Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
tarik
Senior Member+
Posts: 37238
Joined: 26 Feb 2016, 13:04

Ethiopia Chaired Z 8th African Union Summit 2Day:Demeqe Said No Foreign Meddling In African Matters!!! WEEY GUUD !!!

Post by tarik » 04 Dec 2021, 11:21


Ethiopian Press Agency /የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት/
48m ·
በአፍሪካ ሃገራት የውስጥ ጉዳይ ላይ የሚደረገው ጣልቃ ገብነት ተቀባይነት እንደሌለው ተገለፀ
👉 8ተኛው የአፍሪካ የሰላምና ፀጥታ ከፍተኛ ጉባኤ በኢትዮጵያ በሊቀመንበርነት እየተመራ ነው እየተካሄ ያለው፣
*****************
(ኢ ፕ ድ)
በሰብዓዊ መብትና በሰብዓዊ ድጋፍ ሰበብ በሉዓላዊ ሃገራት የውስጥ ጉዳይ ላይ የሚደረግ ጣልቃ ገብነት ተቀባይነት እንደሌለው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ገለፁ፡፡
በአቶ ደመቀ መኮንን የሚመራው ከፍተኛ የመንግስት ልዑካን ቡድን በአልጄሪያ ኦራን ከተማ 8ተኛው የአፍሪካ የሰላምና ፀጥታ ከፍተኛ ጉባኤ ላይ ተሳትፏል፡፡
በጉባኤው በአፍሪካ ህብረት የሰላምና የፀጥታ ምክር ቤትና በተመድ አፍሪካን ወክለው የሚሳተፉ ተለዋጭ አባል አገራት መካከል በተ.መ.ድ የፀጥታ ምክር ቤት የአፍሪካን የጋራ ጥቅም ሊያስጠብቅ በሚችል ግንኙነትና ትብብር ላይ ትኩረት አድርገው መክረዋል።
8ተኛው የአፍሪካ የሰላምና ፀጥታ ከፍተኛ ጉባኤ ኢትዮጵያ በሊቀመንበርነት በምትመራው መድረክ ላይ አቶ ደመቀ፤ በተመድ ባለብዙ ወገን ግንኙነትን ወደ ጎን እየተገፋ እንዲሁም አንዳንድ ሃያላን ሃገራት በራሳቸው ባለአንድ ወገን መርህ ላይ ተመስርተው በአፍሪካ ላይ የሚያደርጉት ያልተገባ ተጽዕኖ ሊቆም እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
"በሰብዓዊ መብትና በሰብዓዊ ድጋፍ ሰበብ በማድረግ በሉዓላዊ ሃገራት የውስጥ ጉዳይ ላይ የሚደረግ ጣልቃ ገብነት መወገዝ ይኖርበታል፡፡" ብለዋል፡፡
በጉባኤው ላይ የአፍሪካ ህብረት የሰላምና የፀጥታ ምክር ቤት ተለዋጭ አባል ሃገራት በተ.መ.ድ የፀጥታ ምክር ቤት የተጫወቱት ሚና ገንቢ ቢሆንም፤ በሃያላን ሃገራት የሚደርስባቸውን ጫና ተቋቁመው የአፍሪካ ሃገራትን ፍትሃዊ ጥቅም ለማስጠበቅ እንዲችሉ በተባበረ ድምጽ እና በተቀናጀ ተግባር ሊደገፉ እንደሚገባ ተመላክቷል፡፡
የአፍሪካን ችግር በአፍሪካውያን የመፍታት መርህን መጋፋት ተቀባይነት እንደሌለው ጉባኤው በስፋት የመከረ ሲሆን፤ አሸባሪነትን በመደገፍ፣ ሙስና እና ኢ-ህገመንግስታዊ በሆነ መንገድ መንግስት ለመቀየር የሚደረግ ህገወጥ እንቅስቃሴ አፍሪካውያን በቅንጅት መመከት እንደሚገባቸው ጉባኤው አስምሮበታል፡፡
ጉባኤው በኢትዮጵያና አንዳንድ ሃገራት ላይ የሚደረጉ ተመሳሳይ ጫናዎችን በማሳያነት የተመለከተ ሲሆን፤ አፍሪካውያን በፓን አፍሪካኒዝም መርህና አስተሳሰብ እየተመሩ ችግሩን በጋራ ሊመክቱ እንደሚገባ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል።፡
እንደአቶ ደመቀ ገለፃ በዚህ ዓመት ኢትዮጵያ ሉዓላዊነቷን ለማስከበር በወሰደችው የህግ ማስከበር እርምጃን ተከትሎ ተጽዕኖ ለመፍጠር እና ማዕቀብ ለመጣል የሚደረጉ ጫናዎች ተቀባይነት አይኖራቸውም።
"ኢትዮጵያ የውስጥ ችግሯን በራሷ የመፍታት አቅም እና ብቃት አላት።" ብለዋል አቶ ደመቀ።
አሸባሪ እና ወራሪው ሃይል ከውስጥ እና ከውጭ ካሉ ፀረ-ኢትዮጵያ ሃይሎች ጋር በመቀናጀት የሚያካሂዱትን ዘመቻ የኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት በአስተማማኝ ሁኔታ እየቀለበሱት መሆኑን በመጠቆም፤ ችግሩን በዘላቂነት የመፍታት ርብርቡ ተጠናክሮ እንደሚቀጠል አረጋግጠዋል፡፡
ይሁንና አንዳንድ የዓለም አቀፍ ሚዲያዎች እና ተቋማት የሃሰት እና የተዛባ መረጃ በማሰራጨት የሚያደርጉት ያልተገባ እንቅስቃሴ፤ በኢትዮጵያ መሬት ላይ ካለው እውነት ጋር ፈፅሞ የሚጋጭ እና የሚቃረን መሆኑን ጠቁመዋል።
ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረት የሰላምና የፀጥታ ምክር ቤት በፈረንጆች አቆጣጠር በዴሴምበር ወር 2021 ዓ.ም ሊቀመንበርነት የምትመራ ሲሆን፤ ለወሩ የተያዙ አጀንዳዎችን የአፍሪካን ጥቅም ባስከበረ መልኩ እንዲካሄድ አስፈላጊውን ዝግጅት መደረጉን ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
አካባቢህን ጠብቅ‼️
ወደ ግንባር ዝመት‼️
ሠራዊቱን ደግፍ ‼️
ተጨማሪ የመረጃ አማራጮቻችን
ዩቲዩብ
https://youtube.com/channel/UCoH2CVwWn9suWP7q0u2L7MA
ቴሌግራም
https://t.me/ethpress
ትዊተር
https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ
https://www.press.et/