Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 11594
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

የኢትዮጵያ እናቶች ግን . . .

Post by sarcasm » 25 May 2021, 06:57

የኢትዮጵያ እናቶች ግን የአካል ወይም የስነልቦና ችግር ላለባቸው ልጆቻቸው የሚሰጡት ማበረታቻና ኮንፊደንስ እንዲኖራቸው ለማድረግ የሚዋሹት ነገር መቅረት አለበት!
ያለዚያ ልጆቹን ዋጋ ያስከፍላል።

ለምሳሌ እኔን እናቴ በልጅነቴ አንተ እኮ አለም ላይ ካሉ ልጆች ሁሉ ቆንጆው ነህ ብላ ሞራል ሰጥታኝ ትምህርት ቤት ውስጥ የአለም ቆንጆ ማነው ሲባል እኔ ብዬ መልሼ ውርንጭላ ተብየ ተሰድቤያለሁ😭

አንድ አጎቴም አለ እናቱ አየር ላይ የሚበር ነገር ጠባቂ ነህ ብላው ኤርፖርት ለአውሮፕላን ጋርድነት ሊቀጠር ቢመላለስም የአውሮፕላን ዘበኛ የለውም ብለውት አሁን አንበጣ እየጠበቀ ነው😂

እናቱ ንጉሥ ትሆናለህ ብላውም የቼዝ ነው የሀገር ብሎ ሳይጠይቅ መከራውን የሚበላ አለ😂

እናቶቻችን እንትን ትሆናለህ ሲሉን የምን ማለት ጥሩ ነው ኦገን
Please wait, video is loading...