Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Naga Tuma
Member+
Posts: 7362
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

አደዋን ኣላሳነስም?

Post by Naga Tuma » 03 Jun 2021, 18:02

ፈረኦ ኣክናተን ከዛም ሙሴ የሆነዉ ምድር ላይ ካለዉ ኣልፎ ጸሃይን ያየ መሪ ነበር። ከእሱ በላይ የነበረ ምድራዊ መሪ ይሄ ነዉ ብሏል ሲባል ኣልሰማሁም። ኣክናተን ጥነት ጊዜ የወጣ ስም ነዉ። አከቶ የሚል ስም ከየት የመጣ ወይም ምን ማለት እንደሆነ የማላዉቀዉ በቅርብ ጊዜ የነበረ ነዉ።

የሠ እና የሮማኑ ቁጥር III መመሳሰል ሠ ከሮም ሃያልነት በፊት ነበርኩ የሚል ይመስላል።

የንግስት ሳባ የጥንት ጊዜ ገናናነት እና ሰበ/ሰብ ቃሎች ሆሞ ሳፕያንስ ስያሜ ቀድሞ መኖር የዘመኑ ሳይንስ ዉስጥ ጠልቀን ኣልተገኘንም የሚሉ ይመስላል።

በዘመናዊነት መባቻ ላይ ኢትዮጵያን ከመሩት ኣጼዎች ኣንዱ የንግስና ስማቸዉ ኣለምሰገድ ብለዉ ሰይመዉ እንደነበር ኣንብቤኣለሁ።

የአደዋ ጊዜ ከፍጥረታችን ጊዜ ጀምሮ የምናዉቀዉን ነፃነት ማንም ኣይገፈንም ብለዉ የተነሳ ይመስላል፣ ያኔ የኖረዉ ህዝባችን።

በቅርቡ የኖቤል ሽልማት ኮሚቴ አባል ታሪክ እነደምያሳየዉ ሁላችንም ኢትዮጵያኖች ነን ብላ መስክራለች።

ታድያ ህዝባችን ከፍጥረቱ እስከ ዘመኑ ወይም ይህ ዘመን ድረስ ያምያዉቀዉ ነፃነት ነዉ ማለት ስህተት ኣለዉ?

ከሌለዉ ወይም እዉነትነት ያለዉ ከሆነ አደዋ ኣፍርሪካን እንዳተረፈ ብቻ ማየት እና መተንተን አደዋን ማሳነስ ኣይሆንም?