አንድ፣ ኢትዮጵያን እስከ ነጻነቷ ለመጠበቅ ልክ አሁን የተነሱባት ጠላቶችን ማሸነፍ አለባት ። ይህ መንግስት ፈሪው የሃይለ ስላሴ መንግስት አይነት አይደለም ። ይህ መንግስት በህዝብ የተጠሉት የደርግና የዎያኔ ትግሬ ማለትም የባንዳዎች መንግስት አይደለም ።
ኢትዮጵያ ከየትኛውም የውስጥ ሆነ የውጭ ጠላት ታግላ ለማሸነፍ ዛሬ ያለው ያቢይን መንግስት የተሻለ የለም ። ውጭ ውጩን ይመስላል እንጂ ኢትዮጵያ እጅግ አንድነት ያላት አገር ነች፣ መንግስትም አንድነት አለው ። የክልል ጦር ማዕከላዊ እዝ መግባት አለበት ።
ይህ መንግስት ትህነግን መቶ በመቶ እንዲያጠፋ ህዝቡ ማንዴት ሰጥቶታል ። እግሩን ሚጎትት መንግስት እንጂ ህዝቡ የዎያኔ መከሰም ከጠየቀ አመታት አለፉ ። ዛሬ ይህ መንግስት በትግሬ ባንዳ የተፈጠረውን ቆሻሻ የጎሳ ስርዓት መቶ በመቶ የማጥፋት ታሪካዊ ዕድል አለው።
ኢትዮጵያ በራሷ ጥረት እስከ ነጻነቷ ማደግ የምትችለውን ያክል የማሳደግ ታሪካዊ እድል ለዚህ መንግስት ተሰጥቶታል ። በምዕራብ ባርነትና በዉሸት ብድር ጂዲፕ ማሳደግና ህዝባችን በራሱ ጉልበት፣ ምግቡን፣ ልብሱን ቤቱን፣ ወዘተ ማምረት መጀመሩ ነው ታሪክ እንጂ ካሜሪካ ስንዴ እየለመኑ ሰው መስሎ በሸንጎ አገር መሆን ያሳፍራል ።
ስለዚህ በሚቀጥሉት ወራትና አመታት የምራብ እርዳታ የሚባል ማስቆም አለብን ። ምራብ ከኛ ጋር እንዲነግድ እንጂ እንዲረዳን አንፈልግም ።
ዉሸታሙ አሜሪካ እቃችን ለሱ እንዳንሸጥ ከልክሎ ስንዴ በነጻ ማለት አሳፋሪ ስድብ ነው ። ስለዚህ ይህን መሰል የነጻ ሰርቶ በላ ሕዝብ ባህሪ ላለም ለማሳወቅ እድል የተሰጠው መንግስት ነው፣ ያቢይ መንግስት ።
ኢትዮጵያ ያፍሪካ ነጻነት መሪ ነች በሚለው ለምናምን ሁሉ ለዚያ መሪነት የሚከፈለው ዋጋ በአለም ኢምፔሪያሊስቶች መጠመድ መጠቃት ነው ። ይህ ነው ኢትዮጵያን ከሌላ ኒዮኮሎሚያል አገር፣ ለምሳሌ ግብጽ የሚለየን! ኢትዮጵያ ለምንድን ነው በ3 ሺ ዘመን ታሪኳ በቅኝ ያልተገዛችው? ልክ ዛሬ እንደ ምታደርገው ቅኝ ገዦችን ወግድ ብላ ንቃ ጸንታ ስለምትቆም ነው!! ይህ ነው የኢትዮጵያ ካራክተር! ይህ ነው የኢትዮጵያዊነት ምስጢር !!!
