Please wait, video is loading...
Re: ዲያስፖራው ገባ ተብሎ ምስኪኖች የሚደበቁበት ምክንያት ምንድነው?
አልገባኝም? ምክንያቱም ሊስትሮዎች በጎዳና ላይ እንዳይታዩ ከተባለ ጫማ ማን ሊያሳምራላችው ነው- ለዲያስፓራዎች? ትንሽ ለየት ያለች ምክንያት አለች። ይመስለኛል የአዲስ አባባ ጎዳናዎች እንደሚታወቀው ሌቦች እና ቀማኛዎች እጅግ የሚተራመሱበት ነው። ኪስ ሳይፈተሽ በሰላም ውሎ መግባት አድስ አበባ በጣም አስቸገሪ ነው - እንኳን አሁን ሰው በዝቶ ድሮም ቢሆን። ስለዚህ የጎዳና ላይ ደህንነት በተለይም አገራቸው ለገቡ እንግዶች በጣም አስፈላጊ ነው። ከዚህ አንጻር የጎዳና ላይ ትራፊክ ቅነሳውም ሊስትሮዎችንም ሊቀንስ ይችላል ምክንያቱም ሊስትሮዎች እቃቸውን ተሸክመው ተዘዋዋሪ ናቸው። ዲያስፓራ ለሌባ እና ለአጭበርባሪዎች የተመቹ ላሜ ቦራዎች ስለሆኑ መንግስት ጥበቃ ሊያደርግላችው ይገባል ምክንያቱም መጥፎ ተሞክሮ ከአጋጠማቸው ለወድፊቱ የአገርህን ጎብኝ ግብዣ ተነሳሽነት ይቀንሳል። Remember this marketing fact, an unhappy customer tells between 9-15 people about his/her experience.