Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 11594
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

"ወዳጄ መወገዝ ያለበት የኔ መናገርና የንፁሃን ድምፅ መሆን ሳይሆን ያንተ ዝምታ ነው ‼️" ዓምዶም ገ/ስላሴ ከዓረና

Post by sarcasm » 26 Jun 2021, 08:17

#እነ_ኢሳት_ተነስተውብኛል ‼️
🚥🚥🚥🚥🚥

ኢሳት ትናንት "በኣሉላ ኦፕሬሽን በTDF የተማረኩ ወታደሮች" የሚያሳይ ፎቶና የሰላም ድርድር የትግራይ ብቻ ሳይሆን የሁላችን ጉዳይ መሆኑ የሚያስረዳ የፃፍኩት ኣጭር ፅሑፍ ተከትሎ " ዓምዶም ገብረስላሴ ከጁንታው ኣብሮ እየሰራ ነው" የሚል ፍረጃ በማስቀደም መንግስት እንዲያስረኝ ምክሩን ለግሰዋል።
ኢሳቶችን መፈራረጁ ይቆይብንና በትግራይ እየተካሄደ ስላለ ጦርነት ሃቀኛ ምስል የሚያሣይ ዘገባዎች ብትሰሩና ለሁላችን የሚበጅ ሰላም በማምጣት የራሳቹ ድርሻ ብትጫወቱ ይሻል ነበር።

ካልሆነ በሰለማዊ ትግል የሚያምን ሰለማዊ ታጋይ ኣሸማቅቃቹና ኣሳስራቹ ትጥቅ ትግል ብቸኛ ኣማራጭ ሆኖ እንዲታይ ባታደርጉ መልካም ነው።

ኢሳት ከዚ በፊት "95 ለ 5 ሚልዮን ነውና እንጨፍጭፋቸው" ያላቹበት ለትግራይ ህዝብ ይቅርታ ኣልጠየቃቹም።
ይሄ ክፉ ምኞት ተሳክቶ ከዕቅዳቹ በላይ 4 ሃገሮች በመጋበዝ የትግራይ ህዝብ ተጨፍጭፈዋል።
ከዚህ በፊትም እነ Seyoum Teshome የመሳሰሉት የኢህኣዴግብልፅግና ኮካዎች በትግራይ ካለው እልፍ ኣእላፍ ግፍ ኣንድ ሁለቱ በማጋለጣችን በክልሉ ካሉት ግምባራቸው መታት ካለባቸው ቶፕ 4 ሰዎች ውስጥ በማካተት(ከ ጀነራል ፃድቃን፣ ወዲ ወረደና ጌታቸው ረዳ እኩል በመፈረጅ ከሁለት ሰዓት በላይ የቆየ ውትወታ ኣቅርበዋል።

የኣብን ደጋፊዎች ደግሞ መንግስት በኣዲስ ኣበባ እርምጃ እንደ ወሰደብኝ በፌስቡክ ፅፈዋል።

በዚህ ኣካሄዳቹ ሁላቹም በሃሳብ ልታሸንፉኝ ኣትችሉም ምክንያቱ ሃቅ ከኔጋር ነች። ይልቁን እኔን የማሸነፍ ኣንድ ብቸኛ ጥበብ ራሴ ልንገራቹ።
ጎበዝ ጎበዝ ባለ ሞያ ጋዜጠኞች ወደ ትግራይ ትልኩና ያለውን ሃቅሳትጨምሩ ሳትቀንሱ እንዳለ እኔጋ ሳይደርስ ኣስቀድማቹ መዘገብና መንግስት መፍትሄ እንዲያበጅለት ማገዝ ብቻ ነው።


እኔ የምታገለው ለትግራይ ህዝብ ነው። ህዝቤ እየሞተ፣ እየተራበ፣ እየተፈናቀለ፣ ሴቶች እየተደፈሩ እያየሁ ዝም ማለት ኣልችልም። በኣውሮፕላን በገበያ ቀን ድብደባ ንፁሃን ህፃናት፣ ሴቶች፣ ኣባቶች እየሞቱ እያየው እንዴት ዝምእላለው።

ወዳጄ መወገዝ ያለበት የኔ መናገርና የንፁሃን ድምፅ መሆን ሳይሆን ያንተ ዝምታ ነው ‼️


"ትግራይ ትስዕር" ብለህ ፅፈሃል የሚል ክስም ያቀርባሉ። ልክ ነው ብያለው። መጀመርያ ግን ሰለማዊ ድርድር ይበጀናል ብያለው። ይሄ ማለት ሁላችን ኣሸናፊ የምንሆንበት ብቸኛ መንገድ መሆኑ ሰብክያለው።

ትግራይ ካላሸነፈች ለ100 ዓመት እንዳትነሳ የማድረግ የመንግስት እቅድ ይሳካል ማለት ነው። ትግራይ የማንበርከክ ዕቅድ ደሞ በፍፁም ኣልደግፍም።
ትግራይ ትስዕር ማለት ትግራይ ኣትጠፋም ማለት ነው።


*ሰላማዊ ድርድር የችግሮቻችን ብቸኛው መፍትሄ ነው‼️

* ትግራይ ትስዕር ❗️
Please wait, video is loading...