ውስጥ በስልጠና መልኩ የተሰጠው የሰላማዊ ድርድር አስፈላጊነት ማኑዋል ብሎም ድህረ ጦርነት ሂደቶችን ለማስተካከል የሚደረጉ አጠቃላይ ሁኔታዎች ይህንን ጠቋሚ ናቸው።
የድርድር ሂደቱ በአመዛኙ ሰላማዊ ሲሆን በጦርነት በፖለቲካ ስራዎች ወይም በዲፕሎማሲያዊ መንገድ የሚካሄድበት ሁኔታዎችም አሉ። በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ ጦርነት ማካሄድ የድርድሩ ሂደት ሊሆን ይችላል። በተለይ TDF በእራሱ አቅም ምዕራብ ትግራይን ተቆጣጥሮ ነው ለድርድሩ እራሱን የሚያዘጋጀው።
ወሳኙ ነጥብ ደግሞ አሁን በተግባር እየተደረገ ያለው የህዝቡን ስነልቦና የማዘጋጀት ለሰላማዊ አየር ምቹ ሁኔታን የመፍጠር ክንውኖች ነው። የዲያስፖራው መምጣት በቀጣይ የሚደረገው የአፍሪካ ዋንጫ የመሳሰሉት ክስተቶች ለዚህ ማሳለጫነት ይውላሉ።
ከሁለት ወር በፊት ያለውንና አሁን ያለው ሁኔታ በተጨባጭ ልዩነት ያመጣው እንዲሁ ከመሬት በተነሳ አቧራ ምክንያት አይደለም። በሎም እና ደመሰስን የሚሉት ቃላት እየቀዘቀዙ የመጡት እንዲሁ ከመሬት ተነስተው አይደለም።
የድርድሩ ሂደት ሪትሙ ቀዝቀዝ እያለ መድረስ ያለበት ቦታ ላይ እስኪደርስ ድረስ የሁለቱም ተፅዕኖ በዝግታ የሚሄድ ነው። የሆነ ነጥብ ላይ እስኪደርሱ መጎሻሸሞች መጣላቶች ሊኖሩ ይችላሉ። ነገር ግን ዋናው ነጥብ የሆነውን ድርድሩን በፍፁም ሁለቱም አይዘነጉትም። ይኸው ነው ...
Finfinne Times
https://www.facebook.com/permalink.php? ... 1731586155