ሙስጠፌ ትእግስቴ አልቋል ራሳችንን ለመከላከል አስፈላጊውን እርምጃ እንወስዳለን እያለ ነው።
....
የአፋር ክልላዊ መንግስት ከውስጥና ከውጪ ሆነው የአገሪቱን ሰላምና መረጋጋት ለማወክ እንደሚሰሩ ሀይሎች ሁሉ የአካባቢው ነዋሪዎች አንድነትና ትብብር እንዳይጠናከር በየጊዜው ጥቃት በመፈጸም አካባቢው የሁከት ቀጠና እንዲሆን የማድረጉን ተግባር አጠናክሮ ቀጥሎበታል።
በመሆኑም የሶማሌ ክልላዊ መንግስት ለአገር ሰላም ዋጋ በመስጠትና ለህዝቦች አንድነት በማሰብ እስካሁን ህዝባችን እየሞተና እየተሰቃየም ቢሆን ጉዳዩን በትእግስትና በማስተዋል ሲከታተለው ቆይቷል።
ይሁን እንጂ ያንድ ወገን ጥረት ዘላቂ መፍትሔ ሊያመጣ ስለማይችል በቀጣይ በክልላችን ነዋሪዎች ላይ የሚደርሰውን ሞት፣ መፈናቀልና የንብረት ውድመት ለመከላከል ማንኛውንም አስፈላጊ እርምጃ ለመውሰድ የምንገደድ መሆኑን እያሳወቅን ጉዳዩ ወደለየለት ግጭት ከማምራቱ በፊት የአፋር ክልል መንግስት ቆም ብሎ ማሰብ እንዲጀምርና የፌደራል መንግስትም የመፍትሔው አካል ለመሆን እንዲሰራ በጥብቅ ለማሳሰብ እንወዳለን።
መጋቢት 28-2013 ዓ.ም
የሶማሊ ክልላዊ መንግስት
ጅግጅጋ “