Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Za-Ilmaknun
Member
Posts: 4487
Joined: 15 Jun 2018, 17:40

የ ኦሮሞው ተወላጅ አምባሳደር ሱለይማን ደደፎ ወልቃዪት ብሎ ትግራይ የለም ብለዋል!

Post by Za-Ilmaknun » 12 Jul 2021, 02:22

ወልቃይት ጎንደር መሆኑን የማያውቅ ካለ የኢትዮጵያን ጂኦግራፊ የማያውቅ ብቻ ነው!
***
በዩናይትድ አረብ ኢምሬትስ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት ክቡር አምባሳደር Suleiman Dedefo በወልቃይት ጉዳይ በኦፊሻል የቲዊተር ገፃቸው የሚከተለውን ታሪካዊ ምስክርነት ሰጥተዋል፤
***
“ሰቲት ሑመራ፣ ጠለምትና ጠገዴን የሚያጠቃልለው ወልቃይት ተብሎ የሚታወቀው አካባቢ በ1984 ዓ.ም በኃይል ወደ ትግራይ ከመጠቃለሉ በፊት የበጌምድርና ጎንደር አካል መሆኑን ስንማር ነው ያደግነው።

እደግመዋለሁ! ወያኔ አሁን ምዕራብ ትግራይ እያለች የምትጠራቸው ፥ ከበጌምድር የጠቀለለቻቸው አካባቢዎችን በሀይል የወሰደችው ነፃይቱን የትግራይ ሪፕብሊክ ስትመሰርት ወደ ሱዳንን የሚያስዎጣት ኮሪደር እንዲኖራት አለም አቀፍ ድንበር ለማኘት ነው።

እነዚህን አካባቢዎች የሚፈልገው ለእርሻ ብቻ ሳይሆን ከውጭው ዓለም ጋር ለመገናኘት እንዲያመቸው ጭምር እው። እነዚህ አካባቢዎች የበጌምድር አካባቢዎች መሆናቸውን የማያውቅ ካለ የኢትዮጵያን ጂኦግራፊ የማያውቅ ብቻ ነው።”

ክቡር አምባሳደር አቶ ሱሌማን ዴዴፎ
***
ክቡር አምባሳደር ለሀቀኛና ታሪካዊ ምስክርነትዎ በህዝባችን ስም ከልብ እናመሰናለን! እንደ እርስዎ ያለ የአገሩን ታሪክና ዲሞግራፊ ጠንቅቆ የሚያውቅ ይህንንም በሀቀኝነት የሚመሰክር አምባሳደር እጅግ ወሳኝ በሆነው የመካከለኛው ምስራቅ ቀጠና በማግኘታችን የአገራችን እና የህዝባችን ጥቅም በአስተማማኝ እጅ ላይ እንዳለን ያረጋግጣል ለዚህም ኩራት ይሰማናል።

Tewodros Tadesse Belay