*ለዚህ ታሪክ መብቃቴ ኩራት ይሰማኛል:ወደን ፈልገን ያመጣነው አይደለም ከልጅ: ልጅ-ልጆቻችን ጋር መሆን ነበር የምንፈልገው: የተሻለ ኑሮም ነበረን
* ለትግራይ ህዝብ ይህን ማድረጌ እንደ እድለኝነት ነው የምቆጥረው .. ይህንን የማያደርግ ደግሞ ፈሪ ነው
* ️ጀግና ሰውን ያከብራል: ጀግና ሴት አይደፍርም: ጀግና አይሰርቅም: ጀግና ንብረት አያወድምም: ጀግና ትሁት ነው ይሄን ሁላ የሚያደርግ ፈሪ ነው
* ️የኤርትራ መንግስት ለጦርነት ዝግጅት ማድረግ አይጠበቅበትም ምክንያቱም ኤርትራ ውስጥ 12 ክፍል ጨርሰህ ወደ ጦር ካምፕ ትገባለህ ከዛ ኢሳያስ ወደ ሚያሰማራህ ትሄዳለህ
* ኢሳያስ ኢ/ያ ውስጥ እንደፈለግኩ ልሁን ሲል "ተው" ስለተባለ ብቻ ፖሊሲ ቀርፆ ሀገሩ መለወጥ ሲችል ለሁሉም ነገር ውድቀቱ #ወያኔ እያለ ጥላቻ ና ቂም ነበረው
* አሁን የሚፈልገው አግኝቷል በተቻለው አቅም ትግራይን አውድሟል:ኢ/ያ ውስጥ ያሉትም ከ27 በላይ በመንግስት የሚታወቁ የምንዛሬ ቢሮዎች ተቆጣጥሯል
* ወደ ኤርትራ ሚሳይል ከመተኮሱ በፊት ዛላንበሳ ላይ ከ2ት ሳምንት በላይ ከኤርትራ ጋር ተዋግተናል
* ህወሓት ታንኩም ባንኩም ትቶላቸው ወደ ክልሉ መጥቶ ህዝቤ ላስተዳድር ሲል: "አታስተዳድርም ከፈጣሪ ቀጥሎ ኢ/ያ ውስጥ ያለው የአማራው ሀይል በሚለው ነው መሄድ ያለብህ ነው ያሉት"
* የአማራ ህዝብ እንደሌላው ህዝብ ሰርቶ መኖር እንጂ የበላይነት ኑሮት (ኤሊቶቹ እንደሚሉት) ለመኖር አይደለም የሚፈልገው
* ️የኢ/ያ ችግር ብቻችን እንፈታዋለን ብለን አናቅም : የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች እና ፖለቲከኞች የተካተቱበት የሽግግር መንግስት ይፈልጋል
* ️በታሪክ የራሱን ህዝብ ከውጭ ሁኖ የወረረ መሪ እኔ አላውቅም
* ምኒሊክ ለጀመረው ስርዓተ መንግስት ለመቀጠል ስጋት ይሆንብናል ብለው ያሰቡት ህወሓት ና የትግራይ ህዝብ ነው
Please wait, video is loading...