Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abere
Senior Member
Posts: 15468
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

የኤርሚያስ ለገሠ ብቸኛው ድል ኢትዮጵያ ከሁለትዮሽ AGOA መታገድ።

Post by Abere » 28 Dec 2021, 12:35

የኤርሚያስ ለገሠ ብቸኛው ድል ኢትዮጵያ ከሁለትዮሽ AGOA መታገድ።ይገርመኛል ወያኔን የምንቃወም ሁሉ ወያኔን የሚራገም ከሆነ ወዳጃችን፤ አብይን የምንቃወም ደግሞ አብይ አህመድን የሚራገም ከሆነ ወዳጃችን ይሆናል። ግን እኛ የኢትዮጵያ ወዳጅ እና ጥላት መለየት የምንችለው መቸ ነው? የተመሳሰለንን ሁሉ ተከትለን የምንነጉድ ከሆነ ዓላማ ቢስ ህዝብ እና አገር እንሆናለን። ኤርሚያስ ለገሰ ለምሳሌ በአጎዋ መታገድ የተደሰተ እንዳምው እንደ ድል አድርጎ የወሰድው ይመስላል። ለነገሩ አጎዋ ኢትዮጵያን የሚይስነጥስም የሚያስልም እዝህ ግባ የሚባል ጉዳይ አይደለም - የሚጠቅመው ነገር ቢኖር የአገሮችን ትስ ስር ነው። ማንኛውም ነገር ደግሞ ነጻ አይደለም:: No lunch is free in America. አጎዋ ሰጥቶ መቀበል እንጅ የበጎ አድራጎት በሰማይ ቤት እቀበለዋለሁ ስራ አይደለም። ቢዝነስ ነው - የገባያ ህግ ተከትሎ ትርፍ የሚገኝበት። ማንም ሂሳብ አጉድሎ ማንንም አይረዳም። በ21ኛው ክፍለ ዘመን የዘመድ ገባያ የለም። እነ ኤርሚያስ ግን ወደ በሉበት ዙረው ይጮሃሉ - ይች ናት የዘመድ ገበያ። ኢትዮጵያን የሚጠቅም ነገር ለመስራት አብይን መደገፍ አይጠበቅብንም - ኢትዮጵያን ብቻ ነው።ኢትዮጵያ ዘላቂ አገር ናት አብይ ግን አርፍዶ ወይ አምሽቶ የሚሄድ ሰው ነው።ውታፍ የነቀለለትም ለዘለዓም አይተክለውም፥ የሚቃወመውም በሃሜት አይገድለውም። ስራው ጠንጋራ ከሆነ ስራው ያስረዋል፥መልካም ከሆነ ደግሞ በስራው ይጸድቃል።

Dibu
Member
Posts: 7
Joined: 26 Dec 2021, 01:58

Re: የኤርሚያስ ለገሠ ብቸኛው ድል ኢትዮጵያ ከሁለትዮሽ AGOA መታገድ።

Post by Dibu » 28 Dec 2021, 16:43

Abere, that is not what he said. Go back and listen to Ermias again. In my view Ermias is an asset to PM Abiye.

Post Reply