እጅግ ያማል!!
By Afar People's Voice - APV
አስቸኳይ መልእክት ለሚመለከተው ሁሉ
----------->>#Share_ያድርጉት!!
____________________
በዛሬው እለት መነሻቸው ከደሴ አቅጣጫ የሆኑ ሁለት የጭነት መኪናዎች ወይን አይሱዙዎች በደቡብ ወሎ ዞን ከለላ ወረዳ ከልጓማ ከፍ ብሎ #ካራላፍቱ በሚባል ኬላ ላይ በአካባቢው ሚሊሻዎችና ወጣቶች በቁጥጥር ስር ውለው ነበር ። በቁጥጥር ውስጥ ሲውሉም የተለያዩ በኮድ ብቻ ሊፈቱ የሚችሉ ካዝናዎች ኮምፒዩተሮች የተለያዩ ዶክመንቶችንና ሌሎች ቁሳቁሶችን ይዘው ነበር።
የመኪናዎቹ አሽከርካሪዎች ፖሊስ ካልመጣ አናስረክብም ብለው እምቢ ብለው ነበረ። በመሆኑም ፖሊሶች መጥተው ሲፈትሹ የተከሰተው ነገር ግን ህዝቡን ያስቆጣና ከፍተኛ ጥርጣሬ ውስጥ የከተተ ሆኗል።
ፖሊሶቹ መሳሪያቸውን በተጠርጣሪው መኪና ላይ ላሉት ሰዎች ሰጥተው ለፍተሻ መግባታቸው ህዝቡን አስቆጥቷቷል ። እናም ፖሊሶቹ መኪናዎቹ በልጓማ ፖሊስ ጣቢያ ይገባሉ በማለት መኪናውቹ ከህብረተሰቡ እንዲያመልጡ አድርገዋል።
ይህን አደገኛ የሆነ የፖሊሶች አካሔድ በአፋጣኝ የሚመለከተው አካል ማጣራት እንዲያደርግና ፖሊሶችን በቁጥጥር እንዲያውል እንጠይቃለን።
የአንደኛው መኪና የታርጋ ቁጥር #ET80300 መሆኑን ማሳወቅ እንወዳለን!!
እነዚህን መኪናዎችና ከነርሱ ጋር የተባበሩትን ፖሊሶች የፀጥታው ሀይል በተለይም የከለላ ወረዳ የፀጥታ ተከታትሎ በቁጥጥር ስር ያድርግ አስፈላጊውን እርምጃ ይውሰድ
ይህ ከታች ያለው ለአብነት ከተያዘው ካዝና ውስጥ ነው።
Please wait, video is loading...