Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Wedi
Member+
Posts: 8649
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

በዛሬይቱ ኢትዮጲያ የዲፋክቶ ሀገራዊ መንግስት የመፈጠሩ እውነታ፦

Post by Wedi » 01 Jul 2021, 16:20

ኢትዮጲያዊያን በሙሉ ዛሬ በሀገራቸው ሉዓላዊ የግዛት ህልውና እና በአቢይ ስልጣን መካከል አንዱን የመምረጥ በሚያስገድድ መስቀልኛ መንገድ ላይ የቆሙ ናቸው- ምርጫቸው ምንድነው???

**ወንድወሰን ተክሉ** (Wondwossen Teklu Wondelove)

👉 በዛሬይቱ ኢትዮጲያ የዲፋክቶ ሀገራዊ መንግስት የመፈጠሩ እውነታ፦

«እኛ መጀመሪያኑ ወደ ትግራይ የገባነው ትግራይን በOccupation ይዞ ለመቆየት ሳይሆን ሰራዊታችንን እና የጦር መሳሪያዎቻችንን ለማውጣት ነው» አቢይ አህመድ ዛሬ ጥያቄ እንዲጠይቁ ሳይሆን የተነገራቸውን አድምጠው በማጨብጨብ እንዲያስተጋቡ ለጠሯቸው በአስሮች ለሚቆጠሩ «ጋዜጠኞች» ከትግራይ የወጡበትን ምክንያትና መንገድ ሲያስረዳ የተናገረው ነው፡፡

እንደ አቢይ መራሹ መንግስት ግልጽ ውሳኔና አቋም መሰረት ባለፈው ኖቬምበር አራት ቀን 2020 ላይ «የህግ የበላይነትን ለማስከበርና የትግራይን ህዝብ ከጁንታው አገዛዝ ነጻ ለማውጣት » ተብሎ ወደ ትግራይ የዘመተው የመከላከያ ሰራዊት ዋና እና ብቸኛ ግብ በትግራይ ያለውን የመከላከያ ሰራዊትና የተለያየ የጦር መሳሪያን ለማውጣት ብቻ እና ብቻ ነው በሚል ከደመደመ በኃላ ዛሬ ያንን ሚሽን በማጠናቀቁ ጦሩ ከትግራይ ሙሉ በሙሉ በመውጣት ክልሉን ለትህነግ አስረክቧል ያለ ሲሆን በዚህም መሰረት «ከዛሬ ጀምሮ በትግራይ ላለው ማንኛውም ጉዳይ የፌዴራሉ መንግስት አያገባውም » በማለት በግልጽ አውጇል፡፡

ይህ አቢይ መራሹ መንግስታዊ እወጃ ዘርዘር ተደርጎ ሲታይና ጠቅለል ተደርጎ ትርጉሜውን ምን ማለት ነው ብሎ ሲጠየቅ የምናገኘው መልስ «መጀመሪያም ትግራይ የገባነው ለህዝቡና ለአጠቃ ኢትዮጲያዊ ሉዓላዊ ግዛት ብለን ሳይሆን በትግራይ ያለውን የመከላከያ ሰራዊታችንን እና በጁንታው እጅ የገባውን የጦር መሳሪያን ብቻ በማውጣት ክልሉን አሸባሪው ጁንታ እንደፈለገ እንዲያደርገው ለቅቀንለት ለመውጣት ነው» የሚል መልስ ይሆንና ይህ መልስ ደግሞ በአጭሩ ሲጠቃለል ትግራይን ዲፋክቶ እስቴት በማድረግ ከኢትዮጲያ መገንጠል ማለት ሆኖ እናገኘዋለን፡፡

የአቢይ መራሹ የኦህዴድ ብልጽግና መንግስት የትግራይን ግዛት ከኢትዮጲያ የመገንጠሉን እርምጃ ዛሬ ያለምንም አንጃ ግራንጃ በግልጽና በአደባባይ ፍርጥ አድርጎ የገለጸ ሲሆን ይህንን አስደንጋጭ እርምጃውን ግን ኢትዮጲያዊያኑ ማወቅ በሚገባቸው መጠን ተረድተው አላወቁትም ወይም ያወቁትም ቢሆኑ በኢትዮጲያ ግዛታዊ ሉዓላዊነት እና በአቢይ ስልጣን መካከል አንዱን መምረጥ ተምታቶባቸው ዝም ብለው እያዩት ያለ .....Read more

Please wait, video is loading...