Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Ejersa
Member
Posts: 3978
Joined: 05 Nov 2019, 10:39

ጣፋጭ ድል ከራያ ኦፍላ ኮረም!!!!

Post by Ejersa » 24 Jun 2021, 14:38

ሰሞኑን ከሃውዜን እስከ ቆላ ተንቤን: ከአገረ ሰላም እስከ አግበ የጭላ: ከብዘት እስከ እንጥጮ እስከ ራማ ድረስ ጀግናው የመከላከያ ሰራዊታችን ባካሄደው የአሰሳ ዘመቻ የተቀጠቀጠው የጁንታው ርዝራዥ ማምለጫ ሲያጣ እንደለመደው ጥሻ ለጥሻ በመሸሽ ሸጡን ተከትሎ ወደ አበርገሌ እና ወደ ኮረም ዙሪያ በመምጣት ተደብቆ ከረመ::
ዛሬ ሃሙስ ቀን የኮረም የገበያ ቀን ነው::

ታዲያ ጁንታው የዛሬውን ሃሙስ የኮረም የገበያ ቀንን በማስታከክ ሰርጎ ገቦችን ገበያተኛ በማስመሰል በማለዳ ወደ ኮረም ከተማ አስገባ:: ቀጥሎም የጁንታው ርዝራዥ ሃይል አድነባ ተብሎ በሚጠራው የኮረም ገጠር አካባቢ ጥይት መተኮስ ጀመረ::

ይህ ማለት በከተማ ውስጥ እና ከከተማ ውጭ ጥቃት በመክፈት ከእጁ የወጣውን የራያን ህዝብ ለመበቀል ያለመ ነበር:: መቼም ቢሆን የጁንታው ሃይል ከተማን ቀርቶ የገጠር ቀበሌን ለመቆጣጠር የሚያስችል ቁመናም ሆነ ሞራል እንደሌለው በጣም ሊታወቅ ይገባል!!!! በማይካድራ እንደፈፀመው ሁሉ የራያን ህዝብ ለመበቀል ግን ሙከራውን ቀጥሏል:: ታዲያ ይህን የጁንታውን ሃሳብ እና እንቅስቃሴ የተገነዘበው የራያ ኦፍላ ኮረምን እና አካባቢውን እያስተዳደረ ያለው ኮማንድ ፖስት ሦስት ነገሮችን በአስቸኳይ አደረገ::

1ኛ) የዛሬው የኮረም ገበያ ዛሬ ጧት ሶስት ሰዓት ገደማ በፍጥነት እንዲፈርስ አደረገ

2ኛ) ህዝቡ ወደ ቤት እንዲገባ አዘዘ:: ከገጠር ለገበያ የሚገባውንም ባለበት እንዲቆይ አደረገ::

3ኛ) ገበያው እንዲፈርስ እና ህዝቡ ወደ ቤት እንዲገባ ካደረገ በኃላ አድነባ አካባቢ የሽፍታነት ተግባር ሲፈፅም የነበረውን ርዝራዥ የጁንታ ሃይል ዛሬ ከ 9:00 ሰዓት ጀምሮ ጀግናው ሰራዊታችን አይቀጡት ቅጣት በመቅጣት የሞተው ሞቶ የተማረከው ተማርኮ የተረፈው ፈርጥጦ ወደ ዛታ እና ወደ ሰቆጣ መስመር ሸሽቷል!!!! የሙት ቁጥሩን በውል ማረጋገጥ ባልቻልም ተማርከው ወደ ወልዲያ የተወሰዱት ግን 29 መሆናቸውን የአይን እማኞች አረጋግጠውልኛል!!!! የፀጥታ ሃይላችን ወታደራዊ የአመራር ብስለት : ለህዝብ ደህንነት ያለው ተጨናቂነት : ከህዝቡ ጋር ያለው ጥልቅ ግንኙነት እና ያካበተው ወታደራዊ ብቃት በቃላት የሚገለፅ አይደለም!!!!! ግሩም ድንቅ ተብሎለታል!!!!

ትላንትና ፍቅረ ወልዳ በተባለው የሰቆጣ መስመር ላይ ጁንታው ተመሳሳይ ቅጣት የተቀጣ ሲሆን ከሶስት ቀናት በፊት ደግሞ በራያ ባላ አካባቢ ታይቶ የነበረውን ርዝራዥ ሰራዊታችን እንዴት እንዳደረገው እዚህ መፃፍ ይቀፈኛል!!!! የጁንታው ተባራሪ ሃይል እሬሳቸውን መቅበር እንኳን ሳይችሉ ቀርተዋል!!!! በራያ ባላ ዙሪያ ሁሉም አመድ ሆነዋል!!!! ዛሬም በኮረም ዙሪያ በተደረገው አፋጣኝ ኦፕሬሽ ግማሽ ቀን ያህል እንኳን መዋጋት ሳይችል ጁንታው በርካታ ሙት : አያሌ ቁስለኛ እና ምርኮኛ ሆኖ የቀረው ጥቂቱ እግሬ አውጭኝ ብሎ ወደ ዛታ እና ሰቆጣ መስመር ፈርጥጧል!!!!! በጣም አሳዛኙ ነገር ጁንታው አሁን በወታደርነት የሚጠቀመው ታዳጊ ህፃናት ልጆችን ነው:: ከኪሳቸው የሚገኘው ደግሞ ሃሽሽ እና ቆሎ ነው:: ((መቼም አስከሬን መለጠፍ ከኢትዮጵያዊ ወግና ባህላችን ውጭ በመሆኑ አላወጣውም እንጅ እጄ ላይ በርካታ ፎቶዎች አሉ!!!)) በአጠቃላይ ግን የጁንታው መቀበሪያ ራያ ላይ ነው የሚለውን ትንግርት ልብ ይሏል!!!!

ጁንታው ሁሌም ቆላ ተምቤን እና የተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች ላይ ሲደቆስ እየፈረጠጠ ወደ ራያ ይወርዳል!!! ከዚያም ራያ ላይ አመድ ይሆናል!!!! የዛሬ ሶስት ወራት ገደማ በማይማእዶ በሺህ የሚቆጠር የጁንታው አስከሬን እንደተቆጠረ መግለፃችን ይታወሳል!!!! ትላንትም ትላንት ወዲያም ዛሬም ይሄው ሆኗል!!!!! እያዞረ እያሽከረከረ ወደ ራያ ያመጣቸዋል!!!! ፍፃሜያቸው ራያ ላይ ለመሆኑ እየታየ ይገኛል!!!! ጁንታው አለሁ ለማለት እዚህም እዚያም ሊያሸብር ቢሞክርም ምሱን እያገኘ በየጊዜው እያለቀና እየተመናመነ ይገኛል!!!! ጁንታው አሁን የቀረው የሚንተፋተፍ ምላሱ ነው!!!! እሱንም በቅርቡ ይውጥዋል!!!!
ደጀን አሰፋ

Axumezana
Senior Member
Posts: 19139
Joined: 27 Jan 2020, 23:15

Re: ጣፋጭ ድል ከራያ ኦፍላ ኮረም!!!!

Post by Axumezana » 24 Jun 2021, 16:03

Keep dreaming!

euroland
Member+
Posts: 7957
Joined: 08 Jun 2018, 12:42

Re: ጣፋጭ ድል ከራያ ኦፍላ ኮረም!!!!

Post by euroland » 24 Jun 2021, 16:11

Axumezana wrote:
24 Jun 2021, 16:03
Keep dreaming!
This, from certified dreamer, the Gilgel junta
Everything the ENDF said has been 100% accurate and truth while every thing your dead junta said was 100% false.,,,,go figure

dawwit
Member
Posts: 4663
Joined: 21 Apr 2015, 12:18

Re: ጣፋጭ ድል ከራያ ኦፍላ ኮረም!!!!

Post by dawwit » 24 Jun 2021, 16:42

every time they say ቆሎ ና ሀሽሽ በኪሳቸው ተገኘ። you know they are gaslighting Bacha style. anyways, we will release the video here

Abere
Senior Member
Posts: 15401
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: ጣፋጭ ድል ከራያ ኦፍላ ኮረም!!!!

Post by Abere » 24 Jun 2021, 17:15

Ignorant TPLF (evil ሓርነት ትግራይ) does not know we are living in a different time. That their own only old good time where they tricked North Wolo Amhara and Gondar to enter into Amhara provinces by riding on Amhara backs to enter to Addis Ababa to later annexed is over. That period of forced Tigre ( Amhara coerced to be Tigre ) is over, TPLF may try a million times but it will be burred a million times a million miles under by Amhara force. If even TPLF escapes Ethiopian Defense force, Amhara Fano is not going to let them cross an inch. I think TPLF as fugitive rebels are sporadically coming out where there is no man around the town to loot, shop their food and save themselves from starvation. TPLF created with already dead purpose, it lived with that dead purpose, now they are buried along with it. አሁን የሚቀባጥሩት ሁሉ የጻዕረ ሞት ሲቃ ነው።

Post Reply