Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 11594
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ተሹመው የነበሩት የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከፍተኛ ባለስልጣን በትግራይ ክልል ያለጥርጥር የዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈጽሟል አሉ።

Post by sarcasm » 29 Oct 2021, 07:50

በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ተሹመው የነበሩት የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከፍተኛ ባለስልጣን በትግራይ ክልል ያለጥርጥር የዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈጽሟል አሉ።

ማለዳ ሚዲያ
**************


ብልጽግና ፓርቲ እንዳደራጀ የሚነገረው የቀድሞ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የካቢኔ ጉዳዮች ሴክረታሪ እና የፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ኃላፊ የነበሩት ገብረመስቀል ካሳ 'ምንም ጥርጥር የለውም በትግራይ ክልል በደንብ ታቅዶበት በመንግሥት ተመርቶ የተፈጸመ የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ ተፈጽሟል' ሲሉ ለግሎብ ኒውስ ኔት ገለጹ።
አቶ ገብረመስቀል ለሚዲያው በሰጡት ቃለ ምልልስ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ጦርነቱ ከመጀመሩ ሁለት ሳምንት አስቀድሞ ከፈንቅል፣ ከትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ፣ ከትግራይ ብልጽግና አባላትና ከሌሎች የትግራይ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የተወጣጡ በቁጥር 200 የሚጠጉ በቀጣይ ትግራይ ክልልን ሊመሩ ያዘጋጃቸውን ሰዎች አዲስ አበባ ከተማ ስብሰባ በመጥራት 'በሶማሌ ክልል እንዳደረኩት ከ3-5 ቀናት ውስጥ ህወሓትን ከስልጣን አወርዳለሁ' ብሎን ነበር ወደ ጦርነት የገባው ሲሉ የጦርነቱን መነሻ አስረድተዋል።

ከጦርነቱ ጅማሮ በኋላ በአክሱም ከተማ ጭፈጨፋ የሞቱ ከ800 እስከ 1100 የሚጠጉ ንጹሃን አስከሬን በጋሪ ተጭኖ አንድ ላይ እንዲቀበር በአካል ተገኝቶ የኤርትራ ጦር አዛዦችን በማግባባቱ ቀብር ማስፈጸሙን፣ በውቅሮ፣ በኢዳጋ ሐሙስ እና በርካታ ቦታዎች ተገድለው የተጣሉ ንጹሐን ዞሮ ስለመመልከቱም ይናገራል።
የአልመዳ ጨርቃጨርቅ፣ ሳባ እምነበረድ፣ አዲግራት መድኃኒት ፋብሪካ፣ የጎዳ ብርጭቆ ፋብሪካ፣ ሰማያታ እምነበረድ፣ ሼባ ሌዘር ወዘተ በኤርትራ ሰራዊት ዘረፋና ውድመት ገጥሟቸዋል። የጤና፣ የትምህርት መሰል የህዝብ መገልገያ ተቋማት ሆን ተብለው እንዲወድሙ ተደርገዋል።

እንደ ገብረመስቀል ገለጻ የግለሰብ መኖሪያ ቤት፣ ሱቆች፣ ቤተክርስቲያን በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አባላት ተዘርፈዋል: ከግለሰብ ዘርፈው በባንክ አካውንታቸው እስከ 10 ሚሊዮን ብር ያስቀመጡ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አባላት አሉ።

ከሶማሊያ የመጡ ወታደሮች በሽሬ ከተማ ዲያቆናትንና ሙሉ ቤተሰቦቻቸውን እላማ ያደረገ በጭካኔ የተሞላ ጭፍጨፋ ፈጽመዋል። ሰዎችን በቢላዋ ጎሮሮኣቸውን እየቀደዱ ገድለዋል።

የፌዴራል ከፍተኛ ሲቪልና ወታደራዊ ባለስልጣናት እነ ዳንኤል ክብረት፣ 'አገኘው ተሻገር'፣ ተመስገን ጥሩነህ፣ ጀነራል አበባው ታደሰ እና ሌሎች በብሔር አማራ የሆኑ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች በትግራይ ህዝብ ጥቃት እንደሚሳለቁ፣ የሰብዓዊ እርዳታም እንደሚያደናቅፉ ገልጿል። ባንድ ወቅት ዳንኤል ክብረት "ችግር ብቻ ማውራት አቁሙ: ገና ምኑ ተነካና" እንዳሏቸውም ያስታውሳል።

እንደ ገብረመስቀል እምነት እሱና በጊዜያዊ አስተዳደሩ ውስጥ የነበሩ አብዛኞቹ ባለስልጣናት በኤርትራ፣ በኢትዮጵያ እና በአማራ ክልል መንግስታት ቅንጅት በትግራይ ህዝብ ላይ በደንብ ታቅዶ: የሚፈጸምበት የራሱ የእዝ ሰንሰለት ተዘርግቶ የዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈጽሟል።

ይህን ሁሉ ግፍ በነበረኝ ስልጣን ምክንያት አብሬያቸው ሆኜ ተመልክቻለሁ የሚለው ገብረመስቀል ጉዳዩን መመርመር የሚፈልጉ አካላት እርዳታዬን ከፈለጉ ለመተባበር ዝግጁ ነኝ ሲል ለሚዲያው ተናግሯል።

ማለዳ ሚዲያ
Please wait, video is loading...