=>ላለፉት ሶስት አመታት ከተለያዩ የብልጽግና አመራርና ካድሬዎች ጋር በተለይ ደግሞ #ከኦዴፓ (የኦሮምያ ብልጽግናዎች) ሳደርጋቸው በነበረው ሙግት ዋነኛ ሀሳቤ "ከህወሀት ጋር እየተደረገ ያለ ትግልም፣ጥላቻም የለም፣ብልጽግና ብሎ የተሰባሰበው ቡድን ዋነኛ ኢላማው #የትግራይ_ህዝብ ነው።ምክንያቱ ደግሞ ፌደራሊዝምና ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች የሚለው አስተሳሰብ የኛ ጸር ነው፣የትግራይ ህዝብ እስካልጠፋ ህወሀት አይጠፋም፣ህወሀት ካልጠፋ ደግሞ ይህ አስተሳሰብ አይጠፋም ስለዚህ የትግራይን ህዝብ እናጥፋ የሚለው ከአመታት በፊት #በመለስ_ዜናዊ የተተነተነው ዳግማዊ #ኢንተርሀምዌ ነው፣ዘጠና አምስት ለአምስት፣አሳውን ለማጥፋት ውሀውን ማጥፋት የሚለው የአማራ ኤሊት ከሻብያ አመራሮች ጋር በጋራ የያዙት አቋም ነው፣መሪው #አብይ_አህመድ በገዛ እግሩ ያልቆመ የአማራ ኤሊትና የአዴፓ ሙሰኞች ተላላኪ ነው ወዘተ የሚል ነበር።ያው የካድሬና የጭፍን ደጋፊ ነገር የጨለማ ሯጭ ነውና አይኔን ግንባር ያድርገው ብለው ሀሳቤን ሲሞግቱ እዚህ ደረስን።
=>ባለፈው ሳምንት የአማራ ኤሊቶችና ክራይ ሰብሳቢዎቻቸው አግልጋይ የሆነው #አገኘሁ_ተሻገር ለታማኝ በላከው ግልጽ መልእክት የዚህ ሀይል አሰላለፍና አላማ ወገግ ያለላቸው ከፍተኛ የኦሮምያ ብልጽግና አመራሮች በማጉረምረም ቆይተው ነበር።
ትናንትና በግልጽና በማያሻማ ቋንቋ #የትግራይ ህዝብ_ጠላታችን ነው፣የብሄር ብሄረሰቦች ጠላት ነው፣ይህ ጠላት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ሳይጠፋ እረፍት የለንም የሚለውን መግለጫ ከተናገረ በኋላ አብይ አህመድ ወትሮ የሚፎክርባቸውና የሚደሰኩርባቸው ሚድያዎች በጠቅላላ የማን ልሳናት እንደሆኑ፣አላማቸውስ ምን እንደሆነ በግልጽ አይተዋል፣ሰምተዋል።
ይህ ከተሰማ በኋላ ሲሟገቱኝ የነበሩ ካድሬዎችና አመራሮች ራሳቸው የመለሱልኝ ምላሽ ቢረፍድም ከእንቅልፋቸው እንደባነኑ አሳይቶኛል።
አብይ አዋረደን፣በእርግጥ አብይ አሽከር መሆኑን ተረዳን፣ሚዲያዎች የነፍጠኛው ልሳን ሆነዋል፣ብልጽግና አብቅቶላታል፣አንተ እንዴት ሁሉን ቀድመህ አወህ??? አሁን አገራችን ወደለየለት መተላለቅና ስትነግረን ወደነበረው የእርስ በርስ ፍጅት ውስጥ እንደምንገባ ተረዳን፣በትግራይም ይሁን በህወሀት ላይ ለሰራነው ክህደትና ግፍ ሰማይም ምድርም ይፈርዱብናል ወዘተ የሚል ምላሽ ሰጥተውኛል።አንዳንዶቹ በስደት ጉዞ ላይ ስለሆኑ እግራቸው ከአገር እንደወጣ ንግግራችንን እለጥፈዋለሁ።
=>የአገኘሁ ተሻገር ንግግር የራሱ ሀሳብ ነው፣ህዝብ ሲል ማለት የፈለገው ጁንታውን ነው፣የአፍ ወለምታ ነው ገለመሌ በሚል የአሀዳዊው ልሳኖች፣ብልጽግና የሚያዝባቸው ሚድያዎች ይህንን ጉድ ለመሸፈን ርብርብ ቢያደርጉም የእውነትነቱ ግዝፈት የነሱን መቀባጠር ድምጥማጡን አጥፍቶታል።አሁን ላይ የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች የጦርነቱን ምክንያትና አላማ፣እነማን ምን ይዘው እንደተነሱና የጠቅላይ ሚኒስትሩን አሻንጉሊትነት በግልጽ ተረድተው ምላሽ በመስጠት ላይ ናቸው።ቢዘገይም ጥሩ እርምጃ ነው።የአሀዳዊው ቡድን ኢትዮጵያን ለእኩይ አላማው ለማፈራረስ ግማሽ መንገድ መድረሱንም አለም እያስተጋባ ነው።በዚህ ሰአት ሰላማዊ የሆነ ሽግግር ካልተደረገ በስተቀር ይህች አገር ወደማትወጣበት ድቅድቅ ጨለማ እየከነፈች ነው።ጋዜጠኞች፣ልሂቃንና ፖለቲከኞች እውነት እውነቷን ቦጭ አድርገው ስለተናገሩ አብይ አህመድና ጌቶቹ ባወጡት የንግግር አዋጅ ተቀፍድደው ዘብጥያ በወረዱባት ሀገር የአንድ ክልል መሪ ነኝ ባይ ህዝብን ጠላቴ ነውና ከምድረገጽ ማጥፋት አለብኝ ብሎ ምንም የማይሆንበት መድረክ የማን መጫወቻ እንደነበር ግልጽ ሆኗል።
አንድ ትልቅ እውነት፣ዘመናትን የተሻገረ መርህንግን ዘርን፣ህዝብን እናጠፋለን ብለው የተነሱ እንደ ኢትዮጵያ መንግስት በልመና የሚኖሩ ሳይሆን የአለምን ኢኮኖሚና የጦር ሀይል የሚዘውሩ ፋሽስቶች በሙሉ ጠፍተዋል፣ተዋርደዋል!!!
አሁንም በብዛት፣በኢኮኖሚ በስልጣንና በግሳንግስ ብዛት ሳይሆን #ትግራይ በመርህ፣በሀቅ፣በእውነት የታወጀባትን ጥፋትና ፍጅት አሸንፋና በጣጥሳ ትወጣለች!!!
የትግራይን ህዝብ እናጠፋለን እንፈጃለን ያሉት ግን ተረት ተረት ይሆናሉ!!! ይረሳሉ!!!
ህዝብ ይቀጥላል!!!
ትግራይ አሸንፋለች!!!
ብሄር ብሄረሰቦች ያሸንፋሉ!!!

https://www.facebook.com/netsa.yerase/p ... 8522471460