Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Ejersa
Member
Posts: 3978
Joined: 05 Nov 2019, 10:39

በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 5 ሚሊየን ብር ተያዘ!

Post by Ejersa » 19 Nov 2021, 03:56

በምዕራብ አርሲ ዞን በኮፈሌ ከተማ በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 5 ሚሊየን ብር መያዙን የወረዳው ፖሊስ የወንጀል መከላከል ዲቪዥን አስተባባሪ ዋና ሳጅን በዳሶ ጉደታ ገለፁ፡፡

በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ ብር የተያዘው ከሻሸመኔ ከተማ ወደ ነንስቦት ከተማ ሊተላለፍ ሲል በኦሮሚያ ልዩ ፖሊስና በኮፈሌ ከተማ ፖሊስ ጥምረት ነው፡፡

ብሩ ለጥፋት ተልኮ ሊውል ሲል መያዙም ታውቋል፡፡

ከጉዳዩ ጋር በተያያዘም ሁለት ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራ መሆኑ ተገልጿል፡፡