Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum

MatiT
Senior Member
Posts: 11549
Joined: 16 Feb 2013, 10:18

Re: **ኤርትራን ያልቆነጠጠ የአለም ማእቀብ-ኢትዮጽያንን አይኮረኩራትም፣** ኤርትራ የኢትዮጵያ ትልቅ ምሳሌ ናት"

Post by MatiT » 25 May 2021, 12:49

ሀገራዊ ህልዉናችን በሰዉ ሀገር ቪዛ ላይ የተመሰረተ አይደለም፡፡ ለቪዛ አሊያም ለሚሰፈርልን የድጋፍ እህል ብለን ብሄራዊ ክብራችንና ሀገራዊ ሉዓላዊነታንን የሚጻረር ማንኛዉንም የዉጭ ጫና አሜን ብለን አንቀበልም፡፡ እጃችንን ጠምዝዘዉ የህዳሴ ግድባችን እንዳይሳካ በማድረግ ለዘለዓለም ደሀ እና የፖሊሲ ነጻነት የሌላት ተላላኪ ሀገር ሆነን እንድንኖር የሚመኙ ሃይሎች ምኞታቸዉ ምኞት ብቻ ሆኖ እንደጉም እንደሚበን በተጨባጭ ማሳየት አለብን፡፡ ለዚህ ደግሞ ተግተን በመስራት የምንመገበዉን ስንዴ ማምረት፣ የጀመርናቸዉን ፕሮጀክቶች በተለይም የታላቁ ሕዳሴ ግድባችንን በአንድነት ተረባርበን በማጠናቀቅ ጥንካሬያችንን ለወዳጅም ለጠላትም ማሳየት አለብን፡፡ በአንድነት ከቆምን የጀመርነዉን እንጨርሳለን፣ አምርተን መመገብ እንችላለን፡፡ በአጠቃላይ ከድህነት እንላቀቃለን፡፡ ያኔ ብሄራዊ ክብራችንን በአስተማማኝ እናስጠብቃለን፡፡ ህልዉናችን በዉጭ ሀይሎች እጅ ላይ ሳይሆን ራሳችንን በራሳችን በማልማት አቅማችን፣ በዉስጣዊ ጥንካሬያችን እና በአንድነታችን ላይ የተመሰረተ ነዉ!

ኢትዮጵያ እያሸነፈች ትቀጥላለች።

አቶ አዲሱ ቂጤሳ


kerenite
Member
Posts: 4680
Joined: 16 Nov 2013, 13:15

Re: **ኤርትራን ያልቆነጠጠ የአለም ማእቀብ-ኢትዮጽያንን አይኮረኩራትም፣** ኤርትራ የኢትዮጵያ ትልቅ ምሳሌ ናት"

Post by kerenite » 25 May 2021, 13:43

MatiT wrote:
24 May 2021, 22:30
"Eritra ye ethiopia tiliQ misale nat" alech weyzero matit or whoever said it.

Let me educate you here:

Issu's eritrea can endure any sanction whether it is political or economical while it doesn't get any aid from uncle sam. Hey! Not because eritrea is rich but due to the stubborness of the dictator and the utter contempt he has for eritreans. Eritreans would welcome any foreign aid.They are in dire need of it.

What about abi's ethiopia?

Hahaha.. Spare us this "we will reaccess our relation with the USA" as announced by their foreign ministry.This is meant for public consumption. Come on! Without the aid it gets from the USA and the European union, ethiopia cannot last even for one month as a viable country.

This is the bitter truth!!!

MatiT
Senior Member
Posts: 11549
Joined: 16 Feb 2013, 10:18

Re: **ኤርትራን ያልቆነጠጠ የአለም ማእቀብ-ኢትዮጽያንን አይኮረኩራትም፣** ኤርትራ የኢትዮጵያ ትልቅ ምሳሌ ናት"

Post by MatiT » 25 May 2021, 16:14

**አስሩ አሜሪካን የማንበርከኪያ ዘዴዎች**
ፋሲል የኔ አለም/ኢሳት

አንድ- አንድ ከሆንን ወይም ከተባበርን
ሁለት- በመላ አገሪቱ ሰላምና መረጋጋት ማስፈን ከቻልን
ሶስት- ምርጫውን ጨርሰን ዝንቅ አስተዳደር እና ህይወት ያለው ፓርላማ ከመሰረትን
አራት- አባይን አጠናቀን ሃይል ማመንጨት ከጀመርን
አምስት- ከቻይናና ሩስያ ጋር ያለንን ሁለንተናዊ ግንኙነት ካጠናክርን
ስድስት- ያለንን እየተካፈልን ለመብላትና ከምዕራቡ ዓለም የሚገቡ የቅንጦት እቃዎችን ከቀነስን
ሰባት- ባለስልጣኖቻችን እንደ ህዝቡ ለመኖር ከወሰኑ
ስምንት- ዲያስፖራው ስራ እየሰራ አገሩን በታታሪነት ከረዳ
ዘጠነኛ- ህዝቡ በብሄራዊ ስሜት ቁጭት በተለይም ወጣቱ ከምዕራባውያን የስነልቦና ባርነት ተላቆ በራሱ እንዲቆምና ለለውጥ እንዲነሳ ከተቀሰቀሰ እና
አስረኛ- የአፍሪካ ህብረትና ተመድን በመጠቀም ብልጠት የተሞላበት የዲፕሎማሲ ስራ ከተሰራ

ኢትዮጵያ ወደ አሜሪካ ሳትሄድ አሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ ትመጣለች። እጃቸውን ስመን ሳይሆን፣ እጃችንን ስመው ይወዳጁናል። ይህ አጋጣሚ ለዘመናት ሰፍኖ የቆየውን የአዛዥና ታዛዥ ግንኙነት ለመስበር ሊጠቅም ይችላል። ፍተናዎችን እንደ መልካም አጋጣሚ ለመጠቀም፣ ቆራጥነት፣ ጽናት፣ ብልጠትና አስተውሎ መጓዝን ይጠይቃል።


Post Reply