Brook Abegaz እንደፃፈው
ጁንታው ሰሞኑን ላንድ ክሩዘር መኪና ቀለም ሲቀባ ከርሞ ከጎኑ የአማራ ክልል ፖሊስ የሚል ጽሁፍ ጽፎ ታርጋም አዘጋጅቶ እዩኝ ማረኩኝ በማለት ፎቶ በፎቶ ሆኗል። ህፃናት ተዋጊወችን ለወሬ ነጋሪ ሳይቀር በገፍ አስደምስሶ የፈረጠጠ ቡድን መኪና የሚማርክበት ምትሀታዊ ሀይል ይኖረዋል ብሎ የሚያስብ ሰው ካለ ሊታለል ይችላል ። ጁንታ ለማያውቅሽ ታጠኝ እባክሽ ፤ እኛ እንደሆን ጥንቅቅ አድርገን እናውቅሻለን!!
ከሰሞኑ 9 ሺህ ሠራዊት ማረክን ብለው የትግራይ ወጣቶችን ሬንጀር በማልበስ የምርኮ የጎዳና ላይ ትያትር ከሰሩ በኋላ ዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ማህበር የምርኮወቹን ስም ዝርዝር አምጡ ሲል 500 ብቻ ነው የማረክነው ብለው ስም ሰጡ። ጁንታው ትልቅ ትከረት አድርጎ እየተንቀሳቀሰ ያለው ከጦር ሜዳ ጦርነት ይልቅ ፕሮፖጋንዳ ላይ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት የትግራይን ሕዝብ በስነልቦና ማሸነፍና ማሰለፍ፣ ዓለም አቀፉን ማህበረሰብ ማታለል፣ ድጋፍ ማግኘት እና ማሳዘን እንዲሁም የቀሪውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ስነልቦና መስለብ ላይ አበክረው እየሰሩ ይገኛሉ።
ጁንታው ለፕሮፖጋንዳ ቪዲዮና ፎቶ ብቻ የራሱን ሰወች ሰብስቦ እየረሸነ ቪዲዮ ሊቀርጽ ይችላል፣ የመኪና ቀለም ቀይሮና ሌላ አስመስሎ ታርጋ አዘጋጅቶ ማረክን ከማለት በላይ ለፕሮፖጋንዳ ሲባል በእጃቸው ያለ መኪናን ሊያቃጥሉ ይችላሉ (በነገራችን ላይ አብዛኛውን የመኪና ታርጋዎች የሚያመርተው መስፍን ኢንጂነሪንግ መቀሌ ነበር፡፡ የመኪናውን ቀለምና ጽሑፍ ደግሞ በርሄ ጋራዥ በአንድ ሰዐት ውስጥ መቀባት ይችላል
የትግራይ ሴቶችን ራሳቸው በተጠና እና ስልታዊ በሆነ መንገድ እየደፈሩ ነገር ግን የኤርትራና የኢትዮጲያ ሠራዊት ሴቶችን ደፈረ በማለት ለዓለምአቀፉ ማህበረሰብ ለቅሶ እና እሮሮ በማቅረብ ስኬት አግኝተውበታል። የህወሓት እስትንፋስ ፕሮፖጋንዳ ነው!! ትናንትና ጀነራል ባጫ ደበሌን ማረክን ፣ ጀነራል አበባውን ገደልን ብለው የመቐለን ህዝብ በባዶ ድል በደረቁ ሲያስጨፍሩ የነበሩ ሰወች አሁን ምንስ ቢሉ ማነው የሚሰማው?