Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
tarik
Senior Member+
Posts: 37252
Joined: 26 Feb 2016, 13:04

Chinese Foreign Ministery:አሜሪካ በሽብር ላይ አካሄድኩ ባለችው ጦርነት ከ37 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ከተለያዩ ሀገራት ተፈናቅለዋል!!! WEEY GUUD !!!

Post by tarik » 14 Dec 2021, 13:13

Please wait, video is loading...

አሜሪካ በሽብር ላይ አካሄድኩ ባለችው ጦርነት ከ37 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ከተለያዩ ሀገራት ተፈናቅለዋል።
***************
(ኢ.ፕ.ድ)

የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ቃል አቀባይ ዋንግ ዊንቢን የአሜሪካ የሽብር ላይ ጦርነት ሚሊዮኖችን ከተለያዩ ሀገራት ያፈናቀለ ነው ሲሉ ይከሳሉ።

አሜሪካ እንደ ሀገር ከተመሠረተች ጀምሮ 92 በመቶ የሚሆነውን ዘመኗን በሌሎች አገራት ላይ ጦርነት በማካሄድ ያሳለፈች አገር ናት ያሉት የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማስረጃቸውን በቁጥር አስደግፈው በማህበራዊ ትሥሥር ገጻቸው አስፍረውታል።

እኤአ ከ1992 እስከ 2017 ድረስ ባሉት 26 አመታት ውስጥ ብቻ አሜሪካ ለ188 ያህል ጊዜ በሌሎች ሀገራት ላይ በወታደራዊ መልኩ ጣልቃ ገብታለች። በዚህ የአሜሪካ ወታደራዊ ጣልቃገብነት የተነሳም ሀገራት ከፍተኛ ፓለቲካዊ፡ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ቀውስ ውስጥ ገብተዋል።

አሜሪካ ሽብርን ለመዋጋት በሚል ባካሄደችው ጦርነት ከ37 ሚሊዮን በላይ የተለያዩ ሀገራት ዜጎች ከሀገራቸው ተፈናቅለዋል። አሜሪካ በኢራቅ፡ በአፍጋኒስታን፡ በየመንና በሶሪያ ሽብርተኝነትን ለመዋጋት ያደረገችው ወታደራዊ ዘመቻ ለዜጎቹ መፈናቀል ዋና ምክንያት መሆኑን ቃል አቀባዩ ገልጸዋል።