Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 42716
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

በምርጫ ማግስት ብልጽግና የገባበት ፈተናና የብርቱካን መደቅሳ ወሳኝነት ፣ ዛሬ ጁላይ 2 አቢይ አህመድ እጅግ ብልህ መሪነቱን አሳይቷል! በቃ ዬቦ

Post by Horus » 25 Jun 2021, 18:42

እኔ ሆረስ ነኝ፣ ቃላት መፍለጥ አይመቸኝም።

እጅግ ግዙፉና ብዙ አቢይን የሚያስከፍለው እርምጃ፣ ያለ የሌለ የመንግስት ሃይል አንቀሳቅሶ ባልተመዛዘነ ውድድር ብቸኛ አሸናፊ ሆኖ መውጣቱ እና ያንድ ፓርቲ ፓርላማና መንግስት ሊሆን መዘጋጀቱ እግጅ ግዙፉ ያቢይ ስህተት ብቻ ሳይሆን ወደ ትልቅ ቀውስ እንደ ሚወስደን ምንም ጥርጥር የለውም ። አቢይ በግድ፣ በግድ መንግስቱን ሰፋ ባለ መሰረት ላይ ማቆም አለበት ባስቸኳይ ።

አሁን በአቢይ መንግስት ላይ ሶስት (3) የሃይል አሰላለፎች በቅዋሜ ተነስተው ፋታ ይነሱታል፤ (1) ኢትዮጵያን ከውጭና ከውስጥ ጠላት ተከላክለው አቢይን የደገፉት ተወዳዳሪዎች ማለትም ቢያንስ ፓርላማ ውስት ሳይወከሉ የቀሩት ብልጽግናን ወደ መቃወም እየሄዱ ነው ። (2) የትግሬ፣ ኦነግና ሌሎች ንቅናቄና ሁከት እየጠነከረ እንጂ እየደከመ አልሄደም ። (3) ምዕራብ አሁንም የተባበረ ግፊቱን አላቆመም ።

በአንድ ቃል የአቢይ መንግስት በአገር ጠባቂነት እና ያርበኛ መንግስትነት ተጠናክሮ መውጣትና እጅግ ግዙፍ ቀውስና መበታተንን ማስወገድ ከፈለገ የምርጫው ዉጤት ምንም ሆነ ምን መንግስቱን አስፍቶ የኢትዮጵያ ጠላቶችን ለመቋቋም በርከት ካሉት ተፎካካሪና ተቃዋሚ ሃይሎች ቢያንስ የፓርላማው 20% የሚሆኑ ወንበሮች ለነሱ ሰጥቶ ያገር አንድነት መንግስት ማቆም አለበት በፊታችን መስከረም ማለት ነው ።

ይህን ካላደረገ ብልጽኛ የተነጠለ አይሶሌትድ የሆነ መንግስት ሆኖ ወደ ልማት ሳይሆን ወደ ብዙ አይነት ጦርነትና ፉክቻ ወስጥ ገብቶ ተንገጫግጮ ይቆማል፣ አቢይም ከልማት አላማው ይወጣል ። ጠባብ መንግስት እንደ ሸክላ ተሰባሪ ነው ። ልድገመው፣ መሰረቱ ጠባብ መንግስት እንደ ሸክላ ተሰባሪ ነው።

የኢትዮጵያ ቁልፍ ችግር ምርጫ ማድረግ አይደለም ፣ መሰረቱ የሰፋ፣ ሊቆም የሚችል መንግስት ማቋቋም ነው ። ስለሆነም አቢይ የምርጫው ዉጤት ምንም ይሁን ምን ከብልጽ ግ ና ሌላ እስከ 20% ወይም 25% የተለየ ሃሳብና አመለካከት ያላቸው የፓራላማ አባልት ማስገቢያ መንገድ ዛሬውኑ መፍጠር አለበት ።

ምርጫው ጥሩ ልምምድ ነበር ፣ ግን ያቢይን ችግር አልፈታለትም! ያንድ ፓርቲ አምባ ገነን ከመሆን የሚገላግለው መንገድ ማምጣት አለበት ። ያ ነው ሪያሊቲው! ያ ነው መፈታት ያለበት ችግር !!

ይህ ሁሉ እንዲሆን የብርቱካን ድርጅት የምርጫው ቦርድ በጥልቀት ማሰብ አለበት ። ይህ ሁሉ ልፋትኮ በመጨረሻ የተረጋጋ ጠንካራ መንግስት ለማምጣት እንጂ የግብር ይውጣ ድምጽ መቁጠር አይደለም ። የምርጫው መጨረሻ ግብ ምንድን ነው? ይህ ነው፣ መሰረቱ የሰፋ መንግስት ለማቆም ነው ! ያ ነው እውነተኛው የምርጫው ፐርፐዝና ትርግሩምና ፋይዳ !!!

ሆረስ አይነ ኩሉ

ዛሬ ጁላይ 2

በቃ አሁን አቢይ አህመድ እጅግ ወሳኝ እጅግ ብልህ እጅግ ጥልቅ ዉሳኔ አደረገ !! ይህ ነው የፖለቲካ መሪነት ማለት !!! ዬቦ ኤቦ !! ይህ ነው የኢትዮጵያን ጠላቶች የምያሳፍር እውቀት !! የሽግግር መንግስት አንፈልግም። የምንፈልገው የህዝባችን አንድነጥ የፓርቲዎች አንድነት ነው !! በቃ አከተመ !! አቢይ አህመድ መሪነቱን አረጋግጧል !!!

Last edited by Horus on 02 Jul 2021, 16:27, edited 5 times in total.

Wedi
Member+
Posts: 8649
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

Re: በምርጫ ማግስት ብልጽግና የገባበት ፈተናና የብርቱካን መደቅሳ ወሳኝነት

Post by Wedi » 25 Jun 2021, 20:39

Horus wrote:
25 Jun 2021, 18:42
ስለሆነም አቢይ የምርጫው ዉጤት ምንም ይሁን ምን ከብልጽ ግ ና ሌላ እስከ 20% ወይም 25% የተለየ ሃሳብና አመለካከት ያላቸው የፓራላማ አባልት ማስገቢያ መንገድ ዛሬውኑ መፍጠር አለበት ።
አይ Horus 20% ምናም ትላለህ አይደል!! አብይ አህመድ እጅግ አሳፍሪ የሆነ ሰው ነው!! ምን እየሰራ ነው ወያኔ ትግራይን በሙሉ እስኪቆጣጠረው? እጅግ ያሳፍራል!!
ስንት መሰዋትነት የተከፈለበትን ትግል መጫወቻ አድረገው!!

አብይ አልቆለታል!! ተስፋ ቁረት!!
:lol: :lol:

Horus
Senior Member+
Posts: 42716
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: በምርጫ ማግስት ብልጽግና የገባበት ፈተናና የብርቱካን መደቅሳ ወሳኝነት

Post by Horus » 25 Jun 2021, 21:10

ወዲ፣
ኢትዮጵያ እንደ ትግሬ ሽብር የሰለቸው ነገር የለም ። ያሻህን ያክል ተዋጋና ሲደክምህ ታቆማለህ! በኢትዮጵያ 86 ጎሳዎች አሉ ። ከሁለቱ ትላልቆቹ አማርና ኦሮሞ ጋር እየተዋጋህ ነው ። 83 መንግስታቸውን ይደግፋሉ። ይህን ነገር አታሸንፍም ። ለ30 አመት ያከማቸሀው ሃብትና ሃይል በከንቱ እያባከንክ ነው። ወያኔ አዲስ አበባ እስካለም ፍጻሜ አይመለስም ። አሁን ጦርነቱ በትግሬና ትግሬ መሃል ነው ። ድሮ ድሮ ይህን ነግሬህ ነበር ። ብቻ አንድ ነገር እወቅ ! Ethiopians are in a total Tigre fatigue እጅግ በጣም የሰለቸን ነገር ስለትግሬ ሽብርና ቀውስ መስማት ነው! አሁን ከህሊናህ ጋር ብቻ ነው ምትመካከር! በቃ!

Wedi
Member+
Posts: 8649
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

Re: በምርጫ ማግስት ብልጽግና የገባበት ፈተናና የብርቱካን መደቅሳ ወሳኝነት

Post by Wedi » 25 Jun 2021, 21:56

Horus wrote:
25 Jun 2021, 21:10
ወዲ፣
ኢትዮጵያ እንደ ትግሬ ሽብር የሰለቸው ነገር የለም ። ያሻህን ያክል ተዋጋና ሲደክምህ ታቆማለህ! በኢትዮጵያ 86 ጎሳዎች አሉ ። ከሁለቱ ትላልቆቹ አማርና ኦሮሞ ጋር እየተዋጋህ ነው ። 83 መንግስታቸውን ይደግፋሉ። ይህን ነገር አታሸንፍም ። ለ30 አመት ያከማቸሀው ሃብትና ሃይል በከንቱ እያባከንክ ነው። ወያኔ አዲስ አበባ እስካለም ፍጻሜ አይመለስም ። አሁን ጦርነቱ በትግሬና ትግሬ መሃል ነው ። ድሮ ድሮ ይህን ነግሬህ ነበር ። ብቻ አንድ ነገር እወቅ ! Ethiopians are in a total Tigre fatigue እጅግ በጣም የሰለቸን ነገር ስለትግሬ ሽብርና ቀውስ መስማት ነው! አሁን ከህሊናህ ጋር ብቻ ነው ምትመካከር! በቃ!
Horus ዝንተም ብዙ የምታውቀው ታሪክ ቢሆንም ትግሬዎች ከድሮ ጀምሮ በኢትዮጵያ ላይ ሲሰሩት የኖሩትን እና አሁንም እየሰሩት ያለውን አሳፋሪ ስራ ስዮም ተሾመ በዚህ መልክ ጥሩ አድርጎ አዘጋጅቶታል አዳምጠው፡፡ Aethiopica 2002 የሚለውን አርቲክልም ጎግል ላይ ፈልገህ አንብበው!!

DefendTheTruth
Senior Member
Posts: 13227
Joined: 08 Mar 2014, 16:32

Re: በምርጫ ማግስት ብልጽግና የገባበት ፈተናና የብርቱካን መደቅሳ ወሳኝነት

Post by DefendTheTruth » 26 Jun 2021, 05:28

Horus wrote:
25 Jun 2021, 18:42
እኔ ሆረስ ነኝ፣ ቃላት መፍለጥ አይመቸኝም።

እጅግ ግዙፉና ብዙ አቢይን የሚያስከፍለው እርምጃ፣ ያለ የሌለ የመንግስት ሃይል አንቀሳቅሶ ባልተመዛዘነ ውድድር ብቸኛ አሸናፊ ሆኖ መውጣቱ እና ያንድ ፓርቲ ፓርላማና መንግስት ሊሆን መዘጋጀቱ እግጅ ግዙፉ ያቢይ ስህተት ብቻ ሳይሆን ወደ ትልቅ ቀውስ እንደ ሚወስደን ምንም ጥርጥር የለውም ። አቢይ በግድ፣ በግድ መንግስቱን ሰፋ ባለ መሰረት ላይ ማቆም አለበት ባስቸኳይ ።

አሁን በአቢይ መንግስት ላይ ሶስት (3) የሃይል አሰላለፎች በቅዋሜ ተነስተው ፋታ ይነሱታል፤ (1) ኢትዮጵያን ከውጭና ከውስጥ ጠላት ተከላክለው አቢይን የደገፉት ተወዳዳሪዎች ማለትም ቢያንስ ፓርላማ ውስት ሳይወከሉ የቀሩት ብልጽግናን ወደ መቃወም እየሄዱ ነው ። (2) የትግሬ፣ ኦነግና ሌሎች ንቅናቄና ሁከት እየጠነከረ እንጂ እየደከመ አልሄደም ። (3) ምዕራብ አሁንም የተባበረ ግፊቱን አላቆመም ።

በአንድ ቃል የአቢይ መንግስት በአገር ጠባቂነት እና ያርበኛ መንግስትነት ተጠናክሮ መውጣትና እጅግ ግዙፍ ቀውስና መበታተንን ማስወገድ ከፈለገ የምርጫው ዉጤት ምንም ሆነ ምን መንግስቱን አስፍቶ የኢትዮጵያ ጠላቶችን ለመቋቋም በርከት ካሉት ተፎካካሪና ተቃዋሚ ሃይሎች ቢያንስ የፓርላማው 20% የሚሆኑ ወንበሮች ለነሱ ሰጥቶ ያገር አንድነት መንግስት ማቆም አለበት በፊታችን መስከረም ማለት ነው ።

ይህን ካላደረገ ብልጽኛ የተነጠለ አይሶሌትድ የሆነ መንግስት ሆኖ ወደ ልማት ሳይሆን ወደ ብዙ አይነት ጦርነትና ፉክቻ ወስጥ ገብቶ ተንገጫግጮ ይቆማል፣ አቢይም ከልማት አላማው ይወጣል ። ጠባብ መንግስት እንደ ሸክላ ተሰባሪ ነው ። ልድገመው፣ መሰረቱ ጠባብ መንግስት እንደ ሸክላ ተሰባሪ ነው።

የኢትዮጵያ ቁልፍ ችግር ምርጫ ማድረግ አይደለም ፣ መሰረቱ የሰፋ፣ ሊቆም የሚችል መንግስት ማቋቋም ነው ። ስለሆነም አቢይ የምርጫው ዉጤት ምንም ይሁን ምን ከብልጽ ግ ና ሌላ እስከ 20% ወይም 25% የተለየ ሃሳብና አመለካከት ያላቸው የፓራላማ አባልት ማስገቢያ መንገድ ዛሬውኑ መፍጠር አለበት ።

ምርጫው ጥሩ ልምምድ ነበር ፣ ግን ያቢይን ችግር አልፈታለትም! ያንድ ፓርቲ አምባ ገነን ከመሆን የሚገላግለው መንገድ ማምጣት አለበት ። ያ ነው ሪያሊቲው! ያ ነው መፈታት ያለበት ችግር !!

ይህ ሁሉ እንዲሆን የብርቱካን ድርጅት የምርጫው ቦርድ በጥልቀት ማሰብ አለበት ። ይህ ሁሉ ልፋትኮ በመጨረሻ የተረጋጋ ጠንካራ መንግስት ለማምጣት እንጂ የግብር ይውጣ ድምጽ መቁጠር አይደለም ። የምርጫው መጨረሻ ግብ ምንድን ነው? ይህ ነው፣ መሰረቱ የሰፋ መንግስት ለማቆም ነው ! ያ ነው እውነተኛው የምርጫው ፐርፐዝና ትርግሩምና ፋይዳ !!!

ሆረስ አይነ ኩሉ
Back to square one, the same old demand that was defeated repeatedly, and the demand is called "install a transitional government", which can only be realised by a means of suspending the country's constitution. The answer is simple and the same: we are tired of "transition".

You can't have it both ways, you were braging about your party shaking the ground during the pre-election campaign but then failed to garner enough votes to entitle it to enter the national parliament and after this failure come back again, shamelessly, to demand, okay, I failed, but still you have to allow me enter the parliament. But on what bases? Who should select those to be allowed into?

This is an insult to the peace loving and patriotic Ethiopians, who braved many challenges and went out to vote in mass who they wish to administer their affairs.

We told many times that:

1. The constitution could be bad (imperfect) but still we have to agree to disagree on certain principles and that principles are provided by the constitution, which you can amend, or even replace after you have the mandate to do so.

2. The road to power should be only one and one, which is through the representational mandate of the populace, else no one else is entitled to allow a different party to come in and mess with the affairs of the people.

3. Abiy Ahmed has no mandate, what so ever, to select a representative for any sector of the Ethiopian people, he can only arrange the means that anybody get selected to the parliament by institutionalizing the an independent election process. You yourself argued that this was the case and now demanding a the other way is your misserable failure not that of the Election Board or the incumbent party.

Go search the reason why you failed and try to correct your failure instead of trying to impose your wish on the free people of Ethiopia.

We voted, now we demand that the will of the voters be respected, else it will be a total chaos.

Respect and Protect the Will of The People!

Horus
Senior Member+
Posts: 42716
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: በምርጫ ማግስት ብልጽግና የገባበት ፈተናና የብርቱካን መደቅሳ ወሳኝነት

Post by Horus » 26 Jun 2021, 10:38

DDT
ፖለቲካ የምታቅ ሰው መስለሀኝ ነበር! አታቅም ማለት ነው ። ከዚህ ሃረግ በታችህ temari post ያደረገውን የህዝብ አስተያየት ስማ። ቃል በቃል ላለፈው 3 ቀን ስጽፈው የነበእውን ነው ሚነግሩህ ። ተቃዋሚዎች ድምጽ ያላገኙት እነሱም መንግስት የመለወጥ አላማ አልነበራቸውም፣ ህዝቡም ያለው መንግስት አተንክሮ ሰላም ለማግኘት እንጂ አዲስ መንግስት የማቆም አላማ አልነበረውም ። አሁንም ቢሆን ህዝቡ ምን አለ መሰልህ ? አቢይ አካታች ኢንክሉሲቨ መንግስት ይሁን ነው ያሉጥ እዚህ ቪዲዮ ላይ ምጸማቸው ሰዎች ፖለቲካ ያስተምሩሃል። ግዚው ወስደህ አዳምጣቸው ። ስለ ኢዜማ መሸነፍ የጻፍኩትን በኋላ ወደ ላይ አማጣዋለሁ። ልብ አድርግ ፖለቲካን እንደ ሳይንስ የተማርኩትና ጥርሴን የነእልኩበት ነገር ነው።

ህዝቡን ስማ፡ ሶስት የምርጫ ጥያቄ ነው የነበረው፤ ሰላም፣ የኑሮ ወድነት (ኢንፍሌሽን እና ስራ አጥነት (ኢምፕሎይመንት) ። የኢዜማ ክሽፈት ምክኛት የሚዳሰስ የሚቀመስ የህዝብ ጥያቄ ስላልነበረው ነው ማሸነፍ ሳይሆን ድምጽ የተነፈገው! አበቃሁ ! አቢይ ሌሎችን ማካተት ያለበት ለራሱ ሲል እንጂ ለማንም አይደለም። ፖለቲካ አለማወቅክን አየሁት!

ይህን ስማ
viewtopic.php?f=2&t=262577

And, this is what I wrote on June 23rd. Compare it with the commentaries of the people in the above video!

ኢዜማ የረባ የፖለቲካ ተጽዕኖ ለመፍጠር ወደ 20% የሚጠጋ ወንበር እንደ ሚፈልግ አስልቼ ከ70 እስከ 100 ወንበር እንዲኖረው ማስፈለጉን ተስፋ አድርጌ ያለኝ አስፐሪሽን ከላይ ብያለሁ ። ይህ የኔ የግል አስፐሬሽን ነበር ። በመሬት ላይ አገር ቤት ያለው ሪያሊቲ ከኔ ምኞት የተለየ ሆነ ። በቃ ሌላ ነገር የለውም ። መሰረታዊ ትንተናዬ በዚያቅ ቀን ብዬዋለሁ ። ያስገረመኝ ነገር ቢኖር ሕዝቡ ድምጹን ይህን ያህል መንፈጉ እንጂ እኔ ኢዜማ አቢይን ያሸንፋል የሚል እምነትም ሃሳብም ኖሮኝ አላቅም ።

እኔ ሆረስ ነኝ፣ ቃል አልፈልጥም! የኢትዮጵያ 2013 ምርጫ ሙሉ ግምገማ ገና አልተደረገም። ነገር ግን በብዙ ብዙ መንገድ ይህ ምርጫ የኢትዮጵያን ፖለቲካ የሚለውጥ ስለሆነ በአንጎሌ ጫፍ ላይ ሳይሆን በልቤ ስር ጥልቅ ደስታ ተሰምቶኛል ። ለምን?

እኔ የማምንበት ነገር አለ፣ ቲኦሪ ሃሳብ ነው፣ ምናብ ነው። ያ ቲኦሪ የሚፈተነው በተግባር ነው ። ጥሩ ቲኦሪ ብቻውን ጥሩ ተግባር አይሆንም። ጥሩ ተግባር የራሱ ሕግ አለው ። እሱን የተግባር ፍልስፍና፣ ዘ ፊሎሶፊ ኦፍ አክሽን ወይም ሆነ ብለን የምናደገው ተግባር ፍልስፍና ይባላል።

ፖለቲካም እንዲሁ የተግባር ህግ አለው ። ላንድ ፖለቲካኛ የፖለቲካ ተግባሩ ቁልፍ ቁም ነገር ቁልጭ አግድርጎ በአንድ ቃል ለማስቀመጥ መቻል አለበት ።

የ2013 ምርጫ አላማ ምንድን ነው ለሚለው ቁጥር አንድ ጥያቄ እኔ ደግሜ ደግሜ እንዳልኩት የዚህ ምርጫ ግብ በሕዝቡ እይታና ፍላጎት አንድ ያለን መንግስት ለመለወጥ፣ አንድ ሪጂም ወይም አስተዳደር ካንዱ ቡድን ወደ ሌላ ቡድን ለመለወጥ አይደለም ብያለሁ ። የህዝቡ ፍላጎ በወያኔ ተሰባብሮ ተፍረክርኮ ያለውን መንግስት ማጠንከር፣ አገር አንድ አድርጎ ማጠንከር ነው የህዝቡ መሰረታዊ ጥያቄና ፍላጎት ።

ይህ ነው የዚህ ምርጫ ተግባር ፍልስፍና መቆሚያ ! ስለሆነም በምርጫው ከተካፈሉት ዋና ዋና ፓርቲዎች ስንቶቹ ይህን ፍልስፍና እንደሚገባቸው አላቅም ። ኢዜማ አንድም ግዜ በዚህ ምርጫ ሲወዳደር አላማው የአቢይን መንግስት አውርዶ ሌላ አዲስ የኢዜማ መንግስት ለማምጣት ነው ብሎ አያውቅም ። ስለዚህ ኢዜማ በዚህ ምርጫ የብልጽግና አጋር እንጂ ተቃራኒ አልነበረም ።

ይህ አቋም ትክክል ነበር ። ሕዝቡ ዛሬ የመሰከረው ያንን ነው ። ኢትዮጵያዊያን ዛሬ ያላቸው ፍላጎት ጠንካራ፣ ሰላም የሚያስጠብቅ፣ አገር የሚያስቀጥል መንግስት ማደራጀት እንጂ የአቢይን መንግስት አውርዶ አዲስ መንግስት ለመሆን አይደለም። ይህን የማያውቅ ፖለቲከኛ ወደ ሌላ ስራ መሄድ አለበት ።

ከሁሉም አስቀድሞ ህዝቡ ፖለቲከኞችን ያስተማረው ትምህርት ይህ ነው። እያንዳንዱ ምርጫ የዚያን ወቅት ግብና አጀንዳ አለው ፣ የዛሬ ምርጫ አጀንዳ ሰላም ማስፈን እንጂ መንግስት መለወጥ አይደለም ፤ የሆነውም ያ ነው ።

እነኢዜማ ፣ አብን ፣ ባልደራስ ፣ ምናምን ለምን የሕዝብ ድምጽ ተከለከሉ? ከላይ ብዬዋለሁ! የተሳሳተ የመሪዎች ቲኦሪ በትክክለኛ የህዝብ ተግባር ይታረማል ይባላል።
እኔ ላለፈው 30 አመት በኢትዮጵያ ከ4 ወይ 5 ፓርቲዎች በላይ መኖር የለባቸውውም ብያለሁ፤ አሁንም እላለሁ ። ዛሬ ህዝቡ የላከው ትምህርት ያ ነው። ወይ አንድ ሁኑ ወይ ወግዱ ነው ያለው ሕዝቡ ።

በኢትዮጵያ አንድ በጎሳ ቀመር የቆመ ፓርቲ አለ፣ እሱም ብልጽግና ነው ። በዜጋ ፖለቲካ ቀመር የሚቆሙ አንድ ሊብራል ፣አንድ ሶሺያል ዴሞክራሲ ፣አንድ ወግ አጥባቂ ፓርቲዎች ሊኖሩ ይችላሉ ። ሌላ አንድ አረንጓዴ ፓርቲ ሊኖር ይችላል። በቃ ከዚህ አልፈው በግለሰቦች ምኞትና ድንቁርና ላይ የቆሙ 50፣ 100 ፓርቲዎች በህዝብ እንደ ሚወገዱ ይህው አየን፣ አበቃ ! የፖለቲካ ፓርቲዎች የመንግስት አደራጅ እንጂ መንግስት እና አገር ማፍረሻ መሳሪያዎች አይደሉም ። ፓርቲ ድርጅት ነው፣ ድርጅት መሳሪያ ነው ።

ሶስተኛው፣ ኢዜማ ለምን ድምጽ ተነፈገ የሚለው ቀላል ጥያቄ ነው! ፈረንጆች ፖለቲካ የሰፈር ጨዋታ፣ የሰፈር ትግል ነው ይላሉ ። ይህም ማለት በዴሞክራሲ ውስጥ አንድ ግለሰብ ምረጡኝ ለማለት እሱ ወይም እሷ በዝርዝር ለዚያ ሰፈር፣ ለዚያ መራጭ ህዝብ ሊያደርግ፣ ምን ሊያሻሽል እንዳቀደ እና ያም ዝርዝር የሰፈር ግብ ከሌላው ፓርቲ ፕላን እንዴት እንደ ሚሻል በፋክት፣ በግልጽ ህዝቡን ማሳመን አለበት ።

ኢዜማ አንድም ቦታ ይህን ሲያደርግ አልታየም፣ ኢዜማ በፍልስፍና በዜጋ ፖለቲካ ንድፈ ነገር ከብልጽግና መለየቱ ቢታወቅም ሪቴይል ፖለቲካ ወይም የፖለቲካ ችርቻሮ የሚባለው ጭብጥ፣ የሚዳሰስ፣ የሚቀመስ ጥቅም ለህዝብ ስላላቀረበ ህዝቡ ድምጹን የሚስጥለት ምክንያት አልነበረም። ይህው ነው ሌላ ምስጢር የለውም ።

ስለሆነም ይህ ምርጫ የብዙሃኖች ጥበብ ወይም ዊዝደም ኦፍ ዘ ማስስ የተረጋገጠበት ልምድ ነው ። ይህ ማለት በተለይ ብልጽግናና ኢዜማ ግልጽ የሆነ የአጭር ግዜ ልዩነት ስለሌላቸው ፣ ፈረንጅ እንደ ሚለው ለአንድ ስራ ሁለት ሰው ከቀጠርክ አንዱን አባርር ፣ ሰዉ ብልህ፣ ብልጥ ስለሆነ ሰላምና ጸጥታ ላይ ያለውን ቡድን አጠናክሮ ጠንካራ አገር እና መንግስት እንዲኖር ድምጹን ለዚያ ሰጠ ። ይህ ነው ምስጢሩ !!

ኢዜማ አልተሸነፈም ፣ ያልጠየቀውን ሊሰጠው አይችልም ። የጎሳው ሲስተም፣ የጎሳው መዋቅር ላይ ኢዜማ ቦታ እንደሌለው ፣ኢዜማ ሊመራው ሊቆጣጠረው የሚችል እስትራክቸር እንዳልሆነ ከኢዜማ በላይ ህዝቡ አውቆ የተሳሳተውን ቲኦሪ አርሞላቸዋል ። ኢዜማ በኤትኖክራሲ ላይ ዴሞክራሲ ለተገብር አይችልም ። ኢጎሳዊ ሲስተም እስከሌለ ድረስ ኢዜማ መንግሳትዊ ስልጣን ልይዝ አይችልም ። ይህ የፖልቲካ ሕግ ነው።

የኢዜማ አላማና ስራ ኢጎሳዊ የሆነ የዜጎች ሲስተም መፍጠር ስለሆነ ወደዚያ ተግባሩ ይሄዳል ማለት ነው።

ይህ ምርጫ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች ህይወት ላንዴም ለሁሌም ይለውጣል የሚል እምነት አለኝ ። በሌላ ፖስት ላይ እንዳልኩት የዜጋ ፓርቲዎች ቢያንስ 20% ወንበር ካላገኙ የብልጽግና ማጣፈጫ ከመሆን ያለፈ ፋይዳ ስለማይኖራቸው ፓርላማ ከመቀመጥ አለመግባታቸው የተሻለው ነው። የዛሬ አምስት አመት 2 ወይም 3 አገር አቀፍ ፓርቲ ሆነው ይምጡ። እስከዚያ ኢትዮጵያ አባይን ትሙላ !! በቃ

DefendTheTruth
Senior Member
Posts: 13227
Joined: 08 Mar 2014, 16:32

Re: በምርጫ ማግስት ብልጽግና የገባበት ፈተናና የብርቱካን መደቅሳ ወሳኝነት

Post by DefendTheTruth » 26 Jun 2021, 14:40

Horse,

you always try to brag about yourself, it is all about your own self-insecurity. A true scholar is humble, among others.

This young man has got a message for you here.

[i][/i]

Horus
Senior Member+
Posts: 42716
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: በምርጫ ማግስት ብልጽግና የገባበት ፈተናና የብርቱካን መደቅሳ ወሳኝነት

Post by Horus » 26 Jun 2021, 14:52

ዲዲቲ

እግር እግር እየተከተልክ ስለእኔ እንድናገር ምታደርገኝ አንተው ነህ ። አንተ ስሜት፣ የምትወደውና የምትጠላው ነገር ነው ሚነዳህ! ለምን ፖለቲካ አታቅም እንዳልኩህ ልንገርህ! አንተ አንድ የፖለቲካ ሰው ሆነህ የህዝብ መሪ ለመሆን ከተነሳህ ያ ህዝብ ማ እንደ ሆነ ለይተህ ማወቅ አለብህ ። ያ ህዝብ በርግጥ ድምጽ እንደ ሚሰጥህ በዝርዝር ማወቅ አለብህ ። ያ ድምጽ የሚሰጥህ ሰው ለምን እንደ ሚመርጥህ ምን ስላደረክለት በፋት ማወቅ አለብህ ። ያንተ ፖለቲከኛ ተብዬዎች እንኳንስ ማ ለምን እንደ ሚመርጣቸው ማረጋገጥ ሳይሆን የህዝቡ ቁልፍ ችግር እንኳ ምን እንደ ሆነ አያቁም ። ይህን መሰል የፖለቲካ አላዋቂ ነው አየሩን ሚያጣብብ! ሰላም!!!

Horus
Senior Member+
Posts: 42716
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: በምርጫ ማግስት ብልጽግና የገባበት ፈተናና የብርቱካን መደቅሳ ወሳኝነት

Post by Horus » 02 Jul 2021, 16:16

በቃ አሁን አቢይ አህመድ እጅግ ወሳኝ እጅግ ብልህ እጅግ ጥልቅ ዉሳኔ አደረገ !! ይህ ነው የፖለቲካ መሪነት ማለት !!! ዬቦ ኤቦ !! ይህ ነው የኢትዮጵያን ጠላቶች የምያሳፍር እውቀት !! የሽግግር መንግስት አንፈልግም። የምንፈልገው የህዝባችን አንድነጥ የፓርቲዎች አንድነት ነው !! በቃ አከተመ !! አቢይ አህመድ መሪነቱን አረጋግጧል !!!

DefendTheTruth
Senior Member
Posts: 13227
Joined: 08 Mar 2014, 16:32

Re: በምርጫ ማግስት ብልጽግና የገባበት ፈተናና የብርቱካን መደቅሳ ወሳኝነት

Post by DefendTheTruth » 02 Jul 2021, 17:22

Horus wrote:
02 Jul 2021, 16:16
በቃ አሁን አቢይ አህመድ እጅግ ወሳኝ እጅግ ብልህ እጅግ ጥልቅ ዉሳኔ አደረገ !! ይህ ነው የፖለቲካ መሪነት ማለት !!! ዬቦ ኤቦ !! ይህ ነው የኢትዮጵያን ጠላቶች የምያሳፍር እውቀት !! የሽግግር መንግስት አንፈልግም። የምንፈልገው የህዝባችን አንድነጥ የፓርቲዎች አንድነት ነው !! በቃ አከተመ !! አቢይ አህመድ መሪነቱን አረጋግጧል !!!

I remember about General Kemal Gelchu here, who was given a key position in the government (security chief of Oromia region) while he was in his own party at the beginning of the current change. I heard him at one time saying he was working during the day for his government job, after the job in the evening and on all of his free time he kept himself busy with his party politics job, as a leader of an opposition party of the incumbent.

There was a clear conflict of interest and he was fired withing very short time, it was in fact weird from the beginning.

I think he has given up on his party and the government embarrassed him gladly and gave him a position in the country's defense system currently, I think but not sure.

Daud Ibsa also demanded that he should be part of the government while waging armed fighting against the government itself, and I wounder how such constellation would ever work.

Daud Ibsa didn't want to follow the road of General Kemal Gelchu and now he is in a limbo, he doesn't have even a political party anymore.

Ethiopian politics is filled with full of intrigue, everyone trying to outsmart the rest, country's interest is secondary for them, many of them are motivated by their own narrow interest than that of the country.

Using the name of the country is only until they come to power, then it is all about how to plunder the same country. ስሾም ያልበላ፣ ስሻር ያልቀሳል፣ ነዉ እስካ አባበሉ።

If such constellation may ever happen, then say goodbye to accountability because everybody will start to blame the other. This could be very dangerous.

All said the message of the PM in this video is different from what you stipulated here, he said we will incorporate you (the opposition) into the government, which is the executive branch. To do so for the legislative branch the party in power has no mandate, what so ever, in my view. This mandate is solely that of the electorate.

Post Reply