Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Noble Amhara
Senior Member
Posts: 13728
Joined: 02 Feb 2020, 13:00
Location: Abysinnia

General

Post by Noble Amhara » 24 Jul 2021, 19:23

Please wait, video is loading...
ʺአሸባሪውን የትህነግ ቡድን ከምድረ ገፅ ማጥፋት አለብን" ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ
የአማራ ልዩ ኃይል አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ በመግለጫቸውም የአሸባሪው ትህነግ ተቀዳሚ ዓላማ ኢትዮጵያን ማፍረስ ነው ብለዋል።

አሸባሪው ትህነግ በአማራና አፋር ክልል ጦርነት በመጀመር ሌላውን ኢትዮጵያዊ ሊያጠቃ ትንኮሳ እየፈጸመ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ሁሉም ኢትዮጵያዊ የአሸባሪው ቡድን ኢትዮጵያን የማፍረስ እኩይ ሴራ በመረዳት በህልውና ዘመቻው ላይ እንደሚገኝ አመላክተዋል። አሸባሪውን የትህነግ ቡድን ከምድረ ገፅ ማጥፋት አለብን ነው ያሉት፡፡

የአሸባሪ ቡድኑን የሐሰት ፕሮፓጋንዳና አሉባልታ የሚያናፍሱ በሕዝብ ውስጥ ያሉ ተላላኪዎችን ማኅበረሰቡ በንቃት ሊከታተል ይገባል ብለዋል ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ።

መንግሥት ያስተላለፈውን ጥሪ ተቀብሎ ሕዝቡ እያደረገ ያለውን ድጋፍ አድንቀዋል። ትግሉን ወጣቱ በጉልበቱ፣ ሕዝቡና ባለሃብቱ በሎጅስቲክ ሊያግዙ እንደሚገባም ገልጸዋል፡፡ ድጋፉ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ነው የጠየቁት፡፡

የጦር ልምድ ያላቸው መሪዎችና ተዋጊዎች ወደ ልዩ ኃይል እየተቀላቀሉ መሆኑንም አስታውቀዋል።

የትግራይ ሕዝብ ቆም ብሎ ሊያስብ ይገባል ያሉት ብርጋዴር ጄኔራሉ ዛሬ እየሆነ ያለው ጊዜያዊ ነው፤ ዘላቂ ወንድሙ ግን የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው ብለዋል።

አሸባሪው ትህነግ ሕጻናትን ወደ እሳት እየማገደ መሆኑን የገለጹት አዛዡ የትግራይ ሕዝብ ልጆቹን ከዚህ ውድመት ማዳን እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

የአማራ ልዩ ኃይል ከሌሎች የጸጥታ ኃይሎች ጋር እየተናበበ በቅንጅት እየተዋጋ ስለመሆኑም አስታውቀዋል።

ለኢትዮጵያ ዘብ ቆመው አሸባሪውን ቡድን በግንባር በመፋለም ላይ ላሉ የጸጥታ ኃይሎች ምስጋና አቅርበዋል።

#አሚኮ


Solomon Alula knows TDF suffered major losses many juntas are now in body bags after failed advances into Amhara and Afar Region 😂😂

tarik
Senior Member+
Posts: 37206
Joined: 26 Feb 2016, 13:04

Re: General

Post by tarik » 24 Jul 2021, 19:35


Post Reply