-
Ewnetu Enyew
- Member
- Posts: 1
- Joined: 11 Dec 2021, 14:01
DEBEBE ESHETU
ደርግ አጼ ኃይሌ ሥላሴን መስከረም 2 ቀን 1967 ዓም ከዙፋናቸው ማስወረዱ ይወደድለት ዘንድ ለመጀመሪያዎቹ ጥቂት ቀናት ታዋቂ ሰዎችን በኢትዮጵያ ሬዲዮ እያስቀረበ የድጋፍ ንግግር ሲያስነግር ነበር። በዚህ መሠረት አቶ ደበበ እሸቱ በኢትዮጵያ ራዲዮ የተናገሩት የጃንሆይን መውረድ ጧት ቤታቸው እንዳሉ በራዲዮ ሲሰሙ እጅግ ተደስተው አንጀታቸው መራሱን ነበር። ግን አቶ ደበበ የጃንሆይን መውረድ ያወቁት ቤታቸው እንዳሉ በሬዲዮ በመስማት ሳይሆን ከሻምበል ደበላ ዲንሳ ቡድን ጋር ቤተመንግሥቱ ተገኝተው መሆኑ ከዓመታት በኋላ በወጣው ፎቶግራፍ ታየ። ሻምበሉ የጃንሆይን መውረድ ሲያነብቡ አቶ ደበበ እሸቱ ያዩትም የሰሙትም ቤተመንግሥቱ ውስጥ ከሻምበሉ ኋላ እንደቆሙ ነበር። ግን ሐቁን ደብቀው ለኢትዮጵያ ሕዝብ በመዋሸት ደርጉን አስደሰቱ። የጃንሆይ መውረድ ደግሞ ከፍተኛ ነገር ስለነበር ወደየት እንደሚያመራ ታግሦ ማየት ሲገባ ገና በሁለተኛው ቀን መፈንጠዝም ችኩልነት እንጂ በሳልነት አልነበረም። ሁኔታዎችን በሚገባ በማጤን ፈንታ መቸኮል ይኸው ከብዙ አሥርተ ዓመታት በኋላ ዐቢይ አሕመድ ሥልጣን ሲይዝ ሌሎች ታዋቂ ሰዎችም ላይ ታየ።