የኢትዮጵያ የተለያዩ ክልል መንግሥታት፣ ወልቃይትን ሰበብ አድርጎ በትግራይ ላይ የሚደረገውን ጦርነት፣
ቢቻል ለማስቆም፣ ግጭቱንም በሰላማዊ መንገድ በዘላቂነት እንዲፈታ ለማግባባትና ለማሸማገል ጥረት ማድረግ ሲጠበቅባቸው፣ ጭራሽ በአብይ ቀስቃሽነት፣ ለአንዱ ወግነው ሌላውን ለመውጋት ልዩ ኅይልና ሚሊሺያ ማዋጣታቸው፣ በሕግም፣ በታሪክም የሚያስጠይቃቸው አሳፋሪ ድርጊት ነው።
በዚህ የክህደትና የአገር ማፍረስ የወንጀል ጦርነት የሚሳተፉ የሚሊሽያና የልዩ ኃይል አባላት፣ ለማይገባ ዓላማ (ለከንቱ የእብሪት ጦርነት) ሕይወታቸውን ለጥፋትና ለሞት እያጋለጡ መሆኑን ሊገነዘቡ ይገባል።
ፍፃሜውና ውጤቱም ሽንፈት፣ ጥፋት፣ እና ግዞት ለሆነ ጦርነት እራሳቸውን ደመ-ከልብ ከማድረግ ቢቆጠቡ መልካም ነው።
በተለይ የኦሮሞና የሌሎች ጭቁን ሕዝቦች ልጆች፣ በማይመለከታቸው የተስፋፊዎች ጸረ-ሕዝብ ጦርነት ከመሳተፍ እንዲቆጠቡ ይመከራሉ። አንመከርም ብለው ከገቡበትም፣ ለሚደርስባቸው፣ ሞት፣ ጥፋትና፣ እንግልት ተጠያቂነቱ የእራሳቸው ብቻ እንደሆነ ሊረዱት ይገባል።
በኦሮሞ ሕዝብ ሥም፣ በሌሎች ሕዝቦች ለይ የሚደረግን ማንኛውንም የጥፋት ዘመቻ እንቃወማለን።
በሃሳብ ከተሸነፈ ብዙ አስርት ዓመታትን ላስቆጠረና በተግባርም በመሬት ላይ በተጨባጭ እየተሸነፈ ላለ ዓላማ መሰዋት፣ ደመ-ከልብነት ነው።
#Not_in_our_name!
#No_2_war_on_peoples!
Please wait, video is loading...