Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abe Abraham
Senior Member
Posts: 14414
Joined: 05 Jun 2013, 13:00

ሰክረታሪ ቴለፎንን ኣንስታ ደውላ መልስ እየጠበቀች ትዘፍናለች ፥ ዛሬ ነው ፡ ነገ ነው ፡ ሙሌቱን የማየው ....

Post by Abe Abraham » 05 Jul 2021, 18:06


ቦታ፥ የጠቅላይ ሚኒስተር ዶክተር ኣብዮት ሰክረታሪ ጽህፈት ቤት

ሰክረታሪ ቴለፎንን ኣንስታ ደውላ መልስ እየጠበቀች ትዘፍናለች ፥ ዛሬ ነው ፡ ነገ ነው ፡ ሙሌቱን የማየው ....

ከግብጽ ፥ ኣሉው ! ኣሉው ! ሚን ማዓያ ? ማን ልበል ?

ሰክረታሪዋ ፥ ኣስዩብያ ! ሲሲ ?

ግብጽ ፥ ኣዎ ሲሲ ነኝ ?

ሰክረታሪዋ ፥ እንዴት ነሽ ? ደህና ነሽ ?

ግብጽ ፥ ደህና ነኝ ። ኩሉ ተማም!!

ሰክረታሪዋ ፥ ስለ ሙሌት ልነግርሽ ነው ምድውለው

ግብጽ ፥ የምን ሙሌት

ሰክረታሪዋ ፥ የሰድ ኣል-ናህዳ ! የህዳሴ ግድብ ! የገርድ ! ሲሲየ ረሳሽው እንዴ ? ነገ ነው !!

ግብጽ፥ ለምን ኡሓዲ/ዩኒላተራል ኣደረጋችሁ ?

ሰክረታሪዋ ፥ ኣንቺ እኛን ለማስፈራራት ከሱዳን ጋር ወታደራዊ መናውራ ካደረግሽ ቡሃላ ወደ ኣራብ ሊግ ሄደሽ ማስፈራራትን ቀጠልሽ ከዚያም ወደ ኣል-ኡመም ኣል-ሙታሒዳ UN ሄደሽ የማጭበርበር ተግባርሽኝ ኣላቋረጥሽም ....እኛ ወደ መሪኽ/ማርስ ጉዞ እስከሚታደርጊ ድረስ ልንጠብቅሽ ኣንችልም ። ኣቶ መሓመድ ኣል-ዓሩሲ እንዳሉት " የህዳሴ ግድቡ ሲሰራ ለጫወታና ለየምዩዝዮም እቃ ሊሆን ሳይሆን ሊሞላ ነው " ። ኣይዞሽ የሚጠጣ ውሃ ኣንከለክልሽም ። ከመጣሽ ነገ በግድቡ እጠብቅሻለሁ ። ግድቡ ውሃውና ተፈጥሮው ልብ የሚማርክ ስለሆነ ስታይው ደስ ይልሻል ። ባይ ! ያ ሓቢብቲ ! የምወድሽ ጓደኛየ !! ለዑስማን ኣል-በዋብ ( ህንጻ ጠባቂ ብለሽ ለምትሰድቢው ጥቁር ሱዳናዊ ) ሰላም በልልኝ ። ለመርየም ኣል-ማህዲ ደሞ ሳምልኝ ።

ግብጽ፥ ነገ ለስራ ስሄድ መታጠብ እችላለሁ ?

ሰክረታሪዋ ፥ እስከዛ ድረስ ኣላስቸግርሽም ። ኪስ ! ኪስ ! ኪስ !!