Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
tarik
Senior Member+
Posts: 37233
Joined: 26 Feb 2016, 13:04

^^^(((JUST IN)))^^^:Bangladesh Ambassador 2 Ethiopia Said Let Ethiopia Solve It's Internal Issues Alone!!! WEEY GUUD !!!

Post by tarik » 25 Nov 2021, 15:54

thiopian Press Agency /የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት/
1h ·
ኢትዮጵያ ውስጣዊ ችግሯን በራሳ የመፍታት አቅም እንዳላት በኢትዮጵያ የባንግላዴሽ አምባሳደር አስታወቁ
*********************
(ኢ ፕ ድ)
ኢትዮጵያ የገጠማትን ወቅታዊ ችግር እንገነዘባለን፤ በመሆኑም ኢትዮጵያ የገጠማትን ችግር ያለማንም ጣልቃ ገብነት በውስጥ አቅሟ መፍታት ትችላለች ሲሉ በኢትዮጵያ የባንግላዴሽ አምባሳደር ናዝሩል ገለጹ። ባንግላዴሽ ከኢትዮጵያ ጎን እንደምትቆም ጨምረው ገልፀዋል።
በኢትዮጵያ የባንግላዴሽ አምባሳደር ናዝሩል ኢስላም ከባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት
ጋር ሁለቱ ሀገራት በጋራ በሚሰሩበት ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።
በውይይታቸውም አምባሳደር ማዝሩል ኢትዮጵያና ባንግላዴሽ የቆየ ግንኙነትና ወዳጅነት እንዳላቸው ጠቁመው ፤ ሁለቱ ሀገራት በተለይ በስፖርትና በባህል ዘርፍ በትብብር ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸው ተናግረዋል።
አለም አቀፍ ሚዲያዎች ኢትዮጵያን በተመለከተ የሚያሰራጩት መረጃም ከእውነት የራቀ ነው። በአዲስ አበባ በአሁኑ ሰዓት ሰላም መሆኑን አምባሳደሩ አረጋግጠዋል።
ሁለቱን ሀገራት በስፓርትና በባህል ልውውጥ ሊያሳድግ የሚያስችል የአርት ኤግዚቢሽን እያዘጋጀ መሆኑን የገለፁት አምባሳደሩ ፤ ሚኒስትር ዴኤታው በዕለቱ መልዕክት እንዲያስተላልፋ ግብዣ አቅርበዋል።
ሚኒስትር ዴኤታው አምባሳደር መስፍን ቸርነት በበኩላቸው የሁለቱ አገራትን ግንኙነት በማጠናከር በባህልና በስፖርት ዘርፍ በጋራ ለመስራትና ልምድ ለመለዋወጥ በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ተደጋግፈው ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸው አንስተዋል ።
የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ ለአምባሳደሩ ገለፃ ያደረጉ ሲሆን ባንግላዴሽ በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ከጣልቃ ገብነት ነፃ የሆነ አቋሞ በመያዝ ኢትዮጵያ የውስጥ ችግሯን በራሷ እንደምትፈታ ለያዘችው አቋም አድናቆታቸውን መግለፃቸውን ሚኒስቴር መስሪያቤቱ አስታውቋል።
አካባቢህን ጠብቅ‼️
ወደ ግንባር ዝመት ‼️
ሠራዊቱን ደግፍ ‼️
ተጨማሪ የመረጃ አማራጮቻችን
ዩቲዩብ
https://youtube.com/channel/UCoH2CVwWn9suWP7q0u2L7MA
ቴሌግራም
https://t.me/ethpress
ትዊተር
https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ
https://www.press.et/