ሶስቱ ተጠርጣሪዎች ተልእኮአቸውን በሚስጢር ለማከናወን ሲንቀሳቀስ በህዝብ ጥቆማ ትብብር መያዛቸውን የኢሳት የመረጃ ምንጮች ተናግረዋል።
ግለሰቦቹ በዛሬው ዕለት በስሚት የኮንዶሚኒየም ግንባታ ሳይት በጥበቃ ድርጅት ውስጥ ተደብቀው መያዛቸውም ታውቋል።
እነዚህ ተጠርጣሪዎች የሳውዲ ፖስፖርት ያላቸው እንዲሁም የአዲስ እበባ የነዋሪነት መታወቂያ የሀሰት በማሰራት ሲንቀሳቀሱ ነበር ተብሏል።
ተጠርጣሪዎቹ የአሽባሪውን ህወሀት ተልዕኮ ሊፈፅሙ ሲንቀሳቀሱ በህብረተሰቡና በዙሪያው ባሉ ሰራተኞች የነቃ ተሳትፎ በቁጥጥር ስር ውለዋል።
