Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 42555
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

ምርጫ 2013 ግዙፍ መማሪያ ተሞክሮ ይሆናል

Post by Horus » 23 Apr 2021, 21:45

የሚቀጥለው ምርጫ ይሳካም አይካ፣ሙሉም ሆነ ጎደሎ፣ በረብሻም ይታጀብ በሰላም ታሪካዊ የሆነ የመጀመሪያ ሙከራ ይሆናል።

በስልጣን ላይ ያለው ብልጽግና በሃይልም ሆነ በሰላም ካጭበረበረ እና ያንድ ፓርቲ ገነንነት ከቀጠለ ያ ራሱ ትልቅ ትምህርት እና ቀጥሎ ሕዝቡ ምን ማድረግ እንዳለበት ያሳያል።

ምርጫው እስከ ተወሰነ ድረስ ተሳክቶ የተለያዩ ፓርቲዎች መንግስት ውስጥ ከገቡ ካሁን በተሻለ ለሕዝብ ክፍት የሆነ መንግስት እንዲኖር ያስገድዳል፣ ማጆሪቲው ብልጽግ ና ቢሆን እንኳን።

ሕዝብ በመንግስት ላይ ቅዋሜ ካላቸው ተቃውሟቸውን ማሳየታቸው (በስልፍ ወዘተ) እና የምርጫ መካሄድ አይቃረኑም። ስለዚህ የአማራ ተቃውሞ እየተደገ በአንድ ላይ መርጫ ማድረግ ይቻላል፣ መቻልም አለበት ።

ምርጫው ምንም አይጠቅመንም የሚሉ ፓርቲዎች ያለመካፈል መብታቸው መከበር አለበት፣ ማለትም አንድ ፓርቲ በምርጫ አላምንም ብሎ ቤቶ በቀመጥ መወቀስ የለበትም ፤ ሌሎች እንዳይከፈሉ የሚያስገድድ ተግባር እስካልፈጸመ ድረስ።