Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
SDAbraha
Member
Posts: 7
Joined: 07 Dec 2020, 15:24

ጥያቄ ለፕሮፌሰር አለማየሁና ሌሎችም የአብይ አክላኪዎች

Post by SDAbraha » 07 May 2021, 06:55

ፕሮፌሰር አለማየሁ ሌሎችም ህሊና ያላችሁ ይችን ጥያቄ መልሱልኝ። ወያኔን ያን ያክል ስትቃወሙ የነበር የዘረጉትን ኋላቀር ከፋፋይ አፓርታይድ አገዛዝ ወይስ ትግሬነታቸውን?? ያው የወያኔ ኦነግ ኋላቀር አፓርታይድ አገዛዝ ተጠንክሮ በቀጠለበት ሕዝብ ለአመታት ከኖረበት እየተፈናቀለ በጅምላ እየትጨፈፈ ከተማ እየተቃአጠለ ወያኔ በኦሕዲድ ተተክቶ ተረኝነት ነግሶ አገዛዙን መደገፍ ፀረትግሬነት ከመሆን ውጭ ምን ይባላል?? የእማማ ኢትዮጵያን ልጆች አንዱን ወዶ አንዱን ጠልቶ ምን አይነት ኢትዮጵያን መውደድ ነው?? እኔ ጎሰኝነት እጅግ የምጠየፍ ውህድ ኢትዮጳይዊ ነኝ። ባገሬ ኢትዮጵያዊነት ነግሶ ሕዝብ በዜግነት በነፃነት በእኩልነት በወንማማችነት እንዲኖር የምመኛና ለዚህ የሚታገሉትን ሁሉ ጎሳ ሀይማኖት ሳለይ የምደግፍ የምረዳ አድርይባነትን የምጠየፍ ኩሩ ኢትዮጵያዊ ነኝ። አምላከኢትዮጵያ ለሕዝባችን ሰላም ፍቅር ያውርድልን አሜን!!!