Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abe Abraham
Senior Member
Posts: 14414
Joined: 05 Jun 2013, 13:00

ደፂ ወኔ ከድቶት፣ ትእቢቱ ቀዝቅዞ፣ ሞራሉ ወድቆ፣ በኮስማና ድምፅ የሰጠው መግለጫ እና ከዛሬ በፊት ካደረጓቸው የንቀት ንግግሮች ውስጥ ሁለቱን በቅምሻ መልክ ጀባ ብያለሁ።

Post by Abe Abraham » 15 Nov 2021, 00:26




  • Courtesy of Misraq

    በብርሃኑ ተፈራ

    የደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ፅንፍ የረገጡ ንግግሮች

    አሁን በህወሓት መንደር የሆነ ብርድ ብርድ የሚያስብል ነገር ገብቷል። መከላከያ ትግራይን ለቅቆ ከወጣ በኋላ የልብ ልብ ተሰምቷቸው የነበሩት የህወሓት አመራሮች፤ ሁሉም ነገር እንዳሰቡት የሆነላቸው አይመስልም።

    ከሳምንት በፊት: ጦርነቱ ተጠናቋል እጃችሁን ስጡ እንዳላሉን ሁሉ፤ ዛሬ ደግሞ ምንጩም ፖለቲካዊ ነው፤ መፍትሄውም ፖለቲካዊ ነው። በሃይል አያልቅም ሲሉ ተደምጠዋል።

    በእኔ እምነት የዛሬውን የደብረፂዮን ንግግር ማየት በራሱ ብዙ ነገር ያሳብቃል። ደፂ ወኔ ከድቶት፣ ትእቢቱ ቀዝቅዞ፣ ሞራሉ ወድቆ፣ በኮስማና ድምፅ የሰጠው መግለጫ እና ከዛሬ በፊት ካደረጓቸው የንቀት ንግግሮች ውስጥ ሁለቱን በቅምሻ መልክ ጀባ ብያለሁ።