አድዋ በብረት የተካሄደ ዲፕሎማሲ ነበር። አፍሪካ የነጭ አህጉር ከመሆን ያስቆሙ የምኒልክ ኢትዮጵያዊያን ነበሩ ።
ዛሬ ያለው በሰላም የሚካሄድ ያድዋ ጦርነት ነው። ይህ የዛሬ ትግል ዳግማዊ አድዋ ተብሎ መሰየም አለበት ። አገር አቀፍ ጦርነት ነው። ያኔ አገር ወራሪና ባሪያ ነጋዴን አባረርን ፤ ዛሬ ደሞ በብስብስ ስንዴ ደልሎ በጅ አዙር የሚገዛን ቅኝ ገዥን እምቢ ብሎ ነጻ ታዳጊ ሕዝብ መሆን ነው ስራችን .።
የፒፒ መግለጫ በጣም ጥሩ ነው! ቁም ነገሩ ከፓርቲ ፖለቲካ ነጻ በሆነ መንፈስ መሬት ላይ መተግበር ነው ።
ይህ ከሆነ በኋላ ለዚህ አገር አቀፍ ጦርነት መሳካት መደረግ ያለበትን ሁሉ ማድረግ የመንግስትና ሕዝብ ስራ ይሆናል ማለት ነው ።
ምሳሌዎች፣
1
ኢትዮጵያ እስከ 5 ሚሊዮን ዲያስፖራ ባለም ላይ አላት ። እነሱም ከ5 ቢሊዮን ዶልላር በላይ ባመት ወደ ኢትዮጵያ ይልካሉ ። አሁን ይህን 5 ቢሊዮን ወደ 8 እና 10 ቢሊዮን ዶላር እንዴት ከፍ እንደ ሚል መንግስት ፕላን ማርቀቅ አለበጥት ። ኢትዮጳዊያን ራሳችን የራሳችንን እድገት ፋይናንስ ማድረግ እንችላለን ። ለዚህም ....
አዲስ የኢትዮጵያ እድገት ባንክ (አለማቀፍ) ተቋቁሞ ዲያስፖራውን ወደ እድገት ባንክ ማሳደግና የምዕራብ እቀባን መስበር ነው ።
ይህ እንዲሆን ዲያስፖራው ኢትዮጵያዊ ዜግነቱን እንዲመለስለት፣ እንዲረጋገጥለት የግድ ነው። ዜግነት የምይሰማው ዲያስፖራ ሃብቱን እውቀቱን ጉልበቱን በኢትዮጵያ ላይ ሙሉ በሙሉ አይሰጥም። ይህ አንዱ ግዙፍ ጉዳይ ነው።
2
የሰኔው ምርጫ ተሳካም አልተሳካ፣ ልክ ምርጫው እንዳበቃ የብልጽኛ ፓርቲ የአንድነት መንግስት የማቆም ጥሪ አቅርቦ ቁልፍ ቁልፍ የሆኑ ፓርቲዎችና ከመንግስት ውጭ ያሉ ልሂቃንን አንድ የሚያደርግ የሰላም ጉባኤ መጥራት ግዴታው ነው ።
ዳግማዊ አድዋ ያን መሰል ሃገራዊ አንድነት በፖለቲካው፣ ሚሊታሪና ኢኮኖሚ መስኮች ባስቸኳ በመጥራት ያሜሪካና ግብጽ ሴራን ማክሸፍ ለነገ የሚባል አይደለም ። ሽግግር ሽግግር ለሚለው ያሜርካ አሽጥር መልሱ ራሳቸው ኢትዮጵያዊያን ያለማንም ነጭ ሰብሳቢና አስታራቂ እንደ ህጻን ሳንታዘዝ አንድ መሆን ነው ።
3
ከላይ እንዳልኩት ከ5 ሚልዮን ሕዝብ በላይ 180 የአለም ቋንቋ የሚናገሩና በአለም ቋንቋዎች ሁሉ እስከ ከፍተኛ ትምህርት የሰልጠኑ ዲያስፖራ ያላት ኢትዮጵያ በደካማ የህዝብ ግ ንኙነትና ዲፕሎማሲ ነጻነቷን ማስደፈር የነአቢይ ያመራር ድክመትና ጠባብነት ነው።
ኢትዮጵያን የሚጠቅሙ ሊቃውንት ሁሉ በአለም ላይ ፈልጎ እንዲሰበሰቡ ማድረግ የመግስት ስራ ነው ። አለያ መንግስትም አገርም ፓርቲም አይኖርምና ።
ይህን ብቻ እንኳን ብናደርግ የአሜርካ እቀባና ጥቃት መስበር እንችላለን