Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 11594
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

ለአገር ሲባል አገር ይጥፋ - Yared Hailemariam

Post by sarcasm » 20 Dec 2021, 17:31

ያለፉት ሃምሳ አመታት መፈክራችን፤ ለአገር ሲባል አገር ይጥፋ፤
++++


ለአገር ሲባል ቀይ ሽብር ይፋፋም፣
ለአገር ሲባል ወጣቶች ይረሸኑ፣
ለአገር ሲባል ትርፍ ቤት ይወረስ፣
ለአገር ሲባል መሬት የመንግስት ይሁን፣
ለአገር ሲባል ሹማምንት ይጠብድሉ፣
ለአገር ሲባል መብቶች ይጣሱ፣
ለአገር ሲባል ርሃብ ይንገስ፣
ለአገር ሲባል የዜጎች ርሃብ እና ጠኔ ይደበቅ፣
ለአገር ሲባል ጦርነት ይነሳ፣
ለአገር ሲባል አገር ይገንጠል፣
ለአገር ሲባል ወደብ እንጣ፣
ለአገር ሲባል ሴቶች ይደፈሩ፣
ለአገር ሲባል አፈና ይንገስ፣
ለአገር ሲባል የመንግስት ግድፈቶች ይሸፈኑ፣
ለአገር ሲባል ጎጠኝነት ይጠብድል፣
ለአገር ሲባል ኦነግ ሽኔ ወታደር በይፋ ያሰልጥን፣
ለአገር ሲባል የኤርትራ ወታደሮች ትግራይ ላይ ይፈንጩ፣
ለአገር ሲባል ሰዎች ይፈናቀሉ፣
ለአገር ሲባል ሙስና ይንገስ፣
ለአገር ሲባል ዝምታ ይስፈን፣
ለአገር ሲባል ጋዜጠኞች ይታሰሩ፣
ለአገር ሲባል ፖለቲከኞች ሽብርተኛ ተብለው ይፈረጁ፣
ለአገር ሲባል ጥፋቶች ሲፈጸሙም እያየን እንዳላየን እንሁን፣
ለአገር ሲባል ባለሥልጣናት ሲቀብጡ እና ሲሳሳቱ አይወቀሱ፣
ለአገር ሲባል ሰብአዊ መብቶችም በገፍ ይጣሱ፣
ለአገር ሲባል ሰዎች በዘራቸው ተለይተው ሲጨፈጨፉ ዝም ይባላል፣
ለአገር ሲባል መብት የጣሱ ሹማምንት አይጠየቁ፣
ለአገር ሲባል እነ እንቶኔ ሺ አመት ይንገሱ፣
ለአገር ሲባል እውነት ትቀበር፣
ለአገር ሲባል አጥፊ ሹማምንት በሹመት ላይ ሹመት ይሰጣቸው፣
ለአገር ሲባል ምርጫ ይራዘም፣
ለአገር ሲባል መንገዶች ይዘጉ፣
ለአገር ሲባል ዜጎች በጅምላ ይታሰሩ፣
ለአገር ሲባል ልሂቃን አንገታቸውን እንደ ሰጎን አሸዋ ውስጥ ይደብቁ፣
ለአገር ሲባል ጋዜጠኞች አብዮታዊ፣ ልማታዊ እና ብልጽግናዊ አስተሳሰብ ያራምዱ፣
ለአገር ሲባል ዳኞች ፍትህን ያዛቡ፣
ለአገር ሲባል ፖሊስ ዜጎችን ይደብድቡ፣ ይሰሩ፣ ያሰቃዩ፣
ለአገር ሲባል እውነት እና ፍትህ በአፍጢማቸው ይደፉ፤
ለአገር ሲባል አገር ይጥፋ አዙሪት ዛሪም አለቀቀንም።
ልኺቃን አስመሳይ የሆኑበት አገር እጣፈንታው ከዚህ የተለየ ሊሆን አይችልም።
Please wait, video is loading...