Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 42555
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

በኢትዮጵያ የወቅቱ ትግል ውስጥ ያሉት ሶስት ካምፖች እና ቅራኔያቸው

Post by Horus » 21 Apr 2021, 23:48


ኢህአዴግን ወርሰው በአቢይ ዙሪያ ያሉት ሃይሎች የቻይና ግሩፕ ብዬያቸዋለሁ።

አቢይን አውርደው ኢትዮጵያን ወይ ለማፍረስ፣ ወይ ለመከፋፈል የሚዋጉት የግብጽ ግሩፕ እላቸዋለሁ።

የዜግነት ዴሞክራሲ ለማምጣት ሚታገሉት የምዕራብ ግሩፕ አልኳቸው።

በግብጽና በምዕራብ ካምፖች መሃል ያለው ቅራኔ የማይታረቅ ነው። የነዚህ ሁለት አይሎች ፊት ለፊት ትግል የሚመጣቸው የግብጽ ቡድን አቢይን ማሸነፈ ከቻለ ብቻ ነው ። እስከዚያ ፊት ለፊት የሚጋጠሙት የግብጽና የቻይና ካምፖች ናቸው።

ሁሉም እንደ ሚያውቀው የፖለቲካ (ጦርም ፖለቲካ ነው) ጨዋታ ተጫዋቾች ያላቸው ፍላጎትና አላማ አራት ናቸው፤ እነሱም (1) ስልጣን፣ (2) ገንዘብ/ሃብት፣ (3) ዝና/መታወቅ እና (4) የማንነት ክብር (መከበር) ናቸው።

በዚህ መሰረት የቻይና ካምፕ ከግብጽ ካምፕ የሚያፋጃቸው አላማ ስልጣንና ገንዘብ ነው።

የቻይናና የምዕራብ ካምፖች ግብጾችን ለማስወገድ ትብብር ያደርጋሉ፤ ነገር ግን ከዚህ ትብብር ባሻገር መሰረታዊ የፖለቲካ ፊሎሶፊና የመንግስት ስርዓት ልዩነት አላቸው። ይህን ልዩነት በሰለማዊ የሕዝብ ምርጫ ለመወሰን መቻላቸው የሚታይ ይሆናል ።

የቻይና ቡድን ትልቅ ችግር እስትራክቸሩ በግብጽ ቡድን ሴሎች መያዙ ነው።

የምዕራብ ቡድን ትልቅ ችግር የዜጋ ፖለቲካ አማኞችን ባንድ ትልቅ ፓርቲ መደራጀት አለመቻሉ ነው ።

የግብጽ ቡድን ትልቅ ችግር የፖለቲካ አላማ አልባና ግዜ ባለፈበት የድሮ እና አሸባሪ እምነት ላይ ህይወቱን ማባከኑ ነው ።

ኬር ለኢትዮጵያ!
ሆረስ ዐይነ ኩሉ